TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን የሚመራው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ማባረሩና ከነበራቸው ድርጅታዊ ሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። ድርጅቱ መስከረም 6/2017 ዓ.ም አካሄድኩት ያለውን ስብሰባ አስመልክቶ ባወጣው ባለ ሦስት ገፅ መግለጫ :- 1. አቶ ጌታቸው ረዳ 2. አቶ በየነ…
#Tigray
" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አቅዷል " - በህወሓት ጉባኤ ያልተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት
በህወሓት ጉባኤ ላይ ያልተሳፉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
በዚህም " ህገመንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን ሌላውን የማባረር ሞራልና ስልጣን የለውም " ብለዋል።
ከሰሞኑን በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማባረሩ ይታወሳል።
የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ " ህገ-መንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ሌላውን የማባረር ህጋዊና ሞራላዊ ስልጣን የለውም " ከማለት ባለፈ " መፈንቀለ መንግስት ለማካሄድ ማቀዱን ደርሰንበታል " ብለዋል።
" የህገወጡ ቡድን መሪ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጄኖሳይድ ፍትህ እንዲያገኝና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መታገል ሲገባው ጉዳቱ ወደ ቁጥር ጨዋታ በማውረድ የህዝብ መስዋእትና የወጣቶች ጉዳት ዋጋ እያሳጣው ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።
ከሰሞኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል " ኒው ሆራይዘን " ከተሰኘ የማህበራዊ ሚድያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ወቅትም " By the way ከአንድ ሚልየን በላይ አለቀ የሚለው ፤ ማስረጃ የለው፣ ጥናት የለው ፣ ለማስፈራርያ ነው የሚውለው። ተጨፍጭፈናል ለማለትም አይደለም ፣ ጄኖሳይድ ተፈፀመብን ለማለትም አይደለም። አመራሩ አስጨረሰን ይላል ፤ አመራር ለመምታት ፣ ስልጣን ለመያዝ የማይሰራ ነገር የለም። " ሲሉ ተናግረው ነበር።
በኃላም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ " በህዝባችን ላይ የተፈፀመው ጄኖሳይድ አሁንም በርካታ በወራሪዎች ስር ያሉ የትግራይ አከባቢዎች ነፃ ባለመውጣታቸው ምክንያት የተሟለ መረጃ መስጠት ባይቻልም የደረሰው እልቂት ግን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ መሆን እንደሚችል ለመግለፅ እፈልጋሎህ " የሚል ማስተባበያ ለመስጠት ሞክረዋል።
የአቶ ጌታቸው ቡድን ህገ-ወጥ ሲል የሚጠራውን የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድንን " ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ሸምጥጦ በመካድ የዓለም ማህበረሰብ የተከራከረለትና የመሰከረውና የህዝብ እልቂት ወደ ጎን በመተው ዋጋ የሌለው እንዲሆን ወሰኖ ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል።
" ህገወጥ ቡድኑ ቡድናዊ የስልጣን ፍላጎቱ በፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ፣ በማሰፈራራትና ሃሳቦች በማፈን ለመጫንና ለማሳካት ላይ ታች በማለት ይገኛል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ይባስ ብሎ የመንግስት መዋቅር አንዲፈርስና ትግራይ መንግስት አልባ ሆና የረብሻና ግርግር ማእከል እንድትሆን እየሰራ ነው " ሲል አሳውቋል።
" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ማቀዱ ግልፅ ሆኗል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ጊዚያዊ አስተዳደሩና ህዝቡ ከአደገኛ አካሄዱ ሊያስቆሙት ይገባል " በማለት አክለዋል።
50 ዓመት ያስቆጠረ ድርጅት እንደ አዲስ እንዲመዘገብ በማድረግ የትግራይ ህዝብ ትግል የካደው ቡድን ህዝቡና የዳያስፓራ አባላት እንዲታገሉት ጥሪ አቅርቦ የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ለማስመለስ ፓለቲካዊ ውይይት መጀመሩን አመልክቷል።
መላው ህዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርቧል።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያልተሳተፉና ሂደቱን የተቋወሙት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነታቸው አባርሪያለሁ " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaMekelle
@tikvahethiopia

አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ።
በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ፊርማ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል።
ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች አልፈፅምም ማለትና ማደናቀፍ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።
ሁለቱ የዞን የስራ ሃላፊዎች ከመስከረም 8/2017 ዓ.ም ከነበራቸው የስራ ሃላፊነታቸው ተሰናብተው የተሰጣቸው የመንግስት ንብረትና ስራ እንዲያስረክቡ በተፃፉላቸው የስንብት ደብዳቤዎች ተገልፆላቸዋል።
አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት በቅርቡ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተመረጡት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተክተው የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪነት እንዲመሩ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾሙ ናቸው።
በተመሳሳይ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 6/2917 ዓ.ም " ከአባላትና ከድርጅታዊ ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ ደብዳቤ የፃፈላቸው የህወሓት ማእካላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ማእከላይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የአክሱም ከተማ የፀጥታ ሃላፊ ፣ የተምቤን ዓብዩ ዓዲ ከተማ ከንቲባና ሁለት የዞን የስራ ሃላፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ በማደናቀፍ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

#Tigray አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ። በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ፊርማ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል። ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ…
#Tigray
" የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል።
ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር።
ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት አመራሮች ክፍፍል እና ስለ ጸጥታ ኃይሉ ተነስቷል።
ካቢኔው " ከጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና ውጪ ፦
- መንግስታዊ የስራ ምደባ ማካሄድ ፣
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ውሳኔዎች ማፍረስ
- የመንግስት መዋቅር ለመረበሽና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
" መንግስት ለዚህ መሰል ተቀባይነት የሌለው እንቅስቃሴ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቋል።
ከህወሓት ክፍፍል ጋር በተያያዘ ካቢኔው " በአሁኑ ወቅት በህወሓት አመራሮች ዙሪያ የተፈጠረው መከፋፈል በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረ ተደርጎ መወሰዱ ልክ አይደለም " ብሏል።
" ክፍፍሉ በጥቂት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረ ነው " ያለው ካቢኔው " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከህወሓት ከሙሁራን ከፀጥታ አካላትና ከተፎካካሪ ድርጅቶች በተወጣጡ አካላት የተደራጀ መሆኑ ከግምት ውሰጥ በማስገባት ከህወሓት ክፍፍል ጋር አቆራኝቶ መግለፅ ልክ አይደለም " ሲል ገልጿል።
ካቢኔው ስለ ፀጥታ ኃይሎች ባነሳው ነጥብ " የፀጥታ አካላት ሁሉም ዓይነት ችግሮችና ፈተናዎች ተቋቁመው የህዝብ ፀጥታ ለማስከበር እያደረጉት ያለውን ጥረት አወንታዊ እና እውቅና የሚቸረው ነው " ብሏል።
" ስራዎቻቸው ከማንኛውም የፓለቲካ አስተሳሰብ ነፃ በማድረግ ገለልተኛ አቋም ይዘው እንዲሰሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ይደግፋል ያበረታታል " ሲል አመልክቷል።

#Tigray " የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ እና ለመበጥበጥ የሚደረግ የተደራጀ ሙከራና እንቅስቃሴ አንቀበልም ፥ መንግስት ለዚህ መሰል እንቅስቃሴ ህጋዊ የሆነ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ አስጠንቅቋል። ከሰሞኑን ካቢኔው ስብሰባ አድርጎ ነበር። ይህን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በዚህም የመንግስት መዋቅር ለመረበሽ ስለሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስለ ህወሓት…
#Tigray
" እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ።
በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ህዝባዊ የተባሉ ስብሰባዎች አካሂዷል።
በእነዚህ መድረኮች የፖርቲው አመራሮች ክፍፍል በስፋት ተነስቷል።
ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል።
ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮንን (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የፖርቲው አመራሮች እና የተመረጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት መድረክ ነበር።
በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል።
በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል።
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። #ዶቼቨለ

#Tigray " እኔ ድርድር ያስፈልጋል በሰላም ይፈታ ስል ፤ እሱ ግን ' ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ' ነበር ያለው " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ። በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት መቐለን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች…
#Tigray
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።
ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው " ቡድን " ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።
መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ " የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ' ቡድኑ ' የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት " ይላል።
ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ' ቡድኑ' ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።
ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።
" ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል " በማለት አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው " ብሏል።
ምንም እንኳን " ኢ-ህገመንግስታዊ " ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።
የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን " ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል " ሲል አሳስቧል።

° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው ነበር።
አቶ ጌታቸውም ንግግር አድርገዋል።
" በፓለቲካዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ትርጉም የሌለው ልዩነት ወደ ጎን በመተው የህዝቡ ሰላም ማስጠበቅ ከስጋት ተላቅቆ ኦፎይታ እንዲያገኝ መስራት ይገባል " ብለዋል።
አቶ ጌታቸው " እንደ አመራር እርባና የሌለው ልዩነታችንን ወደ ጎን በማለት ለህዝባችን ሰላምና እፎይታን እንስጠው ፤ አንድነታችንን አጠናክረን ብቁ አመራር በመስጠት ወጣቶቻችንን ከህገወጥ ስደት እንታደግ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
" ከቡድናዊነት በመውጣት የጋራ ፍላጎት በማስቀደም ለህዝብና አገር መስራት አለብን " ብለዋል።
" መስቀላችን አንድነታችን የምናጠናክርበት ፣ ሰላማችን ጠብቀን በመከራ ላይ የሚገኘው ተፈናቃይ ህዝባችን ወደ ቄየው የምንመልስበት ፤ የትግራይ ግዛት ሙሉ በሙሉ ተረጋግጦ ወደ እድገት የምናማትርበት ጊዜ ይሁንልን " ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፥ የመስቀል በዓልና ደመራን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት የህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለመላ ህዝቡ ፣ ለዳይስፖራው እና ለጸጥታ ኃይሎች እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኃላ" " የተጠናከረ ፓለቲካዊ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይገባል " በማለት አሳስበዋል።
በዓሉ መስከረም 17/2017 ዓ.ም በዓዲግራት መከበር የሚቀጥል ሲሆን የሃይማኖት መሪዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መምእምናን በተገኙበት እንደሚከበር ዓዲግራት የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
ፎቶ/ቪድዮ፦ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በመቐለ ጮምዓ

#Tigray ° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ ° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው…
#Tigray
" ስም በማጥፋት የሚፈታ የትግራይ ችግር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች ጋር በመቐለ የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ተወያይተዋል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎቹ በአግባቡ እንዳይወጣና እንዳይፈፅም ከቅርብና ከሩቅ የሚያጋጥሙት መሰናክሎች በመመከት በትኩረት ይሰራል "
ብለዋል።
" ስም በማጥፋት የሚፈታ የትግራይ ችግር የለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ የምንሰራዎች የጋራ ስራዎች በአንድነት መፈፀም አለባቸው " ሲሉ አክለዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ዛሬ ከደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች በመቐለ የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ያካሄዱት ህዝባዊ ውይይት የነበረው መልክ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታዝቧል።
" በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት " ተብሎ ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ዛሬ በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው መሪነት በመቐለ የተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ከባድ ድባብ ነበረው።
ውይይቱ መስከረም 13/2017 ዓ.ም ሊካሄድ ታቅዶ ይፋ ባልሆነ ምክንያት ወደ መስከረም 19 / 2017 ዓ.ም የተሸጋገረ ነድ።
ዛሬ በህዝባዊ ውይይቱ ለመሳተፈ በመቐለ ዙሪያ ከሚገኙ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወረዳዎች ዶግዓ ተምቤን ፣ እንደርታ ፣ ሕንጣሎ ወጀራት ፣ ሳምረ ሳሓርቲ የተውጣጡ የህዝብ ተወካዮች በአራት አቅጣጫ ወደ መቐለ ሲገቡ በከተማዋ መግብያ የፓሊስ ፍተሻ ገጥሟቸው ነበር።
በተያያዘ ህወሓት ለዓመታት በብቸኝነት ለፓለቲካዊ ስብሰባዎቹ ሲጠቀምበት የነበረውን የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ለመግባት የተሰበሰበው ህዝብ የአዳራሹ ቁልፍ በሰአቱ ባለመከፈቱ ከአዳራሹ ውጭ ፀሐይ ላይ እንዲቆይ ተገዷል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከተምቤን ፣ ዓዲግራት ፣ ማይጨውና ፣ መኾኒ ቀጥለው በእንዳስላሰ ሽረ ሊያካሂዱት ያቀዱት ህዝባዊ ውይይት በአዳራሽ ውስጥ በተፈጠረ አለመደማመጥና ግርግር ተቋርጦ ነበር።
ዛሬ በመቐለ ከደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች ያካሄዱት ውይይት " ተጨማሪ ድጋፍ ያስገኝላቸዋል ፤ የሚታየው ህዝባዊ መነቃቃት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና የመሰብሰብ ዴሞክራሲ መብቶች ያጎለብታል " የሚሉ ብዙሃን አስተያየት ሰጪዎች ጎን ለጎን " ፕሬዜዳንቱ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ሳይሰሩ በህዝብ ደጋፍ እየሰከሩ ነው " የሚሉ አልታጡም።
በመቐለ ዙሪያ የሚገኘው የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዶ/ር ደብረፅዮን በሚመሩት ህወሓት የፓሊት ቢሮ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ አቶ ፀጋይ ገብረተኽለ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖው እንዲሰሩ በጊዚያዊ አስተዳደሩ በቅርቡ መሾማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መሪነት ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች በተከናወነው ህዝባዊ ውይይት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

Photo
#Tigray
በምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " አስቸኳይ " ያለውን ሰብሰባ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
ዛሬ መሰከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመቐለ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት አዳራሽ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን ህወሓት በይፋ የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ ካድሬዎች ተገኝተዋል።
አቶ ጌታቸው በሰብሰባው መክፈቻ " ፓለቲካዊና ሰላማዊ ትግል በማጠንከር በብቃት በመምራት ወደፊት የሚያራምድ አመራር መፍጠር ልዩ ትኩረት ያሻዋል " ብለዋል።
ህወሓት ያጋጠመው ችግርና መፍትሄዎቹ አልሞ መካሄድ በጀመረው ስብሰባ በድርጅቱ ወስጥ የተፈጠረው ችግር ተገንዝቦ ውስብስቡን በማቅለል ተገቢ የፓለቲካ መፍትሄና አቅጣጫ የሚሰጥ አመራር የሚያስፈልግበት ወቅት አሁን ነው ተብሏል።
" የፕሪቶሪ ስምምነት ህዝብን ከተጨማሪ እልቂት የታደገ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " ስምምነቱ ያሰገኘው ሰላም ማስቀጠል ቁልፍ ጉዳይ ነው " ብለዋል።
" በምክትል ሊቀመንበር የተመራው ማእከላይ ኮሚቴና የከፍተኛ ካድሬዎች ስበሰባ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል " ሲል ድምፂ ወያነ ጠቅሶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#Afar #Tigray
የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ።
ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል።
የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ይፋዊ ግንኙነት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የሻከረው ግንኙነት ለማደስ ያለመ እንደሆነ ድምጺ ወያነ ዘግቧል።

#Afar #Tigray የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ። ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው። በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል። የሁለቱ…
#Afar #Tigray
ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ።
በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል።
ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል አጎራባች ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጸጋይ ገብረተኽለ ፥ " ውይይቱ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ጉርብትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ነው " ብሎውታል።
" በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ፣ ነፃ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እና የቆየው የሰላም እና የልማት ግንኙነት እንዲቀጥል በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።
" ሁለቱ ክልሎች በሚያዋስኑ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ " የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው " ግጭት ጠማቂዎችና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ ፣ የጋራ የሰላም እና የፀጥታ እቅድ እንዲኖርና በየወሩ እየተገመገመ እንዲመራ ትግራይ እና ዓፋር ተስማምተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል የነበረው የአንድ ቀን ቆይታ አጠናቅቆ ወደ መቐለ መመለሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Afar #Tigray ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ። በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል። ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል…
#Afar #Tigray
" የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ
የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ?
" የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።
በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ነው።
የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ መረጋጋትን ለመፍጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል።
ለክልሉ ሰላምና መረጋገት የድርሻችንን እንወጣለን " ብለዋል።

#TPLF " ህጋዊ እና ትክክለኛ 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን " - በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ " በሚል መሪ ቃል ሰብሰባ የተቀመጠው በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ሰብሰባውን ቀጥሏል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ከፍተኛ ካድሬዎች " ህዝብ እና ህወሓት በማዳን የትግራይ…
#Tigray
" የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ።
በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፥ " የህወሓት ህጋዊነት ለመመለስ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል " ገልጿል።
" ውይይቱን የሚያስቀጥል የትግራይ የሰላም ልኡክ አንደ አዲስ እንዲደራጅና በሰው ሃይል እንዲጠናከር ይደረጋል " ብሏል።
" ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የሪፎርም እቅድ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል " ሲልም ገልጿል።
አቶ ጌታቸው የሚመሩት ህወሓት " ድርጅቱን በማጠናከር የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንሰራለን " ብሏል።
በትግራይ የሚታየው ቀላል የማይባል የህግ ጥሰት ስርዓት ለማስያዝና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በመግለፅም የፀጥታ መዋቅርና የህዝብ ድጋፍ ጠይቋል።
በአቶ ጌታቸው የሚማራው ህወሓት " ከጎረቤቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ለማሻሻል ሰላማዊ ዝምድና ለማጠናከር ከሁሉም ጎረቤቶች በጋራ እንሰራለን " ብሏል።
ቡድኑ ባካሄዘው የ3 ቀን ውይይት በሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከሰባቱ የትግራይ ዞኖች የተወጣጡ ከፍተኛ ካድሬዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

ኮሚሽነር ግርማይ ማንጁስ !
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ህይወታቸው እስካላፈበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ኮሚሽነር ግርማይ ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቢቆዩም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ከነሐሴ 01 ቀን 1994 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ከዋና መምሪያ እስከ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ኃላፊነት ሠርተዋል።
እስከ ህልፈታቸው ጊዜ ድረስም የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ነበር።
ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።
ዛሬ አስክሬናቸው በልዩ ወታደራዊ አጀብ እና ሃይማኖታዊ ስነርዓት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ተሸኝቷል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ እሁድ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመቐለ ጽርሃ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
#FederalPolice #Tigray #CommissionerGirmayKebede

" ለሚፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ስርዓት አልበኝነት ለመቆጣጠር " የጥፋት ሃይል " ሲል በስም ባልገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
" ህግና ስርዓት ለማስክበር የተጀመሩ ጥረቶች በማጠናክር የህዝቡ ስጋት ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ " ብሏል ጊዚያዊ አስተዳደሩ።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 27/2017 ዓ.ም ያወጣውን የመንግስታዊ ስልጣን ሹም ሽር የነቀፈው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፤ " ቡድኑ ወደ ስርዓት አልበኝነት ለመሸጋገር የሚያስችለው ግልፅ መንግስታዊ ግልበጣ ማካሄዱን አውጇል " ሲል ከሰዋል።
" ቡድኑ የመንግስት ስልጣን እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚያዝ ተደብቆት ሳይሆን ከዛሬ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርዓት አልበኝነት ለማስፈን ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ለማሳካት ሆን ብሎ ያደረገው ነው " ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ።
" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህንን ስርዓት አልበኝነት በትእግስት አያልፈውም " ብሎ " የጥፋት ሃይል " ሲል በገለፀው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ብሏል።
" በሂደቱ ለሚፈጠር ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂ ቡድኑና አመራሩ መሆናቸውን ለህዝባችን መግለፅ እንወዳለን " ሲል አስጠንቅቋል።
በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራ ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው በጉባኤ ያልተሳተፉ 13 የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች በጉባኤ በተሳተፉ 14 አመራሮች ለመተካት " ወሰኛለሁ " የሚል መግለጫ ዛሬ መስከረም 27/2917 ዓ.ም ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#DDR #Tigray
የእንግሊዝ (UK) መንግስት የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም (DDR) የሚያግዝ የ16 ነጥብ 9 ሚሊዮን ፓወንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡
የድጋፍ ማእቀፉን ያሳወቁት በብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሎርድ ኮሊንስ የተመራው ልዑክ በመቐለ በመገኘት የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ አባል ሌ/ጀ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ እና ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንዲሁም የዩኤንዲፒ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የቀድሞ ተዋጊዎች ዲሞቢላይዜሽን ማእከል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
#UKinEthiopia

" ጠቅላይ ሚንስትሩ ያስቀመጡት የመፍትሄ አቅጣጫ ተግባራዊ አልሆነም " - የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች
የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ ግብረ ሃይል ተወካዮች ከሰሞኑን ውይይት ተቀምጠው ነበር።
በዚህም ወቅት ፤ " ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በትግራይ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተከማች የብድር ወለድና ቅጣት መልክ እንዲይዝ ባለፈው ዓመት የሰየሙት የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን እስካሁን ያስቀመጠው ተጨባጭ ነገር የለም " ብለዋል።
" ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት የአመራር አቅጣጫ የገንዘብ ሚንስቴር ፣ የብሄራዊ ባንክና ልሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሃላፊዎች ያካተተ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ቢቋቋምም እስከ አሁን የሚዳሰሰ የሚጨበጥ ለውጥ አልመጣም " ሲሉ ገልጸዋል።
ተወካዮቹ ፥ " ከ7 ወራት በፊት በ2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አዲስ አበባ ከጋበዟቸው የንግድ ማህበረሰብ ያካተተ ልኡክ ጋር ባካሄዱት ውይይት ማጠቃለያ በጦርነቱ ጊዜ የተከማቸው የብድር ወለድና ቅጣት ተሰልቶ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መፍትሄ እንዲሰጠው አቅጣጫ ቢያስቀምጡም እስከ አሁን ጠብ የሚል መፍትሄ አለመጣም ይህም በጣም አሳዝኖናል " ብለዋል።
አበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የሰጡት የብድር ወለድ ከነቅጣቱ እንዲመለስ የንግድ ማህበረሰቡ ማስጨነቅ እንደጀመሩ በዚሁ ውይይት ወቅት ተነግሯል።
ተግባሩ በጦርነት ምክንያት የደቀቀው የክልሉ ኢኮኖሚያዊ አቅም ይበልጥ ጉልበት የሚያሳጣ መሆኑ በመገንዘብ አገራዊ የፓሊሲና የፓለቲካ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል።
ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አይደለምና " አስቸኳይ ትኩረት እና መፍትሄ " እንደሚያሻው አፅንኦት ተሰጥቷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የፌደራል መንግስት የትግራይ የንግድ ማህበረሰብ የሚታደግ የመፍትሄ እርምጃ እንዲያስቀመጥ ተጠይቋል።
#TikvahEthiopiaMekelleFamily

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ
የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።
እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።
ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።
" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።
" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል።
" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።
ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።
የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።

#መቐለ " የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከስራ አገዱ። ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለዶ/ር ረዳኢ በርሀ " በማለት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ህጋዊ ያልሆነ…
#Tigray
" እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል አሳስቧል።
መመሪያ ደ/18/8/84 እንደሚለው " በህወሓት አመራሮች የተፈጠረ የፓለቲካ ልዩነት ምክንያት በማድረግ መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።
በመሆኑም ፦
1. ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ፤ ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ፤
2. በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ፤
... ሲል ማስጠንቀቅያ ሰጥቷል።
ከዚህ ባለፈ የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች የሚፃረር የከተማና የገጠር ወረዳ የአስተዳደር መዋቅር በጀት እስከመገደብ የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት በአፅንኦት አሳስቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMeklle

#ትግራይ
" ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል አሁንም ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።
በተለይም ከነሀሴ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና በግልፅ የታየው ልዪነት መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄያዎች በተቀናጀ መልኩ እንዳይፈቱ ከባድ እንቅፋት ፈጥረዋል ብሏል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች በተቀናጀ መልኩ የሚያደናቅፈው ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ከፍተኛ አመራር ነው ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ " ደርጊቱ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ሲል አውግዞታል።
" የቡድኑ ተግባር የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ከማደናቀፍ በዘለለ ይፋዊ ወደ ሆነ የመንግስት ግልበጣ እና ስርዓት አልበኝነት ማስስፋፋት ከፍ ብሏል " ሲል ከሷል።
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በመቐለ ከተማ ፣ በሰሜናዊ እና ማእከላዊ ዞኖች የታዩት የመንግስት ግልበጣና ስርዓት አልበኝነት ምልክቶች የቡድኑ ህግ አልበኝነት ማሳያ ናቸው ሲል አስረድቷል።
" ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የመንግስት የአመራር እርከን ከላይ እስከ ታች ለመቆጣጠር ጨርሰናል " የሚል የማደናገሪያ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
" የቡድኑ ማደናገሪያ በአጉል ተስፋ ራስን ከማታለል የዘለለ ቅንጣት ሀቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት " ያለው አስተዳደሩ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ መጥቷል " ሲል ገልጿል።
" ' ከሰራዊት አመራሮች ተግባብተናል ' በሚል እየነዛው ያለው ማደናገሪያ ለጠባብ የስልጣን ፍላጎቱ ማሟያ ነው " ብሏል።
" በትግራይ ህልውና የቆመው ሃይል ከመጠቀም እንደማይመለስም ማሳያ ነው " ሲል አክሏል።
" ቡድን " ሲል የገለፀው አካል በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው ነገሮች በውይይት የመፍታት ሂደት እንደማይቀበል በአደባባይ ገልፀዋልም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮቼ አሁንም ነገሮች በሰከነ አኳሃን በሰላም እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ናቸው ብሏል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች የጀመሩት የሰላምና የውይይት ጥረት እንዲሳካ ሁሉም ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።
በቅርቡ የትግራይ ሃይማኖት አባቶች የህወሓት አመራሮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ እና አመራሮቻቸውን በአካል አገናኝተው ነበር።
ከዚህ መድረክ በኃላ በወጡ የተለያዩ ፎቶዎች በርካቶች " ችግሩ በንግግር ሊፈታ ነው " በሚል ብዙ ተስፋ አድርገው ነበር።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።
አንዳንድ ሚዲያዎች ደግሞ " ለእርቅና ሽምግልና ተስማምተዋል " የሚል መረጃ እስከማሰራጨትም ደርሰው ነበር።
በኃላ በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ሲል አሳውዋል።
" ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለንን ክብርና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ነበር የገለጸው።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ።
#TikvahEthiopiaFamilyAA #Tigray #Mekelle

#ትግራይ " ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው። " ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል…
#Tigray
🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ
🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት
🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ባለፈው እሁድ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከስራ ባለደርቦቻቸው ጋር ከአክሱም ወደ መቐለ ሰጓዙ የግድያ ሙከራ እንደ ተቃጣባቸውና ከግድያ ሙከራው እንደተረፉ ተናግረዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው ገልጸዋል።
ለጊዜው እነማን እንደተኮሱባቸው ማንነታቸውን / የታጣቂዎችን ማንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸው በተተኮሰባቸው ጥይቶች መኪናቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።
በጥይት የተመታው መኪናቸውን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አድርገዋል።
በመኪናው ውስጥ ከእሳቸው በተጨማሪ ጥበቃቸው እና የመኪናው ሹፌር ነበሩ።
ዋና አስተዳዳሪው የደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት እንደሌለ አረጋግጠዋል።
እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የመግደል ሙከራ መደረጉ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኃላ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ማይቅነጣል ወረዳ ስልክ ቢደውልም ጉዳዩ የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር።
የዞኑ መቀመጫ ወደሆነችው አክሱም የሚገኝ ፓሊስ ማዘዣ ስልክ ቢደወልም የተጣራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
ይህ በእንዲህ እያለ የመግደል መከራ ተቃጥቶበታል የተባለው ቦታ የሚያስተዳድረው የማይ ቅነጣል ወረዳ " ጉዳዩ አልተፈፀመም " የሚል መግለጫ አውጥቷል።
የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ " በአከባቢው አለ ጉዳዩ ፈፅሞታል " ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተደጋግሞ የተጠቀሰው የትግራይ ሰራዊት አርሚ 60 አዛዥ ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ እሳቸው የሚያዙት በፀሃፊዎቹ የተገለፀው ሰራዊት በአከባቢው እንደሌለ በመግለፅ " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " ሲሉ ተጠምደዋል።
ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዚያት መሰል የግደያ ሙከራዎች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማመንት በየነ መኩሩ ፣ ነጋ ኣሰፋ ፣ ሰሎሙን ትኩእ እንዲሁም በአክሱም ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር መደረጋቸው የተነገረ ቢሆንም እስካሁን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጣርተው የተወሰደ እርምጃ የለም።
#VOATigrigna #TikvahEthiopiaFamilyMekelle