#update በትናንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት በአቢዬ ጊዜያዊ የደኅንነት ሀይል ግቢ ውስጥ በሂሊኮፍተር አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ መሸኘቱ ተገለጸ፡፡ የሱዳንና በደቡብ ሱዳን ተወካዮች ለተጎጂ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ሂሊኮፍተሯ ትናንት የተከሰከሰችው 23 የሠላም አስከባሪ አባላትን አሳፍራ በአካባቢው ቅኝት እያደረገች ሳለ መሆኑና ምክንያቱ እስካሁን አለመታወቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል። በአደጋው የአራት ሰላም አስከባሪዎች ህይዎት አልፏል አስሩ ደግሞ ተጎድተዋል። ተጎጂዎች ለሰለም አስከባሪዎች አገልግሎት ወደ ሚሰጠው ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ዘገባው አስታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ የሠላም አስከባሪ አባላት MI-8 በተባለች ሄሊኮፕተር ካዱግሊ ከተባለ ሥፍራ ወደ አብየ ግዛት ለመደበኛ ቅኝት ተሰማርተው እያሉ ነው አደጋው እንደደረሰ የተዘገበው። አደጋው የደረሰው በተባበሩት መንግሥታት የአብየ ግዛት ሰላም አስከባሪ ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ነው። በአብየ ግዛት የተመድ ሰላም ማስከበር የተልዕኮና ግዳጅ ተጠባባቂ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገብረ አድሃና ወልደእዝጉ የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
ምንጭ - ተመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ - ተመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ስነተዋልዶ ጤና ክሊኒክን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀላባ ከተማ‼️
በደቡብ ክልል ሀላባ ከተማ ትናንት በተሰራጨ #ሀሰተኛ_ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች በከተማው በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ላይ #ጉዳት ማድረሳቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ እንዳሉት በከተማው #የማቃጠልና የንብረት #ማውደም ድርጊቱ የተፈጸመው ሌንዳ በር እና ዋጃ በር በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ላይ ነው፡፡ በስፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የከተማው አዛውንት ጥቃቱ የተጀመረው በድራሜ ከተማ መስኪድ መቃጠሉንና ኢማም መገደሉን የሚገልጹ ወሬዎች ከተናፈሱ በኋላ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በቤተክርስቲያናቱ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ መመልከታቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል፡፡
የጀርመን ድምፅ ራድዮ በሥልክ ያነጋገራቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ #ዓለሙ_ሌንቢሶ ደግሞ በከተማው በተሳሳተ ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን በሌሎች ሰባት ቤተክርስቲያናት ላይ ደግሞ ንብረቶችን የማውደም ድርጊት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እጅ ከፍንጅ የተያዙ 20 ግለሰቦችን ጨምሮ 63 ተጠረጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ሃላፊው የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽነርም ጥቃቱን ለመከላከል ጥረት ባለማድረጋቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምንጫቸው ባልተረጋገጡ ወሬዎች በመነሳሳት የሚፈጸሙ የደቦ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ በቅርቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቀደም ባሉት ጊዚያት ደቦ እርሻን በህብረት ለመሥራት ይውል እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ጸብም በደቦ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

#update የሀላባ ዞኑ ፖሊስ ኮሚሽነር ጥቃቱን ለመከላከል ጥረት ባለማድረጋቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ሞሚና መሀመድ‼️
ለ102 ህሙማን የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማከናወኑን በጤና ሚኒስቴር ብሄራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ማእከል አስታወቀ።
የማእከሉ መስራችና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር #ሞሚና_መሀመድ እንዳሉት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መጨመር ለኩላሊት መድከም መንስኤ እየሆነ በመምጣቱና ተገቢውን ህክምና አለመከታታል ጫና በማሳደሩ ከሶስት አመት በፊት ለማእከሉ መመስረት ምክንያት ሆኗል፡፡
ከብዙ ታዳጊ ሃገራት አኳያ ሲታይ በተጠቀሰው ጊዜ ለ102 ሰዎች ንቅለ ተከላ ማካሄድ “በጣም ከፍተኛ ስኬት ነው” ማለት ይቻላል ያሉት ዶክተር ሞሚና ያለማቋረጥ በየወሩ ከ4-5 ሰዎች ንቅለ ተከላውን እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ታካሚዎችና የኩላሊት ለጋሾች በበኩላቸው የኩላሊት ህክምና አገልግሎት ሊስፋፋና አሰራሩም ላይ ማሻሻያ ሊደረግለት አንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሆስፒታሉን ህክምና የመስጠት አቅም ለመገንባት ከላብራቶሪ፣ከራጅ ምርመራ፣ ከፓቶሎጂ አኳያ ለንቅለ ተከላውን ታስበው የተሰሩ ስራዎች ባጠቃላይ የሆስፒታሉን አቅም ገንብተውታል ብለዋል፡፡
የንቅላ ተከላው ህክምና ቀጣይነቱም ታስቦበት እንደተገባ ገልፀው ከሰው ሃይል ግንባታ አኳያ ትኩረት ተሰጥቷል፤ ስራው ሲጀመር በአንድየኩላሊት ስፔሻሊስት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ስድስት መድረሳቸውንና በመማርም ላይ ያሉ መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡
“የኩላሊት ቀዶ ህክምና ባለሙያም አልነበረንም፣ ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ጋር ሆነን እንሰራ ነበር”ያሉት ዶክተሯ አሁን ላይ አራት የንቅለ ተከላ ሃኪሞች መኖራቸውንና ከነርሶችና ደጋፊ ባለሙያዎችም ዙሪያ አቅም የመገንባት ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡
ማእከሉ የግብዓትና የቦታ ጥበት ችግር ቢፈታለት አሁን ከሚሰራው በተሻለ መልኩ አገልግሎቱን መስጠት ያስችለው ነበር ያሉት ዳይሬክተሯ እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

መከላከያ~ማስጠንቀቂያ ሰጠ‼️
ወታደራዊ መለዮ እየለበሱ ዝርፊያ እና ውንብድና በሚፈጽሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ 33ኛ አባይ ክፍለ ጦር አስጠነቀቀ።
ክፍለ ጦሩ በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስተካከል ከሕዝቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የ33ኛ አባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #ዓለሙ_አየነ ሠላምን ለማስፈን በሁለቱም ዞኖች ከ37 ሺህ በላይ ሠዎችን ማወያየታቸውን ተናግረዋል። እርቅና መግባባት ላይም ተደርሷል ነው ያሉት።
በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ታውቋል።
እስካሁንም በቡድንና በግል ሆነው በቤት ዝርፊያ እና በሌሎች የውንብድና ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሰላምን ሲያሳጡ የነበሩ 76 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጀነራል ዓለሙ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ አብመድ

#VisitEthiopia🔝 #BlueNileRiver #HarennaFores #SofOmerCave #Dallol #Ethiopia #LandofOrigins
Via MysticalEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via MysticalEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝
"በጎንደር ዩኒቨርስቲ የምንገኝ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ተማሪዎች በዛሬው እለት #ካለን_ብናካፍል በሚባል የአረጋውያን እና የአይምሮ መርጃ የበጎ አድራጎት ማህበር 10 ደርዘን ሳሙና፣ ምላጭ እንዲሁም ልብስ እና ጫማ ይዘን በመሄድ አረጋውያንን እና የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ገላቸውን ስናጥብ ፀጉራቸውን በማስተካከል ሴቶቹን ደግሞ ፀጉራቸውን በመስራት የተቀደሰ ምግባር ሰርተናል። ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።"