TIKVAH-ETHIOPIA
1.42M subscribers
55.2K photos
1.38K videos
199 files
3.7K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (No.7) • “ እኔ 50 ሺህ፣ ጓደኛዬ 30ዐ ሺህ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃዩ ነው ” - ከእገታ የተለቀቀ ተማሪ • “ እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል ” - የታጋች ተማሪ ወንድም ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ 10 ቀናት አስቆጥረዋል። ስለታጋቾቹ ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ? ቲክቫህ…
#Update (No.8)

" ባነር አሰርተን ልመና ወጥተናል ገንዘብ ግን እየተገኘ አይደለም " - የታጋች ተማሪ ቤተሰብ

ትምህርት አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ ገብረ ጉራቻ ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸው አይዘነጋም።

ተማሪዎቹ የታገቱት ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ብዛታቸው በትክክል ባይታወቅም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከእገታው ያመለጡ ተማሪዎች በሁለት ታታ አውቶብስ የነበሩ መሆናቸውን በወቅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ከታጋቾቹ መካከል አንዳንዶቹ ከፍተኛ ብር ከፍለው መለቀቃቸውን መግለጻቸውም ይታወሳል።

የታጋቾቹ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የታጋቾቹ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የታጋች ቤተሰቦቸ፣ ልጆቻቸው ባለመለቀቃቸው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ቃሏን ለቲክቫህ የሰጠች አንድ የታጋች እህት አጋቾቹ የጠየቁትን ግማሽ ሚሊዮን ብር ካልተላከላቸው ታጋቾቹን ‘ አንለቅም ’ ማለታቸውን ገልጻ፣ “ ባነር አሰርተን ልመና ወጥተናል ገንዘብ ግን እየተገኘ አይደለም ” ብላለች።

በተጨማሪም እህቷ ፤ ያሉት ታጋች ተማሪዎች ምግብ በወቅቱ እንደማያገኙና ልብስም ስለሌላቸው በብርድ እየተሰቃዩ እንደሆነ እንደገለጸችላት ተናግራለች።

" አጋቾቹ 700 ሺህ ጠይቀውናል " ያለ ሌላኛው የአንዲት ታጋች ተማሪ ወንድም፣ ታጋቿ በስቃይ ውስጥ እንዳለች ቤተሰብ ገንዘቡን ለመላክ አቅም እንዳላገኘ ገልጿል።

" ቤተሰቡ በከባድ ሀዘን ላይ ነው። በተወለድንበት ሀገር ለዛውም ንጹሐን ተማሪ ታግተው ሲሰቃዩ መንግስት ምን እየሰራ ነው ? " ሲል ጠይቋል።

ታጋቾቹን ለማስቀቅ ምን እየሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ የጠየቀው የኦሮሚያ ክልል ስላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከዚህ ቀደም የሰጠው መግለጫ እንዳለ ከመጥቀስ ውጪ በጸጥታ ቢሮው በኩል ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማትም ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠተ ፈቃደኛ አልሆኑም።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ፣ በ 'ሸኔ ቡድን ታግተው ተወሰዱ' ካላቸው 167 ታጋቾች መካከል የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ ተለቀው፣ 7 ታጋቾች ብቻ እንደቀሩ አሳውቆ ነበር።

አንድ ከቀናት በፊት ገንዘብ ከፍሎ ከእገታ የተለቀቀ ተማሪ ግን እርሱ ከነበረበት የእገታ ቦታ ብቻ ከ60 በላይ ታጋቾች እንዳሉ ለቲክቫህ ተናግሮ ነበር።

ሌላኛዋ በእገታው ላይ ያለች ተማሪ ባለችበት ጫካ ፣ በርካታ ታጋች ተማሪዎች እንዳሉ እንደተናገረች ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OnlineScam ባለፈው ወር ላይ የላኦ እና የቻይና ፖሊስ በሰሜን ላኦስ ጎልደን ትሪያንግል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በህገወጥ የጥሪ ማእከል የኦንላይን ማጭበርበር (Online Scam) ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያሏቸውን 280 ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ግለሰቦቹም ወደ ቻይና ዲፖርት ተደርገዋል። ፖሊስ ግለሰቦቹን በያዘበት ወቅት 460 ኮምፒዩተሮች እና 1,345 ስልኮችን ይዟል። እንዚህ አካላት…
#Update

ሕንድ በማይናማር እንዲሁም ካምቦዲያ በሳይበር ወንጀል / የኦንላይን የማጭበርበሪያ ማዕከላት (Online Scam Centers) ውስጥ ያሉ ዜጎቿን አስወጣች።

ሀገሪቱ በማይንማር፣ ማያዋዲ ' ሽዌ ኮ ኮ '  በሚገኝ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ 11 ተጎጂ ዜጎቿን እንዳስወጣች ገልጻለች።

ሕንዳዊያኑ ከማዕከሉ እንዲወጡ የተደረገው በማይናማር ባለስልጣናት እና በአካባቢው ወጣቶችን ከቦታው እንዲወጡ በሚረዱ ሰዎች ርብርብ ነው።

አሁን ላይ እነዚህ ሕንዳዊያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሕንድ እንዲመለሱ እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ የሕንድ መንግሥት ከካምቦዲያ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር በሳይበር ወንጀል / ኦንላይን ማጭበርበር ማዕከላት ውስጥ እንዲሰሩ ሲደረጉ የነበሩ 14 የሕንድ ዜጎችን አስወጥቷል።

በፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ስለመሆኑም ሰምተናል።

ሕንድ በርካታ ወጣቶቿ በማጭበርበሪያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙባት ሀገር ስትሆን ከዚህ ቀደም መሰል ዜጎቿን የማስወጣት እርምጃ የወሰደች ሲሆን አሁንም ቀጥላለች።

ሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ ተጠቂ ናቸው ያሏቸው ዜጎቻቸውን የማስወጣት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።

በማይናማር፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ ፣ ቻይና ታይላንድ ድንበር፣ ታይላንድ ማይናማር ድንበር ባሉ የማጭበርበሪያ ማዕከላት እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ የሌሎች ሀገር ዜጎች ይገኛሉ።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች አሉ (ከተለያዩ ሀገራት)።

በስፍራው የሚገኙት ብዙሃኑ ወጣቶች ናቸው።

ወደዚህ ተግባር የገቡት እራሳቸው ተጭበርበረው ነው / ይህ ማለት እራሳቸውም ተጎጂዎች (ሰለባ) ናቸው።

ደላሎችና ኤጀንሲዎች ወጣቶች 'ወደ ታይላንድ / ወደ ሌላ ሀገር' ለ፦
- ሴልስ
- የማርኬቲንግ
- ለሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- ለተቋማት ደንበኞችን ማነጋገር በሚል ነው የሚልኳቸው።

በኃላም ወደ ጎረቤት ሀገራት በመውሰድ የተደረጀ የኦንላይ ማጭበርበር ስራ ላይ እንዲሰማሩ ነው የሚደረገው።

ወጣቶቹ ከሚሰማሩባቸው ተግባራት ዋነኛው ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት በመክፈት ሰዎችን በተለይ ሴትን በወንድ / ወንድ በሴት አስመስለው በማነጋገር ገንዘብ ማጭበርበር ነው።

የታዘዙትን አድርገው ገንዘብ ካላመጡም የከፋ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል።

ወጣቶችን እንዲያጭበረብሩ የሚያሰሩ ማፊያዎቹ በቀጠናው እጃቸው ረጅም የሆነ ሰዎች ናቸው።

እጃቸው በረዘመ ማፊያዎች በሚመራው የሳይበር ወንጀል / የኦንላይን ማጭበርበር / ተግባር በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ይዘረፋል።

ስለ ማጭበርበሪያ ስልቶቹ / ሰዎችን በምን መንገድ እንደሚያጭበረብሩ በዚህ ያንብቡ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88986

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሚዲያ ዘመቻችሁን እንድታቆሙ እንጠይቃለን " - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፥ " በሕገ-ወጥ መንገድ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይለማ የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ለልማት እንዲውል ማድረግ ሕገ- መንግስትን ማስከበር እና ማክበር እንጂ የሚያስወቅስ ጉዳይ አይደለም " አለ። ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ነው። አስተዳደሩ ፥ " ሕግ እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር የአንድ…
#Update

“ ሁለቱንም አካላት ፊት ለፊት ለማገናኘት የጋራ መድረክ ይዘናል ” - የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር “በጉልበት ሊወስደው ነው” ስትል በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረቧ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ የጠየቀው የከተማ አሰተዳደሩ በበኩሉ፣ “ መሬቱ በNGO እጅ የነበረ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ይህንኑ የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ የተመለከተችው ቤተክርስቲያኗ፣ “ መሬቱ በጭራሽ በNGO እጅ ገብቶ አያውቅም ከመጀመሪያው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ እጅ የነበረ ነው ” የሚል አጸፋ መሰጠቷ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ስለጉዳዩ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሁለቱም አካላት በጋራ ተወያይተው ችግራቸውን እንዲፈቱ በተናጠል እንዳነጋገራቸው ገልጿል።

የጉባዔው ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ሁለቱንም አካላት ፊት ለፊት ለማገናኘት የጋራ መድረክ ይዘናል ” ብለዋል።

“ ህዝቡ ወዴት ይሄዳል ? ሰው ሲያኮርፍ ወዴት ያመራል ? የሚሉ ጉዳዮች ይኖሬሉ ” ያሉት ዋና ፀሐፊው፣ “ ስለዚህ ይህንን ቁጭ ብሎ Manage ማድረግ ያስፈልጋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሁለቱም አካላት በጋራ ለመነጋገር ፈቃደኞች እንደሆኑ ነገር ግን ጉዳዩ ገና በሂደት ላይ እንደሆነ፣ ወደ ስምምነት እንዲመጡ ለማድረግ ጉባዔው የጋራ መድረክ እንዳዘጋጀ አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩን በተናጠል እንዳወያዩ፣ ቤተ ክርስቲያኗን ለማወያዬት በሂደት ላይ እንደሆኑ የገለጹት ዋና ፀሐፊው፣ “ አንድ ሳምንት ሊፈጅብን ይችላል ጨፌ ስብሰባ ስለገቡ ዋናዎቹ። የጋራ ፕሮግራም ይዘናል እንወስናለን ” ብለዋል።

ጉባዔው ሁለቱም አካላት የቃላት ውርዋሮ አቁመው ወደ ስምምነት እንዲመጡ የማግባባት ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን…
#Update

° " የተቆራረጠ ደሞዝ አንወስድም ምክኒያቱም ካሁን በፊትም እንዲሁ ተደርገናል " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች

° " የተፈጠረው የካሽ እጥረት በመሆኑ ወደስራ ተመለሱ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች " ከግንቦት ወር ጀምሮ ደሞዝ አልተከፈለንም " በሚል ስራ አቁመው ወደ ዞኑ ጤና መምሪያ ጥያቄ ለማቅረብ ለመሄድ ሲሞክሩ በሀድያ ዞን ፖሊስ ተደብድበው ወደ ሆሳዕና ከተማ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጉዳዩን ከምን ደረሰ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላችሁ ሰራተኞቹ አሁንም ስራ እንዳቆሙ መሆኑን በመግለጽ የተፈቀደውን የአንድ ወር ደሞዝ እንዳይወስዱ በ2015 ዓ/ም በዚህ መልኩ እንደተቃጠለው ገንዘባቸው እንዳይሆን ስጋት እንደገባቸው ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ አሁን ላይ ውይይት አድርገዉ አንዳች ውሳኔ ላይ ለመድረስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ በቅርቡ አቋማቸውን እንደሚገልጹ ነግረዉናል።

የሰራተኞቹን ስራ ማቆም ተከትሎ በስራ ላይ  ችግር አልተፈጠረም ወይ ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ  አብርሀም ሎምቤ ፥ " ስራ ያላቆሙ ሰራተኞች በጫና ውስጥ ሆነው እየሰሩ ቢሆንም ስራ ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ ገበታቸው ተመልሰው ብንነጋገር የተሻለ ነው " ብለዋል።

ለምን የሰሩበትን ክፍያ አትሰጧቸውም ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ " የካሽ እጥረት ነው የተፈጠረው ፤ የካሽ እጥረት እንደሀገር የሚገጥም በመሆኑ ክፍያቸው አይቀርባቸውም " ሲሉ መልሰዋል።

በሌላ በኩል ስራቸውን ያቆሙ ሰራተኞች ወደስራ መመለሳቸውን በደብዳቤ እየገለጹ የአንድ ወር ደሞዝ ይውሰዱ ስለተባለው ጉዳይ የጠየቅናቸው አቶ አብርሀም " ዋናው ወደስራ መመለሳቸው በመሆኑ በቃልም ቢሆን ከሰው ሀብት ጋር ተነጋግረን ስራ መጀመር ይችላሉ " ብለዋል።

ሰራተኞች ግን ባለሙያ ሆስፒታል ውስጥ እንደሌለ እየታወቀ ማስታወቂያው የተነገረው ብለዋል።

" ሲጀመር የሰኔዉ ላይ ለመወያየት ቀድሞ የግንቦት የት ነዉ ያለዉ ስላልን ነዉ ይሄ ሁሉ በደል የደረሰብን። " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም የግንቦት ላባችን እንዳይበላ ሁሉም ይወቅልን " ብለዋል።

ሰራተኞቹ አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮ የሰኔ ላይ እንዲፈርሙ ከተደረጉ በኃላ የግንቦቱ ክፍያቸው ተበልቶ ሊቀር ይችላል ሚል ስጋት እንዳላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀዘናቸውን ገለጹ።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ  ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ  ዜጎቻችንን ሕይወት ቀጥፏል " ብለዋል።

" በደረሰው አስከፊ ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ " ብለዋል።

" አደጋውን ተከትሎ የፌዴራል የአደጋ መከላከል ግብረ-ሀይል በአካባቢው ተሰማርቶ የአደጋውን ጉዳት ለመቀነስ ርብርብ እያደረገ ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Tassa Tassa Tassa 😭 “ ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ቁፋሮ እየተደረገ እየተፈለገ ነው ያለው ” - ዞኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት አብዛኛዎቹ ነፍስ ለማዳን የገቡ እንዲሁም ችግሩን ለማዬት የተሰበሰቡ ሰዎች መሆናቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት…
#Update

የሟቾች ቁጥር 229 ደረሰ።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ወገኖች ቁጥር 229 ደርሷል።

ከወረዳው አስተዳዳር በተገኘ መረጃ የሟቾች ቁጥር ወንድ 148 ሴት 81 በድምሩ 229 መድረሱ ተሰምቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ትላንት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ መድረሱ ይታወሳል።

አስክሬን የማፈላለጉ ስራ አሁንም ቀጥሏል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯️ “ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን…
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ ከቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በማሆን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተው በመሬት ናዳ የተጎዱ ወገኖችን እያጽናኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ወደ ስፍራው ሊያቀኑ የነበረ ቢሆንም አጋጣሚ አየሩ ዳመናማና ለጉዞ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት እንደቀሩ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° " የከተማዉ ከንቲባ ሙሉ ደሞዛችን በሂደት እንደሚከፈለን ቃል ገብተው ወደስራ ብንመለስም ፈርማችሁ ስራ ጀምሩ መባላችን አስፈርቶናል " - ሰራተኞች

° " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተው እንደወጡ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


ከሰሞኑ " የሶስት ወር ደሞዝ ዘግይቶብናል " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ይህን ለማሳወቅም ወደዞኑ ዋና ከተማ ሲያቀኑ ፖሊስ " ሆሳዕና አትገቡም " ብሎ ከከተማው መግቢያ እንዳስመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ሰራተኞቹ ምንም እንኳን ወደዞኑ አመራሮች ቀርበው አቤቱታቸውን ባያቀርቡም ስራ አቁመው መሰንበታቸዉን ተከትሎ የሾኔ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት አወያይተዋቸው ነበር።

በውይይቱም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ማለትም የሰኔን ቅድሚያ  እንዲወስዱና ቀሪውን የግንቦት ወር ደግሞ በሂደት እንደሚያገኙ ከንቲባው ቃል ገብተውላቸው ወደስራ ቢመለሱም እስካሁን ስራ በማቋረጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ መባሉን ተከትሎ ስራውን መጀመር አለመቻላቸውንና መፈረም የሚለዉ ሀሳብ እንዳስፈራቸው ገልጸዉልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከቀናት በፊት ወደስራ ከገቡ በቃል ሪፖርት አድርገው ስራቸዉን መጀመር ይችላሉ ያሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ሎምቤ ምን ሀሳባችሁን ቀየራችሁ ? ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ " ሀሳብ መቀየር ሳይሆን የድርጅቱ አሰራር ስለሆነ ነው " ሲሉ መልሰውልናል።

" ሰራተኞቹ ፍርሀት ሊሰማቸው አይገባም " ያሉት ስራ አስኪያጁ " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተዉ እንደወጡ ሁሉ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል ይህ ደግሞ ሊያስፈራቸዉ አይገባም ብ ጉዳዩ ችግር የለውም ብለን አስረድተናቸዋል " ሲሉም ገልጸዉልናል።

አሁን ላይ የተወሰኑ ሰራተኞች ፈርመዉ ስራ ሲጀምሩ  የተወሰኑት ፊርማዉን ባለመፈረማቸው ምክኒያት ወደስራ አለመመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሰራተኞቹ ያለፈው የደከሙበት ደመወዛቸውን ተብልቶ ይቀራል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይናገሩ አላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል…
#Update

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑ 2.556 ቢሊዮን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ የ4 ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት ዛሬ አጽድቋል።

ይህ የ4 ዓመት ፓኬጅ፦
- የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን
- በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን
- የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን የሚደግፍ ነው ተብሏል።

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታት ተብሏል።

በተጨማሪ በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊዮን SDR ወይም 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም  "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል። አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን…
#Update

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።

በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል።
#DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን  ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው  ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ  ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት  ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ  ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።

የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ  በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን  መቷታል።

በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።

ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ  የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ  ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ  ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን  ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88024?single

#CentralEthiopiaRegionPolice  #WolkiteUniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው። ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም። " አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች። ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ…
#Update

" የተሰበሰበልንን 300 ሽህ ብር ከፍለን ወረፋ ብናስይዝም ገንዘቡ ሊሞላልን ባለመቻሉ ህክምናዉ ሊያልፈን ነው " -  ወላጆች

ከዚህ ቀደም በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘዉን ህጻን ህክምና በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝብ የድጋፍ ጥሪ መድረሱን ተከትሎ አንዲት ልበ ቀና እህት 200 ሺህ ብር እንዲሁም ከህዝቡ በተሰበሰበ 100 ሽህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተከፍሎ ወረፋ ተይዞለት ነበር።

ይሁንና አሁን ላይ ወረፋዉ ቢደርስም ቀሪዉ ገንዘብ መሰብሰብ ባለመቻሉ የህጻኑ ወላጆች በከባድ ጭንቀት ዉስጥ የወደቁ ሲሆን የህጻኑ ስቃይም ከጊዜዉ መሄድ ጋር ተባብሶ ቀጥሎ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።

" እባካችሁ የሆስፒታሉ ወረፋ ሳያልፈን ልጃችንም ሳያመልጠን ድረሱልን " የሚሉት የህጻኑ ወላጆች መምህርት ወ/ሮ አልሻምጌጥ ንጉሴ እና አቶ አንተነህ ደፈርሻ " አቅም ያላችሁ በገንዘባችሁ አቅም የሌላችሁ ደግሞ በጸሎት አግዙን " ብለዋል።

በልብ ክፍተት ችግር እየተሰቃዩ ያለዉንና በተያዘለት ቀጠሮ የልብ ክፍተቱ የማይስተካከል ከሆነ ለከፋ ችግር ይወድቃል የተባለዉን ህጻን ለመርዳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000243926053 አልሻምጌጥ ንጉሴ መኮንን መጠቀም እንደሚቻል መምህርቷ እናት ተናግረዋል።

በስልክ ቁጥር
0916155490 በመደወል ደግሞ አስገላጊ ማስረጃ እና ጥያቄ ቤተሰቡን መጠየቅ ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy “ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች…
#Update

" ለልማት ይፈለጋል ልቀቁ " በመባሉ የተማሪ ወላጆችን ያበሳጨው የአዲስ ግሎባል አካዳሚ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

አዲስ ግሎባል ትምህርት ቤት ያለበት ቦታ " ለልማት ይፈለጋል " በመባሉ የተማሪ ወላጆች ልጆቻችን የት እናስመዝግብ ? ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል መጠየቃቸው ይታወሳል።

ት/ቤቱ በበኩሉ፣ ባይሆን የአንድ አመት ጊዜ እንኳ እንዲሰጠው ነበር የጠየቀው።

ት/ቤቱ ምን አይነት ውሳኔ ላይ ደረሰ ?

ዛሬ ትምህርት ቤቱ አነጋግረን ነበር ፤ የትምህርት ቤቱ ዲን ት/ቤቱ በኪራይ ቤት ለማስተማር መገደዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በኪራይ በማስተማሩ ለይ ተስማምታችሁ ነው ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ የትምህርት ቤቱ ዲን ፤ " ምን እናድርግ ! በኪራይ እንድንሰራ መንግስትም ድጋፍ እንደሚያደርግልን ነግሮናል " ብለዋል።

" ልማቱ መቀጠል አለበት " ስለተባለ የመጨረሻው አማራጭ በኪራይ ቤት ተማሪዎቹን ማስተማር መሆኑን አስረድተዋል።

ስለዚህ ተማሪዎቹ አይበተኑም በኪራይ ቤቱ ለማመር ተስማምተዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ማስገደድ አንችልም። የሚፈልጉን ነባር ተማሪዎች አብረውን ይቀጥላሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ኪራይም ባይሆን በራሳቸው መንገድ የሚለቁ ይኖራሉ " ያለው ትምህርት ቤቱ፣ " ስለዚህ አዲስም የያዝናቸው አሉ። ነባር ተማሪዎችንና ወላጆቻችንን ይዘን እንቀጥላለን " ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በንግድ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሬ እንዴት ዋለ ? በባንኩ የውጭ ምንዛሬ በተለይ የዶላር ዋጋ ከትላንት ከሰዓቱ የተለየ አልነበረም። ዶላር ትላንትና ከሰዓት ሲገዛ እና ሲሸጥ በነበረበት ዛሬም በዛው ውሏል። አንድ ዶላር መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫው 81 ብር ከ6207 ሳንቲም ሆኖ ውሏል። ዩሮም ዛሬ ከትላንቱ ያን ያህል ልዩነት አልነበረውም። መግዣው 86 ብር ከ63 ሳንቲም መሸጫው 88 ብር…
#Update

ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም ጨምሯል። መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
#Update

የጤና ሙያተኞች የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ተማሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰኔ 19/2016 ዓ.ም መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

በ17 የጤና ሙያዎች የተሰጠውን የምዘና ፈተና 15 ሺ የሚጠጉ ተመዛኞች መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከምዘናው ፈተናው እርማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዚህ ሳምንት ተጠናቀው፤ ውጤቱ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#የደመወዝ_ጭማሪ " ታች ላለው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ መንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ምን ተባለ ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት…
#Update

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በቅርቡ እንደሚጸድቅ የገንዝብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

" ለታችኛው የደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛ የተሻለ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚያችል ጭማሪ ተሰርቷል " ብለዋል።

ዝርዝሩ በቅርብ ይጸድቃል ሲሉም አሳውቀዋል።

ከዓለም አቀፍ ተቋማት ከተገኘው ድጋፍ ውስጥም አንዱ የሚውለው ለሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ / በድጎማ መልኩ እንደሆነ አመልክተዋል።

ትላንትና በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ እንዳለው በመግለፅ ጭማሪ እንደሚደረግ ተናግረው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኑ የደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት እንደጠየቀና ፤ ከታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግሥት ሠራተኛ 300% ደመወዙ እንደሚጨመር በይፋ መናገራቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
#Update

ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia