TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SafaricomEthiopia #Harari

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል።

በሐረሪ ክልል የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶችን የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን መጠቀም መቀጠል ይችላሉ።

በሐረሪ ክልል አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia #ሐረር_ክልል #Harari

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia #Harari ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ-ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በሐረሪ ክልል መጀመሩን አሳውቋል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት መሆኑን ተገልጿል። በሐረሪ ክልል የደንበኞች…
#Harari #SafaricomEthiopia

በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል።

በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎት በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጥሪ ማዕከል በተለያዩ ቋንቋዎች ፦
- በአማርኛ፣
- በአፋን ኦሮሞ ፣
- በሱማሊኛ፣
- በትግርኛ እና እንግሊዝኛ አገልግሎት የማግኘት አማራጭ ያላቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን በ 👉 700 ላይ በመደወል ማናገር ይቻላል።

#SafaricomEthiopia #ሐረሪ #Harari

@tikvahethiopia
ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

1. ዛሬ ህወሓት የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ሆነው በ4 አቅጣጫ ጥቃት ከፍተዋል ሲል ከሷል። ጥቃቱ ከፍቅያ ገብረ እስከ አደመይቲ፣ ከሰላሞ - ሽራሮ፣ ከጎቦ ፅንዓት ወደ እርዲ ማቲዎስና አዲ አሰር እና አዲ ጎሹ በከባድ መሳሪያ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል። እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከኤርትራ በኩል ለዚህ ክስ ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠም።

2. የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ፦

• ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሏል ብሏል። ህወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰውና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው ብሏል። ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ መውደቁን ገልጿል።

• በሕወሓት ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም ለሰላማዊ  አማራጭ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባቡለበት ሁኔታ ሕወሓትን መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ ስለሆነ ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።

• ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገርን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይል በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል ብሏል።

3. የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት ላይ የትኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዛሬ ለአምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በሰጡት ማብራሪያ ገልጽዋል። ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን አሁንም #የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ አፋር፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች እስር፣ የነዳጅ ዘረፋና ተሸከርካሪ በኃይል የመውሰድ ጨምሮ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። ዕርዳታ ለተቸገሩት ይደርስ ዘንድ ሁሉም ወገኖች የሰብአዊ ተግባራትን እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል። ፓወር በዚህ መልዕክታቸው የድርጊቶቹ ፈፃሚዎችን በግልፅ አልተናግሩም። ፓወር ከዚህ ቀደም ህወሓት 150 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዝረፉንና ሰራተኞችን ማንገላታቱን በመግለፅ ነዳጁን እንዲመልስ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ መልዕክታቸው በአማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ ስለተፈፀሙ ድርጊቶችና ፈፃሚዎች በግልፅ ሳያብራሩ አልፈዋል።

- አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት በእጥፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች። ጦርነቱ እንደገና መቀስቀሱ ​ና በዚህ ሳቢያ አደጋ ላይ የሚወድቀው ህይወት ያሳስበናል ብላለች።

- የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ከአማራ ክልል ግጭት አቁመው ወደ ትግራይ እንዲመለሱ የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ እንዲወጡ ጠይቋል። ንግግር ቢጀመር ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀምር እንዲያደርግ ህወሓት ከWFP የወሰደውን ነዳጅ ለሰብዓዊ ስራ እንዲውል እንዲያደርግ ጠይቋል። ይህን ግጭት ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ግጭት በማቆም ወደፖለቲካ ድርድር ማምራት ነው ብሏል ለዚህም የUK መንግስት የአፍሪካ ህብረትን የማሸማገል ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#ScholarshipProgram

ካስ ኢትዮጵያ/አፍሪካ ሕብረት ቢሮ የነፃ ትምሕርት ዕድል ለኢትዮጵያዊያን የማስተርስ እና የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችና ምሩቃን ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ቤተሰቦች በላከው መረጃ ገልጿል።

የማስተርስ ትምህርታችሁን በሀገር ውስጥ የጀመራችሁ እንዲሁም ለመጀመር እቅድ ያላችሁ የዚህ ስኮላርሽፕ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የማስተርስ ድግሪ ወይም PHD ኖሯችሁ ተጨማሪ ኮርሶችን መማር ለምትፈልጉ በተመሳሳይ እድሉን እንድትጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

የማመልከቻ ቀን ከነሐሴ 26/2014  - መስከረም 20/2015 ዓ/ም ነው።

ዝርዝር መስፈርቶችንና የማመልከቻ መንገዶችን https://www.kas.de/en/web/aethiopien/sur-place-scholarship-program መመልከት ይቻላል።

መልካም ዕድል!

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል። ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል። ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል። ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር…
#Update

#ደቡብ_ወሎ

በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው የደቡብ ወሎ ዞን ከሰሜን ወሎ ዞን ጋር በመሆን መመለስ ያለባቸውን ተፈናቃዮች እና ሰሌዳ አልባ ተሽከርካሪዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

#አምባሰል_ወረዳ

በአምባሳል ወረዳ ሀሰተኛ አሉባልታ ሲነዙ እና ህብረተሰቡን በማወክ ዘረፋ ሊፈፅሙ ተዘጋጅተው የነበሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

መላው ነዋሪ በሀሰተኛ ወሬና አሉባልታ ሳይደናገጥ በፍፁም መረጋጋት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

#ሐይቅ

በሐይቅ ከተማ " ከዚህ ቀደም ህወሓት ቀብሮት የነበረ ከባድ እና ቀላል መሳሪያ ተገኘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳውቋል።

የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክና አካባቢው እንዳይረጋጋ እንዲሁም ተከታይ ለማብዛት ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

" ምንም ባላያችሁበትና ባላረጋገጣችሁበት አዲስ አበባ ቁጭ ብላችሁ በሀሰተኛ መረጃ ህዝብ የምትረብሹ ኃላፊነት የጎደላችሁ የማህበራዊ አንቂ ነን የምትሉ ግለሰቦች፣ ዩትዩበሮች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " ያለው የሐይቅ ፖሊስ ይህን የፈፀሙት ላይ በህግ እንዲጠየቁ እየሰራው ነው ብሏል።

ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ይስደናገጡ በተረጋጋ ሁኔታ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቁ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው…
#Update

#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
"ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል"

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍቶ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት መሳሪያ ወርዶ ወደ ንግግር እንዲገባ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ቀጥለዋል።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል" ሲል የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ጉኤው ምን አለ?

- ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊቆምና የሰላም ሂደቱ ሊቀጥል ይገባል።

- የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው።

- ከዚህ ቀደም የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤አሁንም የሰላም ጥሪ እናቀርባለን።

- የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሌሎችም ወገኖች ለዚህ ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል።

- የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።

- ህፃናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል።

- በወቅታዊ ጉዳይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

- ትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መሪዎች የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለስ በመምከር አባታዊና መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

- የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና የውጭ ሀገራት መንግሥታት፣አፍሪካ ሕብረት፣ ተመድና ሌሎች አካላት ሁሉ የሰላም ጥረቱ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

- የጳጉሜን 5ቱን ቀናት ምእመናን በፆምና ፀሎት እንዲያሳልፉ ጥሪ እናቀርባለን።

(የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ)

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION

ሰንበቴ !

የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደብ አውጇል።

በዚህም መሰረት ፦

- የከተማ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ በከተማው ውስጥ ማሽከርከር ተከልክለዋል።

- ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ #ማንኛውም_ሰው መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

የተጠቀሰው የሰአት እላፊ ገደብ ጥሶ የተገኘ ግለሰብ ላይ አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንዲወሰድ ታዟል ሲል የከተማ አስተዳደሩ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia