TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናትን ህይወት አጥፍታለች።

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" ቦታው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነው፤ ወረዳ አራት አራብሳ ኮንዶሚኒየም እዛ አካባቢ ነው።

ወንጀሉ ተፈፀመው አራት ሰዓት አካባቢ ነው። ግለሰቧ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ወንጀል ነው የፈፀመችው።

የሁለት ዓመት እና የሶስት ዓመት (ክርስቲያን መላኩ እና ጊዮናዊት መላኩ) ህፃናትን ነፍስ ነው ያጠፋችው።

ምክንያቱ ገና እየተጣራ ነው ወንጀል ፈፃሚዋ ግን በቁጥጥር ስር ውላለች። እስካሁን ባለን መረጃ ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ ፀብ ነው የሚባለው።

የአገዳደል ሁኔታው እየተጣራ ነው። በምንድነው የገደለችው እንዴት ነው የገደለችው የሚለው ነገር ... ግማሹ አርዳነው ያላል ግማሹ አንቃ ነው ይላል እየተጣራ ነው ዞሮ ዞሮ ግን የህፃናቱ ህይወት አልፏል ይሄ ነው አሁን ላይ በተጨባጭ ሊገለፅ የሚገባው።

ወንጀሉ እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ፖሊስ መስራት የሚገባውን ሰርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ያቀርባል ህብረተሰቡ መረጋጋት አለበት። "

#ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ…
የፖሊስ መልዕክት !

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦

" ምንም በማያውቁት ጉዳይ በህጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ሁሉንም በእጅጉ አሳዝኗል።

ወላጆች የሚቀጥሯቸው የቤት ሠራተኞችን ማንነት ጠንቅቀው ማወቅ ይገባቸዋል።

እንደ ቤተሰብ ሆነው የሚኖሩ የቤት ሠራተኞች እንዳሉ ሁሉ እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል የሚፈጽሙም ስላሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። "

#ተጨማሪ_መረጃ

• በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ሁለት ታዳጊ ልጆቻቸውን ያጡት ወላጆች በከባድ ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።

• ወንጀሉ በተፈጸመበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም በእጅጉ ተረብሸው ነው የሚገኙት።

• ፖሊስ በወንጀሉ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ነው።

- ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ።

- ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው።

- በወንጀሉ የተጠርጠረችው ግለሰብ በቤት ሠራተኛነት ግድያው ለተፈጸመበት ቤተሰብ ስታገለግል ቆይታለች።

• ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው ወላጆች የሌሉበትን ሰዓት ጠብቃ ነው።

መረጃው ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የአማርኛ አገልግሎት ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
ሸዋሮቢት !

አቶ ውብሸት አያሌው ተገደሉ።

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

አቶ ውብሽተ ለእረፍት ትላንት ማታ ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ አካባቢ ወደ ቤታቸው ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

አቶ ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት ነበሩ።

በሌላ በኩል ፤ በሸዋ ሮቢት ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች ከነሐሴ 26 ጀምሮ በከተማው የፀጥታ ምክር ቤት ተወስኗል።

ከክልከላዎች መካከልም ፦

- ማንኛውም ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል ከምሽቱ 2 ሰአት በኃለ መንቀሳቀስ አይችልም።

- የሰው እንቅስቃሴ ገደብ ከምሽቱ አምስት ስዓት በኃላ ተገድቧል።

- መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች እንዲሁም ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋማት ከምሽት 4 ሰዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ከየትኛውም አካባቢ ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው የሚገኙ ወገኞች ከምሽቱ12 በኃላ መንቀሳቀስ አይችሉም የሚሉት ይገኙበታል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ሰንበቴ ! የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደብ አውጇል። በዚህም መሰረት ፦ - የከተማ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ በከተማው ውስጥ ማሽከርከር ተከልክለዋል። - ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት…
#ATTENTION

የጎንደር ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የተለያዩ የፀጥታ አካላት አልባሳትን መልበስ ተከልክሏል።

- ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ፣ በከተማው በብሎክ አደረጃጀት አካባቢን እንዲጠብቅ በተሰጠው ተራው ከተሰማራው ውጭ በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፡

- ማህበረሰቡን የሚያውኩ አሉባልታዎች ወይም የሃሰት መረጃዎችን በተለያዩ ሚዲያዎች፣ በመጠጥ ቤቶች ወዘተ ማሰራጨት ህዝቡን ማወዛገብ፣ ማሰጨነቅ በጥብቅ ተከልክሏል።

- በከተማው ያሉ ተፈናቃዮች ከተሰጣቸው መጠለያ ካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ለገበያ፣ ለህክምና፣ ለአንገብጋቢ ጉዳዮች፣ ለተለያዩ ስራዎች ከመጠለያው መውጣት ያለበት ተፈናቃይ በሚመለከታቸው የካምፕ አስተባባሪዎችና በክ/ከተማው የፀጥታ መዋቅር እውቅና እና የመውጫና የመግቢያ ፈቃድ መለያ ካርድ ይዞ ተመዝግቦ ተፈቅዶለት የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡

- በአሉባልታ ወሬዎችና ስበብ በመፈለግ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ባንክ ቤት፣ ሱቆችና ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከሎች እና የመሳሰሉትን መዝጋት ተከልክሏል።

- ከነሀሴ 27 ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት ተከልክሏል። አስቸኳይ የሆነ ለምሳሌ ለህክምና፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ለመሄድ፣ ወደ ውጭ አገር ለሚደረግ ጉዞ ከገጠሙ የክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና የክ/ከተማው ሰላምና ደህንነት በጋራ በማየት መታወቂያ ሊሰጡ ይችላሉ።

- አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት የሚፈጥሩ በሸቀጦች በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት በጥብቅ ተከልክሏል።

- በጫት ቤቶች ተሰብስቦ በመቃም አሉባልታና ሽብር መንዛት ተከልክሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወልድያ

ወልድያ አዳሯ #ሰላም የነበረ ሲሆን ዛሬ በ27/12/2014 ባንኮች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

በወልድያ ከተማ አቢሲኒያ እና ህብረት ባንክ ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ጨምሮ ሌሎች በከተማዋ ያሉ ባንኮች አገልግሎት ለመሰጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ገልጿል።

የወልድያ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለሰ አሁንም ቢሆን ወልድያ ሰላም እንደሆነች ገልፀው ፤ ህዝቡ እንዲረጋጋ እና ከሀሰተኛ ወሬ እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ትምህርት የማስጀመር ንቅናቄ በግልገል በለስ ከተማ ተካሄደ።

በንቅናቄው መድረኩ ከትምህርት ሁኔታው ጋር በተያያዘ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

በመተከል ዞን በ2014 የትምህርት ዘመን በነበረው ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች የወደሙን ሲሆን በዚህም ቀላል የማይባሉ ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል።

አሁን ላይ በዞኑ በእጅጉ የተሸሻለ ሰላም በመስፈኑ በ2015 የትምህርት ዘመን ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክና የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መልሶ ግንባታ ማካሄድ እንደሚገባ ተገልጿል።

የመተከል ዞን በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለትምህርት ስራ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቼ ሰራለሁ ብሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ነባር አዲስና ያቋረጡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማገባት በሚስራው ስራ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ማስገንዝቡን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ መተከል ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ ባጋጠመ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከተሉ ሆነዋል ፤ በዚህም ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ደርሶባቸዋል አሁን ላይ የተፈጠረው የተሻለ ሰላም ተማሪዎቹን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ትልቅ ተስፋን ያሳደረ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ሰቆጣ መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል። #ኮምቦልቻ ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር። በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው…
#Update

#ወልድያ

ሰሞኑን በአሉባልታና ሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ የተወሰነ አለመረጋጋት ውስጥ የነበረችው ወልድያ ዛሬ ወደ ቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሷ ተገልጿል። ከከተማዋ ወጥተው የነበሩም ተመልሰዋል። መደበኛ ትራንስፖርት ፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ጀምረዋል።

ዛሬ ጥዋት ላይ አቢሲንያ እና ህብረት ባንኮች ስራ መጀመራቸው እና ሌሎች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል ፤ በዚሁ መሰረት ከሰዓት በከተማው ውስጥ ያሉ ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

#ደሴ

ደሴ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለች ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ከሀሰተኛ መረጃ እና አሉባልታ በመራቅ ሰላሙን ሊያስጠብቅ ይገባዋል። በሀሰተኛ መረጃ አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

#ኮምቦልቻ

ዛሬም እንደትላንቱ ኮምፖልቻ ከተማ እና ነዋሪዎቿ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሆኑ አሁንም ነዋሪው ተረብሾ አካባቢውን ለቆ ፣ ንብረቱን ጥሎ እንዲወጣ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና አሉባልታዎች ሊኖሩ ይችላሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

#ሐይቅ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተሰራጨ የሀሰተኛ መረጃ ሳቢያ አካባቢያቸውን ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን የመመለስ ስራ በከተማው አስተዳደር እየተሰራ ነው። በተጨማሪ በከተማው የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እንዲሁም የኬላ ላይ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን መላው ነዋሪ የወጡትን ክልከላዎች እና ገደቦች እንዲያከብር ተጠይቋል።

#ሸዋሮቢት

በትላንትናው ዕለት " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች የተገደሉት የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ስርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት በደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን መፈፀሙን ከተማ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን #ለውጭ_ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ በዛሬው ዕለት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

@tikvahethiopia