TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና! ዶክተር አብይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግልጫ እየሰጡ ይገኛሉ። ETV ZENA Live!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ነጥብ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ
-ወንድ 362
-ሴት 345

በህብረተሰብ ሳይንስ
-ወንድ 345
-ሴት 335

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡት መግለጫ የነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:-

• ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም #አሸናፊ የሚሆንበት አውድ እንዲፈጠር እንፈልጋለን፡፡

• የአሸናፊዎች ስብስብ አሸናፊ አገር ይፈጥራል፡፡

• አንዱ አሸናፊ አንዱ #ተሸናፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ አያስፈልገንም ይበቃናል፡፡

• ባንድራ የሀሳብ መግለጫ፣ የፓርቲዎች አርማ ነው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ከሆነ ባንድራ በውይይት ሊቀየር ይችላል፣ በጉልበት ማስቀየር የሚፈልግ ካለ እሱ ጉልበት እንዳለው ሌለውን ጉልበት ስላለው አያዋጠም፡፡

• የትኛውም ጫፍ የፖለቲካ አመለካከት ያለው የፖለቲካ ኃይል ካለ የኢትዮጵያ ህዝብ መቀበል አለበት፣ የማግለል ፖለቲካ መቆም አለበት፡፡

• ወንድም ወንድሙን ገድሉ ማሸነፍ አይችልም፤ በሀሳብ ግን አሸናፊ መሆን ይቻላል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «የመግቢያ ነጥብ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች፦ በተፈጥሮ ሳይንስ -ወንድ 362 -ሴት 345 በህብረተሰብ ሳይንስ -ወንድ 345 -ሴት 335 @tsegabwolde @tikvahethiopia»
#አዲስ_አበባ ተረጋጉ እባካችሁ📌

ሳይታወቀን ወሮበላዎች ወደሚፈልጉት የትርምስምስና ሀገር የማፍረስድራማ እንዳገባ ጥንቃቄ እናድርግ። በተለይም አንድነታችንን ጠበቅ አድርገን እንያዘው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV ZENA Live! የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ህግን ለማስከበር እንደሚገደድ እና #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ2011 የትምህርት ዘመን በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ በዘመኑ "295" እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርታቸውን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተው እንዲከታተሉ #ተወስኗል

©የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
@tsegawolde @tikvahethiopia
#update የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2011 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2011 ዘመን በመደበኛ ሆነ መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ 295 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርታቸውን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲከታተሉ መወሰኑን ገልጿል፡፡

በዚህም በመደበኛ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት የ2011 የመግቢያ መስፈርት መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 362 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 345 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

መደበኛ እና የማታ በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 345 እና ከዚያ በላይ ለሴት 335 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ለታዳጊ ክልል ተማሪዎች፣ አርብቶ አደር አካባቢ ተወላጆች እና በፀጥታ ምክንያት ትኩረት የተሰጣቸው ተማሪዎች መግቢያ ውጤት ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 345 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለሴት 330 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 335 እና ከዚያ በላይ እና ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ለግል ተፈታኞች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 375 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 370 እና ከዚያ በላይ ሲሀፖን በህብረተሰብ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 375 እና ከዚያ በላይ ለሴት 270 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 275 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 265 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በህብረተሰብ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 275 እና ከዚያ በላ ለሴት 265 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

እንዲሁም ለዐይነስውራን ተማሪዎች በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 210 እና ከዚያ በላይ ለሴት 200 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

©FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde
እባካችሁ📌የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ አክቲቪስቶች የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወጣቱን አረጋጉት። በመነጋገር የማይፈታ ችግር የለም። ወንድም ወንድሙ ላይ በፍፁም ሊነሳ አይገባም። እኛ ስንኖር እኛ ጤና ስንሆን ነው ስለ ባንዲራ የምናወራው፤ ስለ ሀገር የምናወራው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የሰነበተው የኢጋድ ስብሰባ በስኬት #ተጠናቅቋል፡፡ በስብሰባው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር፣ ሪያክ ማቻርና የሌሎች ቡድኖች መሪዎች የተሻሻለውን የሰላም ስምምነት ፈርመዋል፡፡ የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐብይ_አህመድ የስምምነቱን ፈራሚዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር መልዕክት ለማወቅ ተችሏል።

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ከአንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር ፖሊስ ሁኔታዎችን እየተቆጣጠረ ይገኛል። ውጥረት በነበረባቸው አካባቢዎች የንግድ እንቅስቃሴ ቆሟል።

▪️ከሰዓታት በፊት ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ሰው #እንዲረጋጋ እና ችግሮችን በንግግር እና በፍቅር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል⬇️

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ተቋማቸው የህዝቡን ፀጥታ እና ሰላም ለማስጠበቅ አስፈላጊውን #እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ቅዳሜ ወደ ሀገር የሚገቡትን የኦነግ አመራሮች ለመቀበል የፀጥታ ተቋሙ በቂ ዝግጅት ማድረጉም ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvhethiopia
የአግ 7 ወቅታዊ መግለጫ⬇️

አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬ በመከሄድ ላይ ያለዉ የለዉጥ እንቅስቃሴ የለዉጥ ሂደቱ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነዉን የኢትዮጵያን #ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የናፈቀዉን መላዉን የአለም ህዝብ ያስደመመ ለዉጥ ነዉ። ይህ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ከተጠናወተን የባዶ ድምር የመጠፋፋት ፖለቲካ አላቆን ልዪነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ ማስወገድ ወደምንችልበት የፖለቲካ ስርአት የሚወስደን የለዉጥ ሂደት ባለፉት ጥቂት ወራት በብዙ ውጣዉረዶች ዉስጥ የተጓዘ ቢሆንም አጀማመሩ የሚያበረታታና ተስፋ የሰነቀ ነዉ።

ባለፉት ሁለትና ሦስት ወራት ዉስጥ በግልጽ እንደተመለከትነዉ የዚህ ለዉጥ ደጋፊ የሆኑና ለዉጡን ወደፊት ለማራመድ የሚፈልጉ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች፥ ታዋቂ ግለሰቦች፥ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሀይማኖት አባቶች ለብዙ አመታት በስደት ከኖሩባቸዉ አገሮች ወደ
እናት አገራቸዉ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ከእነዚህ ወደ አገራቸዉ ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዉስጥ አንዱ አርበኞች ግንቦት 7 ነዉ።

አርበኞች ግንቦት 7 ገና ከምስረታዉ ጀምሮ ካራመዳቸዉና ዛሬም በግምባር ቀደም ከሚያራምዳቸዉ መርሆዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚመሰረተዉ የፖለቲካ ስርአት በዜግነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርአት መሆን አለበት የሚል ጠንካራ መርህ ነዉ።

የዜግነት ፖለቲካ ደግሞ የራሱ መብትና ነጻነት እንዲከበር የሚፈልገዉን ያክል እሱም የሌሎችን መብትና ነጻነት ማክበር እንዳለበት የሚያውቅና የሚረዳ ዜጋ መኖርን የግድ ይላል። አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያ ዉስጥ መገንባት አለበት ብሎ ለአመታት የታገለለት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ከሚፈልጋቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች ዉስጥ አንዱና ትልቁ የፖለቲካ አካሄዳቸዉ ከማይጥመንና በሃሳብ ከምንለያያቸዉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ወይም የወል ስብሰቦች ጋር ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር መቻልን ነዉ። የማይስማማንን እና የምንቃወመዉን የፖለቲካ አቋም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ የማንችል ከሆነ #ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት ቀርቶ ስለ ዲሞክራሲ ማሰብም አንችልም።

ባለፈዉ እሁድ ጳጉሜ 4 ቀን 2010 ዓም በዉጭ አገሮች ለረጂም አመታት ይንቀሳቀሱ የነበሩት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ አመራር አባላት ወደ አገራቸዉ ሲመለሱ የአዲስ አበባና አካባቢዉ ነዋሪ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የኔ ነዉ ብሎ የሚያምንበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እያውለበለበ በደስታና በሆታ ከፍተኛ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አገር ውስጥ ሆነው በነጻነት ትግል ለማካሄድ እንዳይችሉ የተገፉ ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች ባለፉት ሶስት ወራት ዉስጥ ወደ አገራቸዉ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፥ አሁንም በመመለስ ላይ ናቸዉ። እነዚህ ወደ አገራቸዉ የሚመለሱ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እናራምዳለን ብለዉ የታገሉለትን የፖለቲካ ፕሮግራምና የኤኮኖሚ ፖሊሲ አምኖ የተቀበለ አባልና ደጋፊ አላቸዉ። የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች የንቅናቄዉ አመራር አባላት ከዉጭ አገሮች ሲገቡ #ያሰኛቸዉን አርማና መፈክር ይዘዉ ወጥተዉ አንደተቀብሏቸዉ ሁሉ አሁን በመግባት ላይ ያሉና ወደፊትም ወደ አገራቸዉ የሚገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች ያሰኛቸዉን አርማና መፈክር አንግበዉ መሪዎቻቸዉን የመቀበል ሙሉ #መብት ሊኖራቸዉ ይገባል ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ንቅናቄው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በጽናት እየታገለ ያለው ዜጎች ድጋፋቸውንም ሆነ ተቃውሟቸውን #በነጻነት መግለጽ የሚችሉበት ሥርአት በአገራችን እንዲሰፍን ነዉ እንጂ አንዱ የሌላውን መብት በጉልበትና በሀይል መጨፍለቅ እንዲችል አይደለም።

ከሰሞኑ በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪዎች ወደ አገራቸዉ ሲመለሱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በጎዳናዎች ላይ የሰቀሉትን የድርጅታቸውን ባንዲራ እናወርዳለን በሚሉና መውረድ የለበትም በሚሉ ሀይሎች መካከል የተነሳዉ አግባብ የለሽ #ግጭት ንቅናቄያችን የሚታገልለትን የዲሞክራሲ መርህ #የሚጻረር ተግባር ከመሆኑም በላይ በአገራችን የፈነጠቀውን የመቻቻል ፖለቲካ ከጅምሩ የሚያደበዝዝ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7 ድርጊቱን በጽኑ #እያወገዘ በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ የንቅናቄያችን አባላትና #ደጋፊዎች ቢኖሩ ከዚህ አይነቱ ትርጉም የለሽና ፀረ-ዲሞክራሲ የሆነ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ #እንዲታቀቡ ያሳስባል።

አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ ስርአት እንገነባለን ስንል የተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች በፖለቲካ አስተሳስብና በርዕዮተ አለም ቢለያዩም በልዩነቶቻቸዉ ላይ ተከባብረዉና የህዝብን ዳኝነት ተቀብለዉ መኖር አለባቸዉ ማለት ነዉ።

ስለሆነም ከሰሞኑ በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በታዩ ሽኩቻዎች ላይ በሁለቱም ጎራዎች የተሳተፉ ሀይሎች ሁሉ እንደ ማህበረሰብ አንድ ላይ ከሚያጠፋን የፖለቲካ አካሄድ ተላቅቀዉ እንደ አንድ አገር ህዝብ ጎን ለጎን አብሮ የሚያቆመንን የፖለቲካ ስርአት በጋራ መገንባት የሚያስችለንን ሁኔታ ፈጥረን የጋራ አገራችንን በጋራ እንድንገነባ አርበኞች ግንቦት 7 አገራዊ የአደራ ጥሪ ያስተላልፋል።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለአለም ትኑር!!!

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦነግ አቀባበል⬇️

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሚደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ #ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፊታችን ቅዳሜ መስከረምን 5 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ለኦነግ የሚደረገው አቀባበል ስነ ስርዓት ለኦሮሞ ህዝብ ክብር የሚዘጋጅ ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ነገሪ፥ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ምህዳር መስፋፋቱን ተከትሎ መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት አድርገው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን አንስተዋል።

ከውጭ ሀገራት እየተመለሱ ላሉና ለተመሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም በክልል እና በፌደራል ደረጃ አቀባበል ተደርጎላቸዋልም፤ እየተደረገላቸው ይገኛልም ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ መስከረም 5 2011 ዓ.ም ምህረት የሚደረገው አቀባበል በተለይ ወጣቶች የህዝቡን አንድነት በሚጠብቅ መልኩ እንዲሆን ማድረግ አለበት ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ የአቀባበል ስነ ስርዓት #የማያስደስታቸው አካላት ሊኖሩ ይችላሉ ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ በተለይ ወጣቱ ከእነዚህ አካላት የሚመጡ ትንኮሳዎችን በብስለት ማለፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።

እንዲሁም የአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ለየት ያለ ነገር በሚመለከቱበት ወቅት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ዶክተር ነገሪ አክለውም፥ ማንኛውም አካል #ይገልፀኛል፤ ይወክለኛል የሚለውን ምልክትና ባንዲራ የመያዝ መብት አለው፤ የተደረገው ትግልም ሀሳብን በነፃነት መግለጽ እንዲቻል ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ከባንዲራ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ በትናንትናው እና በዛሬው እለት የሚስተዋሉ ችግሮች በምንም መስፈርት #ተቀባይነት የሌለ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

አሁን ያለንበት ወቅት ምክንያት ፈልገን የምንጣላበት ሳይሆን ምክንያት ፈልገን አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ማንኛውም አካል ከባንዲራ ጋር በተያያዘ #ሊጋጭ አይገባም ብለዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ - ዛሬ⬇️

🔹1

ዛሬም በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች #ስንደቅ_አላማ በመስቀልና የከተማዋን ጎዳናዎች በማቅለም ዙሪያ አለመግባባቶች ታይተዋል። #አዲሱ_ገበያ አካባቢ የኦነግን አርማ ይሰቀል/ይቀባ በሚሉና ቀድሞ የተሰቀለው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ስንደቅ #አናስነካም ባሉ ወጣቶች መካከል ግብ ግብ ተነስቶ ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። በአስለቃሽ ጭስ ወጣቶቹን መበተን ያቃተው ፖሊስ ጥይት ወደ ስማይ #ተኩሷል። ኋላም በዶፍ ዝናብ ምክንያት ወጣቶቹ #ተበትነዋል
.
.
🔹2

የአዲስ አበባ ወጣቶችም ሆኑ የኦነግ ደጋፊዎች ከጠብ #አጫሪነት እንዲቆጠቡ ይህ ካልሆነ ግን ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት ለማስከበር #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ዘይኑ ጀማል አስታወቁ። ባለፉት ሁለት ቀናት ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ ግጭቶች መከሰታቸውንና ሁኔታው ተባብሶ በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሙከራ መደረጉን የተናገሩት ኮምሽነር ዘይኑ ማናቸውም ዜጋ ያመነበትን የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ #የመውጣትና ተገቢ በሆኑ አካባቢዎች የመስቀል መብቱ የተከበረ ሲሆን፣ ጎዳናዎችንና የጋራ መገልገያዎችን #ቀለም መቀባት ግን ተገቢ አለመሆኑን አስረድተዋል።
.
.
🔹3

#የኦነግ አቀባበል ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ ደጋፊዎች ከግጭት እራሳቸውን በማራቅ በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ #አሳስቧል

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#udate ኢንሴኖ⬇️

ቡታጅራ አቅራቢያ ኢንሴኖ በተባለች ከተማ አለመረጋጋት መኖሩን በከተማዋ የሚገኙ የቻናላችን አባላት ገልፀዋል። የክልል ልዩ ሀይል ሁኔታውን ለመቆጣጠር እየሰራ እንደሆነም ተሰምቷል።

📌ለአለመረጋጋቱ መነሻ የሆነውን ጉዳይ እንዲሁም ስለ ደረሰው ጉዳት ዝርዝር እና የተጣራ መረጃ ሲደርሰኝ ወደናተ አደርሳለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia