TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
⚠️እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

ትላንት ለሊት 6:30 አካባቢ በድሬዳዋ አስተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ ዶልፊን ” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መስመር በኩል ይጓዝ ከነበረ በተለምዶ “ ሲኖትራክ ” ተብሎ ከሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ነው።

(ድሬዳዋ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ? የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል። በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።…
🔈#የተማሪዎችድምጽ

ባለፈው ወር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከፈተናው ጋር ተያይዞ ያላቸውን ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ ፦

- የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እኩል ፈተናውን ወስደው፣ ውጤት ለምን በተለያየ ጊዜ ተገለፀ ?

- የመንግሥት ተፈታኞች በብዛት ሲያልፉ በርካታ የግል ተቋማት ተፈታኞች ለምን ወደቁ?

- እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ነጥብ ያላቸው መቶ ጥያቄዎች ተፈትን 37.92 አይነት ውጤት እንዴት ተመዘገበ ? የAI ስህተት ካለ ይነገረን።

- በጣም ተዘጋጅተን የተፈተንን ሰዎች በዚህ ትኩረት ሳይሰጠው በተፈተነው ፈተና ምክንያት ሞራላችን እንዲነካ እና ተስፋም እንድንቆርጥ ተደርገናል።

- ፈተናው ላይ ትልቅ ውጤትን ያመጣሉ የተባሉ ብዙ ጎበዝ ልጆች እንደተጠበቀው አልሆነም።

- ውጤታችን እንደገና ሊታይልንና የተፈተነው ጥያቄ ከነመልሱ ይፋ ሊደረግልን ይገባል።

... የሚሉ ቅሬታዎች በተፈታኞቹ ተነስቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ የሆኑትን እዮብ አየነው (ዶ/ር) ጠይቋል።

ከውጤት ነጥብ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ኃላፊው ተከታዩን ብለዋል ፦

1ኛ. የጤና ትምህርት ዘርፍ ሁለት ፈተና (ጠዋት ከ100 ከሰዓት ከ100 በድምሩ ከ200) ስለሚፈተኑና ለማለፊያ የሁለቱ ፈተናዎች ውጤት ተደምሮ አማካኝ ውጤት ስለሚያዝ ውጤታቸው በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

2ኛ. አንዳንድ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ለምሳሌ ፦ ሒሳብ እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት በተለያዩ ምክንያቶች ተማሪዎች የተፈተኑት ጥያቄ ቁጥር ከመቶ ያነሰ ስለነበር ያገኙት ውጤት ወደ መቶ ሲቀየር በነጥብ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

" ውጤት ሲገለፅ የጊዜ መቀዳደም ካልሆነ በስተቀር በሲሰተሙ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልነበረ " ኃላፊው ገልጸዋል።

የማለፍ ምጣኔን በተመለከተም ፥ " ተፈታኞቹ የተማሩባቸውን ተቋማት እንዲሁም የራሳቸውን ብቃት መመልከት " አለባቸው ብለዋል።

ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች 100% ያሳለፉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ኃላፊው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።


ይህንን ምላሽ የተመለከቱ ተማሪዎች ፥ " ለቅሬታችን የተሰጠው ምላሽ ተገቢ አይደለም ፤ አሁንም ቢሆን ውጤታችን እና የሰራነው በድጋሚ ይታይ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የፋርማሲ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ፥ " ከዚህ በፊት እንደነበረው የጠዋት እና የከሰአት አማካይ (Average) የሚያዝ እንደሆነ በምላሹ ላይ ሰምተናል " ብለዋል።

" ግን ፈተናውን ከጨረስን ከአንድ ቀን በኋላ ፈተናው ችግር አለበት / ተሰርቋል ተብለን በአንድ ቀን ልዩነት እንደገና ፈተና ተቀምጠናል፤ ስንቀመጥም የጠዋቱን ብቻ ነበር አንዴ የተፈተንነው እንጂ የከሰአቱን ሌላ ጊዜ ነው የተባልነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ በጠዋቱ ፈተና ብቻ ነው pass and fail የሆነው። ስለዚህ ትምህርት ሚኒስቴር ቃሉን አክብሮ የከሰአቱን ፈተና ከተፈተንን በኋላ ነው አማካይ መያዝ ያለበት " ብለዋል።

ተማሪዎቹ አለን ያሉትን ቅሬታ ይዘን የሚመለከተውን አካል የምናነጋግር ይሆናል።

Via @tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#OFC #Ethiopia

" በአንድ ፓርቲ ፍላጎትና ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም !! " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦

" ዋና የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ መንግሥት ነው። ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም።

ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሆነን ፣ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ጋር ሆነን ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላደረግነው ነገር የለም።

ዋናው ጉዳይ ስልጣን የያዘው ቡድን ሀቀኛ ፍትሃዊ የሚባለውን ነገር በጭራሽ አይፈልገውም።

' ስልጣን እኛ እጅ ነው ' ተንበርከኩና እኛ ጋር ግቡ ወይም የስልጣን ፍርፋሪ ኑና ውሰዱ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ ከመገዳደል ፖለቲካ ወደ መደራደር ፖለቲካ እንዲገባ አይፈልግም።

ችግሩ ይሄ ነው በአንድ እጅ ማጨብጨብ አይቻልም።

እኛ የምንችለውን ያክል ይሄ ሀገር መሸጋገር የሚችለው ፣ የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መምጣት የሚችለው ፣ የተሳካ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት የሚችለው ሁሉም የኢትዮጵያ ኃይሎች የተሳተፉበት ፦
- ብሔራዊ እርቅ
- ብሔራዊ ድርድር
- ብሔራዊ ምክክር ሲደረግ ነው እያልን ስንጠይቅ ነበር።

ፖለቲካ እስከሚገባን ድረስ አሁን እየተገፋ ባለበት መንገድ 3 ነገሮች በኢትዮጵያ ምድር መሆን አይችሉም።

1ኛ. ሀቀኛ ሰላምና መረጋጋት አይመጣም ፥ ሰላምና መረጋጋት አሁን እየገፉ ባሉበት መንገድ መምጣት አይችልም። እኛም ኖርን አልኖርን !

2ኛ. በኢትዮጵያ ምድር ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ፣ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ፣ ሀቀኛ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፣ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ስልጣን ላይ የሚወጣ መንግሥት ፣ የህዝቡን ይሁንታ ካጣ ከስልጣን የሚወርድ መንግሥት መፍጠር አይቻልም።

3ኛ. በአንድ ፓርቲ ፍላጎት ፣ ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም።

አንድ ቀን እነሱም ሰምተው ፤ ችግሩም ደግሞ አስተምሯቸው መስመር ሊይዝ ይችላል።

እኛ እንሞክር ነበር አሁንም ያንኑ ህጋዊ እና ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን።

በሀገሪቱ ግጭት ያባባሰው ስር የሰደደው የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ነው። "


#OromoFederalistCongress

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC #Ethiopia " በአንድ ፓርቲ ፍላጎትና ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም !! " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦ " ዋና የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ መንግሥት ነው። ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም። ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሆነን ፣ከዲፕሎማቲክ…
#OromiaRegion

" ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ችግሮቹ እንዲወሳሰቡ እያደረጉ ያሉት እኮ እነሱ ናቸው ( ኦፌኮን ጨምሮ አንዳንድ ፓርቲዎች) " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦

" የኢፌዴሪ መንግሥት ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ፣ ያሉትን አለመግባባቶች በሀሳብ ትግል እልባት ለመስጠት ብዙ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል።

ከነዚህ ውስጥ ከሀገሪቱ ታሪክ ፣ ከሀገረ መንግስቱ ግንባታ ጋር ተያይዞ ያደሩ ቅሬታዎች ስላሉ እነዚህ ቅሬታዎች እንዲፈቱ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ እየሰራ ነው።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ከጠብመንጃ ይልቅ በሀሳብ ትግል እንዲደረግ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ነው የቀጠለው።

ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከማድረግ አኳያ እኛ የምንታማበት ነገር የለም።

አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች
#ኦፌኮን ጨምሮ የድርሻቸውን ባለመወጣት ፤ ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ችግሮቹ እንዲወሳሰቡ እያደረጉ ያሉት እነሱ ናቸው።

አንዱ የኮሚሽኑ ስራ እንዳይሳካ እራሳቸውን በማግለል እየተንቀሳቀሱ መገኘታቸው ነው።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተከሰተውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አንደኛ በሀገር በቀል በገዳ ስርዓት አባገዳዎችን ፣ የሃይማኖት አባቶችን ፣ ሃደሲንቄዎችን በማሳተፍ እርቅ እንዲወርድ ብዙ ጥረት አድርገናል። ጥረታችን አልተሳካም።

ሁለተኛ የሶስተኛ ወገኖችን ባሳተፈ መልኩ ችግሩ ይፈታ በሚል ሀሳብ ስለቀረበ ተቀብለን በሁለት ዙር ከዚህ ከአሸባሪው ቡድን (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ማለታቸው ነው) ውይይቶችን አድርገናል። ሁኔታው በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ አልቻለም።

ነገር ግን በአንድ እና ሁለቴ ብቻ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን ለሰላም ጠንክረን እንሰራለን። "

#OromiaRegionalGovernment
#VOA

@tikvahEthiopia
#Rwanda

በሩዋንዳ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖል ካጋሜ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ያልተጠናቀቀ ቆጠራ አሳይቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በበርካታ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ባካሄደው ቆጠራ (79% ቆጠራ) ካጋሜ 99.15 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል።

24 ዓመታትን ሩዋንዳን በፕሬዜዳንትነት የመሩት ፖል ካጋሜ ውጤቱ ለተጨማሪ 5 ዓመታት በስልጣን እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል።

ሶስት ብርቱ ናቸው የተባሉ ተቀናቃኞቻቸው ከምርጫ ፉክክሩ ውጭ በሆኑበት ነው ምርጫው የተካሄደው።

በምርጫው የተሳተፉት የአየር ንብረት ጥበቃ ተሟጋች ፍራንክ ሃቢኔዝ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ፊሊፕ ምፓይማና ከ1 በመቶ ያነሰ መራጭ ነው ያገኙት።

ከዚህ በፊት በነበረው የአውሮፓውያኑ 2017 ምርጫ ካጋሜ በ98.8 ድምጽ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ፖል ካጋሜ እኤአ 1994 የሩዋንዳ የዘር ፍጅት በኋላ በመሪነት ስፍራ የተቀመጡ ሲሆን ከ2000 በኋላም በፕሬዚዳንትነት ቀጥለዋል።

#BBC #AlJazeera

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
⚠️እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️ ትላንት ለሊት 6:30 አካባቢ በድሬዳዋ አስተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ ዶልፊን ” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መስመር በኩል ይጓዝ ከነበረ በተለምዶ…
⚠️እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

በሶማሌ ክልል፣ ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው በተባለ ቦታ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በተጨማሪም በ14 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

አደጋው የተከሰተው በሁለት መኪኖች ግጭት መሆኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ትላንትና ለሊት 6:30 አካባቢ ላይ በድሬዳዋ  ከተማ ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ዛሬ ጥዋት መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Ethiotelecom #telebirr

ሁለቱን የከተማ መስተዳድሮች ጨምሮ የአብዛኛዎቹ የክልል ገቢዎች ግብር በቴሌብር መክፈል ተችሏል፤ እንኳን ደስ አላችሁ!!

ግብር ለመክፈል መጉላላት ሳይጠበቅብዎ በሥራ ገበታዎ ላይ እንዳሉ በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ባሉበት ቦታ ሆነው በምቾት ይክፈሉ!

ሥራን በክብር
ግብርዎን በቴሌብር !

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ !

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ https://t.me/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#EDR

ኢጂነር ታከለ ኡማ ሹመት ተሰጣቸው።

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው እንደሾሟቸው የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አሳውቋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ላለፉት ዓመታት በትምህርት ላይ ነበሩ።

ለትምህርታቸው ወደ ውጭ ሀገር ከመጓዛቸው በፊት የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዛ ቀድሞ አዲስ አበባ አስተዳደርን በከንቲባነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወደ ትግበራ እንዲገባ መደረጉ ታውቋል።

ይህ መመሪያ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያን ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የመንግስትና የግል ድርጅቶች ገበያውን በመጠቀም የድርጅቶችን የድርሻ እና የብድር ስነዶችን በመሸጥ እና ገንዘብ በመስብሰብ ፕሮጀክቶችን ለመስራት አቅም ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርላቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው መውጣቱ የድርሻ ወይም የብድር ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ኢንቨስተር ፈቃድ ካለው ገበያ አስፈላጊው ቁጥጥርና ግልጸኝነት በተሟላበት የግብይት አሰራር፣ ፈቃድ ባለው ተገበያይ አማካኝነት የተፈቀዱ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት እና ለመሸጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል ተብሏል።

#EthiopianCapitalMarketAuthority

@tikvahethiopia
#Ethiopia #UAE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ የተፈራረሙት ስምምነት ምንድነው ?

1ኛ. በኢትዮጵያ ብር እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) ድርሀም መካከል የምንዛሬ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል።

ይህ ስምምነት 46 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊዮን UAE ድርሃም በማዕከላዊ ባንክ በኩል ለመቀያየር / ለመለዋወጥ ያመቻችላቸዋል።

ዓላማው ፦
° በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ለመደገፍ ነው።
° ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶችን የበለጠ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ነው።

2ኛ. ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ/UAE በራሳቸው ገንዘብ (በብር እና ድርሃም) ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° የንግድ ልውውጦችን በራሳቸው (በሁለቱ ሀገራት ገንዘብ) ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
° የፋይናንስ እና የባንክ ትብብርን ያጠናክራል።
° የፋይናንስ ገበያዎችን ያዳብራል።
° የሁለትዮሽ ንግድን ያመቻቻል።
° የቀጥታ ኢንቨስትመንት ያበረታታል።
° የሙያ እና መረጃ ልውውጥ እንዲኖር ያመቻቻል።

3ኛ. የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ስርዓቶችን ለማገናኘት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ልውውጦችን ውጤታማነት ያሳድጋል።
° በፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ እና በማዕከላዊ ባንኮች ዲጂታል ምንዛሬዎች ላይ ትብብር እንዲደረግ ይረዳል።
° በክፍያ መድረክ አገልግሎቶችና በኤሌክትሮኒክ ስዊች በኩል ትብብር ያደርጋሉ። በክፍያ ስርዓቶቻቸው በኩል ኢቲስዊች እና ዩኤኢስዊች እንዲሁም በመልእክት መላላኪያ ስርዓቶች በሀገራቱ የቁጥጥር መስፈርቶች በማገናኘት ትብብር ያደርጋሉ።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በአሁን ሰዓት ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር አንዷ ናት።

ሁለቱም የ #BRICS+ አባል ሀገራት እንደሆኑም ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከብሔራዊ ባንክ እና ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#ይነበብ ወጣቶችን ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ? በኦንላይን ወይም በደላሎች አልያም በኤጀንሲዎች " እዚህ ሀገር ጥሩ ስራ አለ ፤ ክፍያውም ከፍ ያለነው " ተብለው ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ሀገራት ይዘዋወራሉ። ለአብነት ያህል ወጣቶች ከሚዘዋወሩባቸው ሀገራት መካከል የሳይበር ማጭበበር ( Cyber Scam) ማዕከላት ተብለው ወደ ሚታወቁት ፦ • ማይናማር ፣ • ካምቦዲያ፣ • ላኦስ • ማይናማር ታይላንድ…
#OnlineScam

ባለፈው ወር ላይ የላኦ እና የቻይና ፖሊስ በሰሜን ላኦስ ጎልደን ትሪያንግል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በህገወጥ የጥሪ ማእከል የኦንላይን ማጭበርበር (Online Scam) ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያሏቸውን 280 ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

ግለሰቦቹም ወደ ቻይና ዲፖርት ተደርገዋል።

ፖሊስ ግለሰቦቹን በያዘበት ወቅት 460 ኮምፒዩተሮች እና 1,345 ስልኮችን ይዟል።

እንዚህ አካላት በኦንላይን የተለያዩ ሀገራት ያሉ ሰዎችን በውሸት ማንነት እያነጋገሩ ገንዘብ የሚያጭበረብሩ ናቸው።

Photo Credit - Lao Security

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሃያ (20) ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችንም እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” - ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ 40 በመቶ የሚሆን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ‘ በጉልበት ሊወስደው ነው ’ ስትል ከሰሞኑን በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል። ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቤተ ክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው…
#Update

“ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው ” - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር 

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን “ 20 ሄክታር ” የሚሆነውን የኮሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር “ በጉልበት አጥሮታል ” ስትል ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን ሰጥታ ነበር።

ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ እንዳስገባችም ገልጻ፣ ምላሽ ካልተሰጣት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንደምትገደድ ነው የገለጸችው።

ቤተ ክርስቲያኗ፣ ይህን ቃል ከመስጠቷ በቀደሙት ቀናት ውስጥም ከተማ አስተዳደሩ 40 በመቶ የሚሆነውን ይዞታዋን “ በጉልበት ሊወስደው ነው ” ስትል ተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምላሹን ሰጥቷል።

አስተዳደሩ ፤ “ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው። በበጎ አድራጎት እጅ ነው የነበረው ” ብሏል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አካል፣ “ በኢትዮጵያ ሲቪክ ማኀበራት በኩል NGO ስራውን ጨርሶ መሬቱን ለመንግስት አስረክቦ ሂዷል ” ብለዋል።

“ በቤተ ክርስትያኗ ጥያቄ ለአምልኮ ወይም ለቀብር ቦታ ተብሎ የተሰጠ መሬት አይደለም ” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ NGO ለበጎ አድራጎት ስራ ወስዶ ሲሰራበት የነበረ፣ በኋላ ፍቃዱን መልሶ የወጣበት የNGO መሬት መሆኑን ነው የማውቀው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ያለው ሂደት ደግሞ በህግ በኩል ነው ተይዞ ያለው። ስለዚህ ‘ በአስተዳደሩ ተወሰደብን፣ ወከባ ተፈጠረብን ’ ለሚለው ነገር አስተዳደሩ የፈጠረው ወከባ የለም ” ብለዋል።

“ ለቤተ ክርስትያን መሬቱ ሲሰጥና ሲቀበሉ ውል አልነበረም፤ እነዚህ ሦስተኛ አካል ናቸው ማለት ነው ”  ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥
- ቤተ ክርስቲያኗ እኮ መሬቱ ይዞታዋ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዳላት፣
- ከግቢው ውስጥ የነበራት መጋዘን ትላንት እንደፈረሰ፣
- ሃያ (20) ሄክታሩ ይዞታዋ እንደታጠረ ነው የገለጸችው ለዚህ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ሲል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

የአስተዳደሩ አካል ፥ “ መሬቱ በእጃቸው ላይ የነበረ አይደለም። በNGO እጅ የነበረ ነው። ስለዚህ ይህን በተመለከተ ይህንን ነው ማድረግ የሚቻለው ” ብለዋል።

“ 12 ሚሊዮን የቃለ ህይወት እምነት ተከታዮች ወይም 35 ሚሊዮን ወንጌላዊያን ተከታዮችን ጠቅሰው እያስኬዱት ያሉትም ስህተት ነው ” ሲሉ አክለዋል።

“ ምክንያቱም ቢመለከትም የቢሾፍቱ ቃለ ሕይወትን ነው እንጂ በአጠቃላይ የወንጌላዊያን ጥያቄና የመብት ጥሰት አድርገው በማቅረባቸው እኛም ትንሽ ከፍቶናል ” ነው ያሉት።

“ የሚመጣውን ስሞታ እንደ መንግስት ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ያለው አስተዳደሩ፣ “ ባለመብት ከሆኑ ሚዲያ መጥራትና ሰላም እንዲጠፋ መቀስቀሱ ተገቢ አይደለም ” ሲል ወቅሷል።

ስለዚህ ይዞታው የቤተክርስቲያን አይደለም ብላችሁ ነው የምታምኑት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ፣ “ በNGO እጅ ነው የነበረው። NGO ደግሞ የወሰደው ለበጎ አድራጎት ስራ ነው። ለአምልኮት፣ ለመቃብር አይደለም ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

መጨረሻም፣ “ የህግን መንገድ መከተሉ የተሻለ ነው የሚሆነው። አዲስ ጥያቄ ከሆነ ከእነርሱ ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

#TilvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ያለሙትን አሳክተው እፎይ የሚሉበትን የተሻለ አማራጭ ይዘን እየመጣን ነው‼️
በቅርብ ቀን ይጠብቁን …
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

“ ከሆስፒታሉ ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው ” - ታካሚዎች

“ የአቅርቦት እጥረት አለ ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል 

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በመድኃኒት እጥረት ሳቢያ ታካሚዎች ከ3 እጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ከግል መድኃኒት ቤቶች መድኃኒት ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

በርካታ ታካሚዎች ዋጋው ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ህክምናቸውን እያቋረጡ መሆኑን፣ ችግሩ መቀረፍ ሲገባው ተባብሶ እንደቀጠለ አስረድተዋል።

በተለይ እንደ ሴፍትሪያክዞን፣ ዲ40% የመሳሰሉ መድኃኒቶች ከሆስፒታሉ ከጠፉ ወራት እንደተቆጠሩ ተናግረዋል።

“ ከሆስፒታል ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው” ያሉት ታካሚዎቹ፣ የላብራቶሪ ምርመራዎች ‘በተደጋጋሚ ተበላሽተዋል’ እየተባለ የምርመራ ከሆስፒታል ውጪ ለማሰራት እየተገደዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩ ለምን ተፈጠረ ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት መለሰ፣ “ አሁን ባለው የበጀት Ristriction፣ የፋይናንስ እጥረት ምክንያት አንዳንድ መድኃኒቶች አይኖሩም ” የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

“ በወቅታዊ ችግር አሁን በወቅታዊ ችግር መንገድ ዝግ ነው። መድኃኒት ቀጥታ ከአዲስ አበባ በደጀን በኩል ነበር የሚመጣው አሁን በአፋር ክልል ነው የሚመጣው። የአቅርቦት እጥረት አለ ” ብለዋል።

➡️ ዲ 40% የተሰኘው መድኃኒት ያልነበረው “ትራውማ ካዡዋሊቲ” በዝቶ ስለነበር እንደሆነ፣
➡️ ይሁን እንጂ አሁን የመድኃኒት አቅርቦቱ እንዳለ፣ 
➡️ የላብራቶሪ ማሽኑ በመብራት መቆራረጥ ሳቢያ በመቆሙ ለሳምንት የተመላላሽ ታካሚዎች ህክምና ተቋርጦ እንደነበርና ማሽኑም እየተጠገነ መሆኑን አስረድተዋል። 

ሆስፒታሉ በቀን ከ3,000 በላይ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 13 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ የህክምና አገልሎቶች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ ጥዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው።

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።

" ጥዋት ስራ መግቢያ እና ስራ መውጫ ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ይታያል " ያለው መ/ቤቱ " ይህንን ለመቀልበስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናት አስጠንቶ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የፍሰት ማሻሻያዎች አሉ " ብሏል።

ከነዛ ውስጥ አንዱ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጿል።

የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንና የሕግ ማዕቀፍም መዘጋጀቱን በጣም ከዘገየ ከ2 እስከ 3 ወር ወደ ተግባር እንደሚገባ አስረድቷል።

" ይሄ ፍሰቱን ያሻሽላል " ያለው መ/ቤቱ " ፒክ ሀወር / ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር ተብሎ ፕሮግራም ወጥቶለት ለምሳሌ ዛሬ ሙሉ ቁጥር የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ጎዶሎ ቁጥር በፈረቃ እንዲንቀሳቀስ የሕግ ማዕቀፍ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው " ሲል አሳውቋል።

የኦሮሚያ እና ፌዴራል ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺህ በላይ እንደሆኑ የተገለጸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጥዋት እና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ብሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia
#SafricomEthiopia

🎉 የምስራች ለሁላችን!
🎁 ተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ተመልሰው መጥተዋል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
⚠️ እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

ዛሬም በትራፊክ አደጋ የበርከታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የዛሬው አደጋ በጌዴኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ዲባንድቤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የደረሰው።

በዚህም የ9 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።

ከሟቾች ባሻገር በ4 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሰ ሲሆን ተጎጂዎቹም ወደ ዲላ ሪፈሪያል ሆስፒታል ሪፈር ተብለው ገብተዋል።

የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤  የአደጋው መንስኤ ታርጋ ቁጥሩ ኢት ኮድ (03)19178 የሆነ ሲኖትራክ፣ ከዲላ ወደ ሞያሌ ሲጓዝ ከነበረው ዶልፈን ሚኒንባስ ኮድ 0322503፣ በተመሳሳይ ከዲላ ወደ ከቡለሆራ ሲጓዝ ከነበረ FSR መኪና ታርጋ ቁጥር AA ከድ 03 74596 ጋር በመጋጨቱ መሆኑን አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM