" እኛ በሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን። ይኸው ሱዳን ውስጥ ስቃያችንን እያየን ነው።
በተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን ተሰብስበው እንዲታሰሩ እና ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ሆኗል።
ለአመታት በኖርንበት ሀገር ምንም በማናውቅበት ሁኔታ ሰብሰው አስረውናል።
30 እና 40 ዓመት በላይ የኖሩ ጭምር ታስረዋል። ምክንያት ስንጠይቅ ' ከላይ ነው ትዕዛዙ ' ይሉናል። ሰዎቹ የሌ/ጄነራል አልቡርሃን ናቸው።
ጭራሽ ' ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF ለሚባለው) መረጃ ትሰጣላችሁ ' የሚል ነገር ያወራሉ የጄነራሉ ሰዎች።
እስካሁን ያለው የታሳሪ ብዛት ከ600 በላይ ይሆናል።
ህጻናት እና ሴቶች በብዛት አሉ ፣ ነፍሰጡሮች ፣ አዛውንቶች፣ ህመም ያለባቸው ሰዎችም አሉ።
ምቹ ባልሆነ ስፍራ ፣ በየሜዳው ነው ያለነው ፤ ከሙቀቱ ተደምሮ እጅግ ስቃያችንን እያየን ነው። ራሳቸውን ስተው የነበሩ ሴቶችም አሉ። ወደ ህክምና ተብሎ ከተወሰዱ በኃሏ የት እንደደረሱ አይታወቅም።
' እዚህ መኖር አትችሉም ' ከተባልን የለፋንበትን ንብረት ይዘን ወደ ሀገራችን እንዲመልሱን ይደረግ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጩኸታችንን ይስማንና ካለንበት ስቃይ ያሶጣን። " - በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን
#TikvahEthiopiaSUDAN
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM