TIKVAH-ETHIOPIA
1.4M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
@samcomptech

እርሶ ከዘመኑ እኩል መራማድ ከሆነ ምርጫዎ ዘመኑን የዋጁ የላፕቶፕ ምርቶችን አኛ ጋር በተመጣጣኝ ዎጋ ያገኛሉ።

ለቢሮ፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን፣ ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ የተለያዩ ከዉጭ በምናስመጣቸዉ አዳዲስ ላብቶፖች እንታወቃለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://t.me/samcomptech
ቤተሰባዊነት ፣ ተአማኒነት ፣ ገንዘቦቻችን ናቸዉ ! ይምጡ ይሸምቱ!
#Ethiopia

በነዳጅ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወቃል።

ይኸው ክልከላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣ እና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር ' ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ ' በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እያተጓጎለ እንደሆነ ጠቁሟል ኮሚሽኑ።

ኮሚሽኑ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንድሂህ ብሏል ፦

- በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡

- ለማንኛውም አይነት አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡

- በግብርና ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ፣ በሆልቲካልቸር ፣በቱሪዝም ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው።

- በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል።


#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
" ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን ! " - ጆ ባይደን

በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲያቸውን ወክለው ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የጤናቸው ነገር አሳሳቢ ነው እየተባለ ነው።

" እርጅናም ተጫጭኗቸዋል፣ በትልልቅ መድረኮች የሚነገሯቸውን ነገሮች እየሳቱ ነው ፤ ስለዚህ ምክትላቸው ይተኳቸውና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከሩ " የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ባይደን ግን ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ ፥
- ፍጹም ጤናማ መሆናቸውን ፣
- እንደ ቀድሞው መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሥራቸውን መጨረስ ካልቻሉ ብቻ እንደበቃቸው ምልክት እንደሚሆን፣
- አሁን ላይ ምንም ዓይነት የድካም ምልክት እንደሌላቸው ነው የሚመልሱት።

ትላንት በነበረ አንድ የNATO ፕሮግራም የሚዲያ መግለጫ ላይ ፥  የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ለንግግር ሲጋብዙ " ፕሬዝደንት ፑቲን " ብለው መጥራታቸው በሥፍራው የነበረውን ታዳሚ አስደንግጧል።

ዜሌንስኪም ክው ብለው ቀርተዋል።

ወዲያው ግን ጆ ባይደን ፥ " የፑቱን ነገር አሳስቢ ሆኖብን እዛ ላይ ብዙ ስለቆየሁ ነው ፤ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ " ሲሉ ስህተታቸውን አርመዋል።

ዜሌንስኪ " እኔ እሻላለሁ ! (ከፑቱን ማለታቸው ነው) " ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደንም ፥ " በእርግጥም በደንብ ትሻላለህ " ሲሉ መልሰዋል።

ከዚህ ቀጥሎ በነበረ አንድ መግለጫ ላይ ደግሞ የገዛ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስን " ምክትል ፕሬዝዳንት ትራምፕ " ብለው ሲጠሩ በርካቶች በድንጋጤ ተመልክተዋቸዋል።

በቅርብ ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበረ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ክርክር ወቅት ያሳዩት አቋምም ምርጫውን ለማሸነፍ አጠያያቂ ሆኖ ነበር።

የ81 ዓመቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ግን " ደህና ነኝ ምርጫውንም አሸንፋለሁ " ባይ ናቸው።

ክስተቶቹን የሚያሳይ ቪድዮ ከላይ ተያይዟል።

#BBC
#CNN

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ 85,219  በመንግስት እና በግል ት/ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

#AddisAbabaEducationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የሕዝብድምጽ " ይኸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ በዋናው ከተማ አሶሳ እና በተለያዩ ወረዳዎች መብራት ከጠፋ ወደ 1 ወር እየተጠጋ ነው። መቼ  ነው ችግሩ የሚፈታው ? ማነው የሚነግረን ? ምንም የሰማነው ነገር የለም። ለበርካታ ቀናት ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለናል። ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነው። ተሰቃየን የሚመለከታችሁ አካላት ስለፈጠራችሁ መፍትሄ ስጡን !! ህዝቡ ጨለማ ውስጥ ነው…
#Update

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላለፉት 17 ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።

ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገቡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይም ተደጋጋሚ ስርቆት ስለሚፈፀም የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራውን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር አስታውቋል።

ለቀናት መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ተሳክቷል።

ከቀኑ 9:05 ሰዓት ጀምሮ አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።

" በአንድ አካባቢ የሚፈፀም የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ተፅዕኖው ሰፊ ነው " ያለው መ/ቤቱ " በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል መቋረጥ በግልፅ የታየው ይኸው ነው " ብሏል።

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ለመሰረተ ልማቱ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#EEP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል። ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል። " አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።…
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
#Kenya

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አካል ጉዳተኛ በመምሰል ስትለምን የነበረች ተጠርጣሪ ከእነ ግብረአበሯ መያዟን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቀን እስከ 500 ብር ድረስ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖራት ነው አካል ጉደተኛ በመምሰል ወገቧን በጎማ በማሰር ዊልቸር ላይ በመሆን ስትለምን ትላንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው " #መገናኛ " አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተያዘችው።

ግለሰቧን ከቦታ ወደ ቦታ ሲያንቀሳቅሳት የነበረው ተጠርጣሪም ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ ዊልቸሩን በቀን 35 ብር ተከራይተው ለ8 ወር እንደተጠቀሙና በቀን እስከ 500 መቶ ብር እንደሚያገኙ ከሰጡት ቃል ማወቅ እንደተቻለ ፖሊስ አስረድቷል።

ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖርባቸው ጉዳተኛ በመስምሰል የሚያታልሉ እንዳሉ ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
" በታሪኬ ከታክስ በፊት ከፍተኛውን ትርፍ አግኝቻለሁ " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 135.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንደሆነ እና በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1.17 ትሪሊዮን ብር የተሻገረ መሆኑን ተናግሯል።

የባንኩ የደንበኞች ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አመልክቷል።

የተበላሸ ብድር ክምችቱ 2.6% መደረሱም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ ከ218 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ማቅረቡን ጎልጾ 91% ወይም ብር 198 ቢሊዮን የሚበልጠው ለግሉ ሴክተር የተለቀቀ ብድር እንደሆነ አሳውቋል።

#CBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎን ዲጂታል ቪዛ ካርድ ለማድረግ ቪድዮውን ይመልከቱ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው። የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል። ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና…
#National_Exam

ላለፉት 3 ቀናት በወረቀት እና ኦንላይን ሲሰጥ የቆየው የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

Via @tikvahuniversity
#Sudan

" በ2 ሳምንት ውስጥ ለቃችሁ ውጡ " - የሱዳን ጸጥታ ኃይሎች

የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የውጪ ዜጎች ከዋና ከተማዋ ካርቱም እና በዙሪያ ካሉ አካባቢዎች እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ።

ፖሊስ ባወጣው ማሳሰቢያ ፥ የውጪ ዜጎች ከተባሉት የሱዳን አካባቢዎች ለመውጣት የ2 ሳምንት ጊዜ ብቻ ነው የተሰጣቸው።

የሱዳን በመንግሥት ወታደሮች እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገቡ በርካታ ወራት አልፈዋል።

ውጊያ አሁን ድረስ ተጠናክሮ በመቀጠሉ የውጪ ዜጎች ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ አካባቢውን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው ነው ፖሊስ ያሳሰበው።

በሌላ በኩል ፥ ' በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ውስጥ የሌላ ሀገር ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አሉ ' በሚል በመገናኛ ብዙሃን መዘገቡን ተከትሎ በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በመጡ የውጪ ዜጎች ላይ ጥላቻ ይስተዋላል።

ከቀናት በፊት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ከ150 በላይ የውጪ ዜጎች መታሰራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

#DW
#Reuters
#SudanMilitary
#RSF

@tikvahethiopia
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እኛ በሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ነን። ይኸው ሱዳን ውስጥ ስቃያችንን እያየን ነው።

በተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን ተሰብስበው እንዲታሰሩ እና ሜዳ ላይ እንዲጣሉ ሆኗል።

ለአመታት በኖርንበት ሀገር ምንም በማናውቅበት ሁኔታ ሰብሰው አስረውናል።

30 እና 40 ዓመት በላይ የኖሩ ጭምር ታስረዋል። ምክንያት ስንጠይቅ ' ከላይ ነው ትዕዛዙ ' ይሉናል። ሰዎቹ የሌ/ጄነራል አልቡርሃን ናቸው።

ጭራሽ ' ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF ለሚባለው) መረጃ  ትሰጣላችሁ ' የሚል ነገር ያወራሉ የጄነራሉ ሰዎች።

እስካሁን ያለው የታሳሪ ብዛት ከ600 በላይ ይሆናል። 

ህጻናት እና ሴቶች በብዛት አሉ ፣ ነፍሰጡሮች ፣ አዛውንቶች፣ ህመም ያለባቸው ሰዎችም አሉ።

ምቹ ባልሆነ ስፍራ ፣ በየሜዳው ነው ያለነው ፤ ከሙቀቱ ተደምሮ እጅግ ስቃያችንን እያየን ነው።  ራሳቸውን ስተው የነበሩ ሴቶችም አሉ። ወደ ህክምና ተብሎ ከተወሰዱ በኃሏ የት እንደደረሱ አይታወቅም።

' እዚህ መኖር አትችሉም ' ከተባልን የለፋንበትን ንብረት ይዘን ወደ ሀገራችን እንዲመልሱን ይደረግ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጩኸታችንን ይስማንና ካለንበት ስቃይ ያሶጣን።
" - በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

#TikvahEthiopiaSUDAN

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ…
#AddisAbaba

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል !

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሠጡት ቃል ፦

“ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ተለቋል። የማለፊያ ውጤት ወስነን ቆርጠን ይፋ አድርገናል።

ወንድም ሴትም 50ና ከዚያ በላይ ያመጡ ናቸው ወደ ሚቀጥለው ክፍል የሚያልፉት። የአካል ጉዳተኞች ማለፊያ ነጥብ 45 እና ከዚያ በላይ ነው።

78 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞቻችን አልፈዋል።

የ6ኛ ክፍል ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል። ”


የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መመልከቻ : https://aa.ministry.et/account#/student-result
(መለያ ቁጥርና ስም ያስገቡ)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ህዝቡ በጣም ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ፣ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ነው " - ወንድማቸው የተገደለባቸው ነዋሪ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳና አካባቢው ተባብሷል በተባለ የታጣቂ ኃይሎች እገታና ግድያ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።

አቶ አወቀ ሰጠኝ የተቡ የህዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ አሽከርካሪ የሆነው ወንድማቸው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 በስራ ላይ እያለ በታጣቂዎች ጥቃት መገደሉን አመልክተዋል።

በዕለቱ 18 ሰዎች አሳፍሮ ከጎንደር ተነስቶ መተማ እየተጓዘ ነበር።

' መቃ ' በተባለው ቦታ ላይ ነው ታጣቂዎች ጥይት ተኩሰው እሱን ጨምሮ 3 ሰዎች ሲገደሉ 14 ሰዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል።

ረዳቱ ሩጦ ማምለጡን አቶ አወቀ አስረድተዋል።

ሌላ ከኋላ የመጣ አንድ መኪናም ሰው ባይገደልም አስወርደው እንደሄዱ ጠቁመዋል።

" ሁል ጊዜ ግድያ፣ ሁል ጊዜ እገታ፣ ሞት በቃ በጣም የሚያሳዝን ነው ፤ ገላጋይ የሌለበት ሀገር ሆነናል " ሲሉ በሀዘም ስሜት ሆነው ተናግረዋል።

" ህዝቡ ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ፣ የሰው ህይወት የሚጨፈጨፍበት ሰዓትና ጊዜ ላይ ነው ያለን። ምንም የሚያድነን አላገኘንም፣ መንግስትም ሊያድነን አልቻለም " ብለዋል።

መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል አስክሬን ክፍል ውስጥ ሰራተኛ የሆኑት  አቅልለው ገነቱ፥ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ተወስደው ከነበሩት መካከል እንደሆነ የተጠቆመ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ቤተሰቡ ባለመቅረቡ ቀብሩ በማዘጋጃ ቤት መፈጸሙን ተናግረዋል።

አንድ ስሜ አይገለጽብኝ ያሉ የመተማ ወረዳ ነዋሪ ፥ በአካባቢው ግድያ እና እገታ ተባብሶ በመቀጠሉ ስራ ውሎ ወደ ቤት መግባት ፈታኝ እንደሆነ ገልጿል።

" እገታ ብቻ መበራከቱ ሳይሆን ሰዎችም ይገደላሉ " ያለው ይኸው ነዋሪ " የታገተ ሰው ብር የጠየቃል መክፈል የማይል አይመለስም " ሲል ተናግረዋል።

ከሰሞኑም ከመተማ ሆስፒታል አንድ አምፑላንስ ከነሹፌሩ መታገቱን ገልጿል። ለማስለቀቂያ 300 ሺህ መጠየቁን ተከትሎ በየመስሪያ ቤቱ እየተለመነ ነው ብሏል።

እገታ በመስፋፋቱ ነዋሪው፣ ሰራተኛው መንቀሳቀስ እንደቸገረው ጠቁሟል።

" በቃ ከቤት መስሪያ ቤት ከዛ ቤት እንጂ ከቤት መውጣት ከባድ ነው " ብሏል።

አንድ ከጎንደር መተማ የሚሰራ ሹፌር ደግሞ ፤ " ማንኛውም ሰው ወጥቶ ለመግባት ፣ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ለመነገድም ሌላም የቀን ተቀን ስራ ለማከናወን በጣም ተቸግሯል። አስፈሪ ሁኔታ ነው ያለው። መንገዱ በጣም አስጊ ነው " ሲል ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

#AmharaRegion
#VOAAmh.
#Metema

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ከሰጡት ቃል ፦ " በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ…
#Update (No.7)

• “ እኔ 50 ሺህ፣ ጓደኛዬ 30ዐ ሺህ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃዩ ነው ” - ከእገታ የተለቀቀ ተማሪ

• “ እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል ” - የታጋች ተማሪ ወንድም


ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰብ እየተመለሱ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ 10 ቀናት አስቆጥረዋል።

ስለታጋቾቹ ዛሬስ ምን አዲስ ነገር አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ገንዘብ ከፍሎ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ እና የታጋች ቤተሰቦችን ስለጉዳዩ ጠይቋል።

አንድ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈቀደ ከእገታው የተለቀቀ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ እኔ 50 ሺህ ፣ ጓደኛዬ 300 ሺ ብር ከፍለን ተለቀናል። በርካታ ተማሪዎች እየተሰቃሉ ነው ” ብሏል።

ከታጋቾች መካከል 36 የሚሆኑት ከኦሮሚያ  ሲሆኑ 28ቱ በነጻ ሲለቀቁ ሌሎች 9ኙ ግን እዛው እደታገቱ ናቸው ፤ ከአማራ እና ደቡብ የሆኑም እንዳልተለቀቁ ገልጿል።

‘ ታጋቾች ተለቀዋል፣ 7 ታጋቾች ናቸው ያልተለቀቁት ’ የሚባለው ዜና ውሸት መሆኑን ገልጾ፣ ከገርበ ጉራቻ በእግር የ1 ሰዓት የእግር መንገድ ከሚወስድ ጫካ አሁንም ከ60 በላይ ታጋቾች እንዳሉ መመልከቱን ተናግሯል።

የአይን እማኙ፥ “ ያሳለፍኩትን ከባድ መከራ በቃላት አልገልጸውም ” ያለ ሲሆን ታጋቾቹ በምግብ እጦትና በብርድ እየተሰቃዩ በመሆናቸው መንግስትም እንዲደርስላቸው አሳስቧል።

“ ቤተሰቦቼ ድሃ ናቸው ብዬ አልቅሼ ነው የለቀቁኝ ። ጓደኛዬ 300 ሺህ ብር ባይከፍል ግን አይለቁኝም ነበር ” ብሏል።

አንድ የታጋች ወንድም በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ “ ' ልጆች ተለቀዋል ' ይባላል ፤ በርካታ ወላጆች ግን ልጆቻቸው በእገታ ላይ ናቸው። ደውለን እየጠየቅን ነው። እኛም 700 ሺህ ላኩ ተብለናል። ግን ገንዘብ የለንም !! ” ብለዋል።

ሌላኛዋ የታጋች እህት በበኩሏ ፣ ታጋች እህቷ እስከ 3 ቀናት 40ዐ ሺህ ብር ላኪ እንደተባለች፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ግን ማግኘት እንዳልቻለ ገልጻላች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚሁ ጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን፣ ሰላምና ጸጥታ ቢሮዎች ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም። 

በተጨማሪም፣ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ አቅርበናል።

የአገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ ፥ " በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከሰጠው ወጪ የተለየ ነገር የለኝም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ፣ ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ በ ' ሸኔ ቡድን ታግተው ተወሰዱ ' ካላቸው 167 ታጋቾች መካከል የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ኦፕሬሽን 160ዎቹ ከእገታ መለቀቃቸውን 7 ታጋቾች ብቻ እንደቀሩ አሳውቆ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia