TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ " - ነዋሪ

በአዳማ ከተማ ፤ በቦኩ ሸነን ክፍለ ከተማ ሀሮሬቲ ወረዳ እና ቶርበን ኦቦ ወረዳ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የሰው ሕይወት ማለፉና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ለመስማት ችለናል።

በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀሰቀሰ ምክንያት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ በወረዳዎቹ የሚገኙ ቤቶችን ሕገ-ወጥ ናቸው በሚል የማፍረስ ሂደት ሊጀምር ሲል መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ይፈርሳሉ ያሏቸውን ቤቶች በቀይ ቀለም " X " እያረጉ እንደነበር እና ዛሬ ለማፍረስ ሲመጡ ነዋሪዎች ተቃውሞ እንዳነሱ ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ መክፈታቸውን አንድ የዐይን እማኝ አስረድተዋል።

ቦታዎቹ ላለፉት ዓመታት ግብር ሲከፈልባቸው የነበሩ እንደሆኑም ጠቁመዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢው ነዋሪ እንዳሉት " በተቀሰቀሰው ግጭት እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ። በዛ አከባቢ ከሰዓት በኋላ እንቅሰቃሴ አልነበረም። ሁሉም ሰው በቤቱ ውስጥ ተቀምጧል እና በአጠቃላይ ያለውን ነገር ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያገኘናቸው ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ የያዙ በርካታ ሰዎች ተቃውሞቸውን ለማሰማት መንገድ በመዝጋት እና " ፈረሳው ይቁም !! " የሚሉ መፈክሮች እየሰሙ እንደነበር ነው።

በሌላ አንድ ቪዲዮ ላይ ነዋሪዎቹ በዱላ እንዲሁም በድንጋይ መንገድ ዘግተው እንደነበር ተመልክተናል።

ነዋሪው ተቃውሞውን ማሰማት በጀመረበት ወቅት ተኩስ መጀመሩና በሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች ሲበታተኑም ተመልክተናል።

በዚህ ውስጥ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዐይን እማኞች መስማት የቻለን ቢሆንም ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ ማረጋገጥ አልተቻለም።

ከከተማው አመራርና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAdama

@tikvahethiopia