TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
ዶላር ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው።

ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል።

ፓውንድ ስተርሊንግንም እጅግ ከፍ ባለ ዋጋ በ110 ብር ከ6446 ሳንቲም ገዝቼ በ116 ብር ከ1768 ሳንቲም እሸጣለሁኝ ብሏል።

ዩሮንም ቢሆን ጨመር አድርጌ በ97 ብር ከ5882 ሳንቲም እገዛለሁ፤ መሸጫዬ ደግሞ 102 ብር ከ4776 ሳንቲም ነው ብሏል።

የUAE ድርሃም የዛሬው መግዣዬ 22 ብር ከ1751 ሳንቲም ነው ፤ መሸጫዬ 23 ብር ከ2837 ነው ሲል አውጇል።

ዛሬ ከግል ባንኮች ቀደም ብሎ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ያሳወቀው አዋሽ ባንክ ነው።

ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም አንዱን የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሳንቲም ነው ብሏል።

ዩሮም መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም አንዱ ድርሃም በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶላር ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው። ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል። ፓውንድ ስተርሊንግንም እጅግ ከፍ ባለ ዋጋ በ110 ብር ከ6446 ሳንቲም ገዝቼ በ116 ብር ከ1768 ሳንቲም እሸጣለሁኝ ብሏል። ዩሮንም ቢሆን ጨመር አድርጌ በ97 ብር ከ5882 ሳንቲም እገዛለሁ፤ መሸጫዬ ደግሞ 102 ብር ከ4776…
#Ethiopia

ሁሉም የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ወደላይ እየተተኮሰ ነው። በባንኮች መካከል ያለው ፉክክርም እየተጧጧፈ ነው።

የግል ባንኮች የዛሬ ዕለታዊ ምዛሬ ዋጋ እያሳወቁ ናቸው።

የውጭ ምንዛሬ ዋጋቸውን በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛሉ።

ዶላር እንደሆነ ወደ 100 እየተጠጋ መጥቷል።

ከሁሉ በላይ ግን ፓውንድ ስተርሊንግ  እና ዩሮ እጅግ ነው የጨመረው። በመቶ ቤቶች መጫወት ጀምረዋል።

እስቲ ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይዘው የወጡ ባንኮችን እንመልከት።

ኦሮሚያ ባንክ ፥ ዶላር በ90 ብር ከ6055 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ6827 ሳንቲም እየሸጣለሁ ብሏል።

ፓውንድ ስተርሊግ በ116 ብር ከ4282 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 121 ብር ከ6673 ሳንቲም እየሸጣለሁ ብሏል።

ዩሮንም ቢሆን በ98 ብር ከ0804 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 102 ብር ከ4940 ሳንቲም እየሸጣለሁ ሲል ቆርጧል።

የUAE ድርሃም በ24 ብር ከ6666 ሳንቲም እየገዛሁ በ25 ብር ከ7766 ሳንቲም እሸጣለሁ ብሏል።

ዳሸን ባንክ ፥ ዶላር መግዣዬ 90 ብር ከ7899 ሳንቲም ነው ፤ ምሸጠው 98 ብር 0511 ሳንቲም ነው ብሏል።

ፓውንድ ደግሞ በ111 ብር ከ6146 ሳንቲም እየገዛሁ በ120 ብር 5437 ሳንቲም እሸጣለሁ ሲል አሳውቋል።

ዩሮን በ98 ብር 4436 ሳንቲም እገዛለሁ ፤ በ106 ብር ከ3191 እገዛለሁ ብሏል።

ድርሃም ይዞ ለሚመጣ መግዣው 22 ብር ከ3694 ሳንቲም ነው ፤ መሸጫ 24 ብር ከ1589 ሳንቲም ነው ብሏል።

አቢሲንያ ባንክ የአንድ ዶላር መግዣው 90 ብር ከ0690 ሳንቲም ፤ መሸጫው 93 ብር ከ2214 ሳንቲም እንደሆነ አሳውቋል።

ፓውንድ 109 ብር ከ3495 ሳንቲም መግዣው ፣ 113 ብር ከ1768 ሳንቲም መሸጫው እንደሆነ ገልጿል።

ዩሮ 97 ብር ከ1394 ሳንቲም እየገዛ በ100 ብር 5393 ሳንቲም እንደሚሸጥ አመልክቷል።

የሌሎችም የግል ባንኮች የዕለቱ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የደመወዝ_ጭማሪ " ታች ላለው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ መንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ምን ተባለ ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት…
#Update

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በቅርቡ እንደሚጸድቅ የገንዝብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

" ለታችኛው የደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛ የተሻለ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚያችል ጭማሪ ተሰርቷል " ብለዋል።

ዝርዝሩ በቅርብ ይጸድቃል ሲሉም አሳውቀዋል።

ከዓለም አቀፍ ተቋማት ከተገኘው ድጋፍ ውስጥም አንዱ የሚውለው ለሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ / በድጎማ መልኩ እንደሆነ አመልክተዋል።

ትላንትና በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ እንዳለው በመግለፅ ጭማሪ እንደሚደረግ ተናግረው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኑ የደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት እንደጠየቀና ፤ ከታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግሥት ሠራተኛ 300% ደመወዙ እንደሚጨመር በይፋ መናገራቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ዶላር በቀናት ውስጥ ምን ያህል ጨመረ ?

የውጭ ምንዛሬው በገበያ ይመራል ወይም floating exchange rate ተግባራዊ ይደረጋል ከመባሉ 3 ቀን በፊት የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 57 ብር ከ4838 ሳንቲም ፤ መሸጫ ዋጋው 58 ብር ከ6335 ሳንቲም ነበር።

ሰኞ መግዣ 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ፤ መሸጫ 76 ብር ከ2311 ሳንቲም

ማክሰኞ መግዣው 74 ብር ከ7364 ሳንቲም ፤ መሸጫ 76 ብር ከ2311 ሳንቲም

ረቡዕ
#ጥዋት መግዣ 77 ብር ከ1280 ሳንቲም ፤ መሸጫ 78 ብር ከ6706 ሳንቲም // #ከሰዓት ፦ መግዣ 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫ 81 ብር ከ6207 ሳንቲም

ሐሙስ መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫ 81 ብር ከ6207 ሳንቲም

አርብ መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫ 85 ብር ከ6201 ሳንቲም

ይህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሲሆን ዛሬ ላይ በግል ባንኮች አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣ ዋጋው ከ90 ብር አልፏል ፤ መሸጫውም ከ94 ብር ተሻግሯል።

አጠቃላይ ዶላር ከብር ጋር ያለው ልዩነት እጅግ እየሰፋ ሲሆን አንዱ ዶላር ወደ መቶ እየተጠጋ ነው።

የሌሎች ምንዛሬ ዋጋም እጅግ በፍጥነት እየተተኮሰ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም ጨምሯል።…
#Update

ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም እጅግ በጣም ጨምሯል። መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ23 ብር ከ3201 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ24 ብር ከ7194 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዶላር መሸጫው ከ100 ብር አለፈ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ ቅዳሜ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል። በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው 101 ብር ከ4347 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል። ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 116 ብር ከ6881 ሳንቲም ፤ መሸጫው 123 ብር ከ6894 ሆኖ ይውላል ብሏል። ዩሮም እጅግ በጣም…
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።

ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር።

ነገ ማለትም
#ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው።

ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት ዩሮ ነው ዛሬ 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መግዣ ፤ መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም ሆነ ነበር የዋለው።

በነገው ምንዛሬ ግን የአንዱ ዩሮ መግዣው 104 ብር ከ4107 ሳንቲም ፤ መሸጫው 110 ብር ከ6754 ሳንቲም ሆኖ ይውላል።

ብዙም የምይነገርለት
#የኩዌይት_ዳናር ደግሞ የአንዱ መሸጫ ከ315 ብር አልፏል።

በነገ ምንዛሬ አንዱ ዲናር በ298 ብር ከ8463 ሳንቲም እየተገዛ በ316 ብር ከ7771 ሳንቲም ይሸጣል ተብሏል።

ይህ መረጃ በ ' ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ' ያለውን ምንዛሬ የሚያሳይ ሲሆን የግል ባንኮች ደግሞ ምን ይዘው እንደሚመጡ ጥዋት ይታያል።

#TikvahEthiopia #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : በዛሬውና ነገ በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል። ዛሬ የነበረው መግዣ 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም ነበር። ነገ ማለትም #ቅዳሜ ሐምሌ 27 የሚውለው የምንዛሬ ዋጋ መግዣው 95 ብር ከ6931 ሳንቲም ፤ መሸጫው ደግሞ 101 ብር ከ4347 ሳንቲም ነው። ሌላው በጣም ልዩነት የታየበት…
#DailyExchangeRate

ዛሬግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።

ከላይ የ7 የግል ባንኮች ዕለታዊ ምዛሬ ቀርቧል።

ከነዚህ ባንኮች 3ቱ ማለትም ኦሮሚያ፣ አባይ ፣ ዳሽን የዶላር መግዣቸውን በ90 ብር አድርገው በሳንቲም ይለያያሉ መሸጫቸው ግን ልዩነት አለው።

ኦሮሚያ የዶላር መግዣው 102 ብር ከ3848 ሳንቲም ነው ፤ ሲሆን በአባይ 102 ብር ከ9560 ሳንቲም ፤ በዳሽን ደግሞ 100 ብር ከ7768 መሸጫው ነው።

ሌሎቹ ባንኮች አቢሲንያ፣ አዋሽ ፣ ሲዳማና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኮች መሸጫቸውም መግዣቸውም ይለያያል።

አቢሲንያ ዛሬ ሁለት (ጥዋት እና ከሰዓት) የዶላር ምንዛሬ ነው የተጠቀመው ።

ጥዋት ላይ በ90 ብር ከ0690 ሳንቲም መግዣ መሸጫ ደግሞ 106 ብር ከ7318 ሳንቲም ነበር ፤ አሁን ይፋ ባደረገው የከሰዓት ምንዛሬ ግን መግዣውን ወደ 96 ብር ከ3738 ሳንቲም መሸጫውን 107 ብር ከ9387 ሳንቲም አሳድጎታል።

አዋሽ ዶላር መግዣው 96 ብር ከ3011 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 106 ብር ከ8941  ሳንቲም ነው። ሲዳማ በ96 ብር ከ6500 ገዝቶ በ106 ብር ከ3110 ሳንቲም እንደሚሸጥ ገልጿል። ኦሮሚያ ህብረት ስራ በበኩሉ መፍዣው 97 ብር ከ7329 ሳንቲም ሲሆን መሸጫው 107 ብር ከ5062 ሳንቲም ነው።

ከዶላር ውጭ ያሉ ምንዛሬዎችም በግል ባንኮች ዋጋቸው ጨምሯል። ዝርዝሩን ከላይ ይመልከቱ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

° " በርካታ መሰረታዊ ሸቀጥ የያዙ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ጣቢያዎች ተንቀሳቅሰዋል " - መንግሥት

° " የዋጋ ጭማሪ ቁጥጥር የአንድ ሰሞን ወሬና ወከና ሆኖ በዛው ጨምሮ እንዳይቀር ተከታተሉልን ፤ከዚህ ቀደም በዘይት የሆነውን አይተናል። ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም " - የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ
(ከአ/አ)

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ተደረገ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ በሚባሉ ሸቀጦች ላይ ጭማሪ፣ እንዲሁም " የለም " የማለት ነገር እያጋጠማቸው እንደሆነ ዜጎች ተናግረዋል።

ይህም ሁኔታ እያማረራቸው እንደሆነ ያመለክታሉ።

በተለይም አንዳንድ ምርቶችን ለመግዛት ሲሄዱ ከፍ ያለ ብር ተጨምሮ እንደሚነገራቸው ፤ ከዚህ ባልፈ ደግሞ " አሁን ምርት የለም " እየተባሉ እንደሚጉላሉ በምሬት ይናገራሉ።

መንግሥት በበኩሉ ገበያው እንዳይናጋ የቁጥጥር ስራ እየሰራ እንደሆነ እየገለጸ ነው።

ዋጋ ጨምረው የተገኙ በርካታ ሱቆችን ከማሸግ በተጨማሪ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠረ ሸቀጥ በገፍ እንዲገባ እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ እያሳወቀ ይገኛል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማሻሻያው ምክንያት የገበያ መናጋት እንዳይፈጠር እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ገልጿል።

ለአብነት በጉምሩክ ጣቢያዎች መሰረታዊ ሸቀጥ ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች እንዲወጡ መፍትሄ እየተሰጠ እንደሆነ አመልክቷል።

በተለይ ገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባወጣው የቫት ክፍያ ምክንያት ቆመው የሚገኙትን እንዲንቀሳቀሱ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት ፦
➡️ 101 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 44,000 ሌትር ዘይት የያዙ ፤
➡️ 80 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 32,000 ኩንታል ስኳር የጫኑ
➡️ 23 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 9,200 ኩንታል ሩዝ የጫኑ
➡️ 69 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው 27,600 ኩንታል የስንዴ ዱቄት የጫኑ በጥቅሉ 273 ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው የጉምሩክ ስነስርዓት ጨርሰው ወደ መዳረሻቸው እንደተንቀሳቀሱ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በነገው እለትም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሰረታዊ ሸቀጥ ከጉምሩክ ጣቢያዎች ወደ መላው ሀገሪቱ አከባቢዎች እንደሚጓጓዝም አሳውቀዋል።

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች " ዶላር ጨምሯል " በሚል በተለይ መሰረታዊ ምርቶች ላይ የሚታየው ጭማሪ ዜጎችን እያማረረ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

በተለይ እንደ ዘይት፣ ስኳር፣ ያሉት ምርቶችን አንዳንድ ቦታ ማግኘት እንደማይቻል ሲገኝ ደግሞ ዋጋው ጨምሮ ነው ለሸማች የሚነገረው።

ቃላቸውን የሰጡን የ4 ልጆች እናት ሰራተኛ ፥ " እኔ ደመወዜ አንድም ጊዜ ሳይጨምር ይኸው ዘይት ጨምሮ ጨምሮ በሺህ ቤት ገብቷል። እንዴት መኖር እንዳለብኝ አልገባኝም። ደመወዘኔ ምኑን ከምኑ እንደማደረገውም ጠፍቶብኛል " ሲሉ በሀዘን ተናግረዋል።

" የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር የሚጨምረው ዋጋ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ወሬና ወከባ ይሆንና ዋጋው በዛው ጨምሮ ጣራ ነክቶ ይቀራል ፤ ይህ ከዚህ በፊት በዘይት አይተነዋል " ብለዋል።

" ነጋዴው አያዝንልን፣ የመንግስት ሰዎች ተገቢና ዘላቂ ቁጥጥር አያደርጉልን፣ መፍትሄ አይሰጡን፣ የሚመጣው ሁሉ ግን እኛ ላይ ያርፋል። እንደ ከዚህ ቀደሙ ዋጋ ጨመረ ተብሎ ቁጥጥሩ የአንድ ሰሞን ግርግር ሆኖ በዛው ዋጋው ተሰቅሎ እንዳይቀር መደረግ ያለበት ይደረግ፤ ኑሮው በጣም ከብዶናል። " ሲሉ አክለዋል።

#Tikvahethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

(ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም)

በኢትዮያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬ ከቅዳሜው ምንዛሬ ዋጋ የተለየ ነገር የለም።

የአሜሪካ ዶላር መግዣው 95.6931 ፤ መሸጫው 101.4347 ሆኖ ዛሬ ቀጥሏል።

የሌሎች ውጭ ምንዛሬዎች ላይም በቅዳሜው ነው የቀጠለው።

በግል ባንኮች ግን ፉክክሩ ደርቷል።

ለአብነት (
#CASH)፦

አቢሲንያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.2288 ፤ መሸጫው 113.2585
💷 ፓውንድ መግዣው 122.2153 ፤ መሸጫው 138.1033
💶 ዩሮ መግዣው 109.3596 ፤ መሸጫው 123.5763

➡️ ወጋገን ባንክ

💵 ዶላር 101.6434 መግዣ ፤ መሸጫው 113.8406
💷 ፓውንድ መግዣ 130.1137 ፤  መሸጫ 145.7273
💶 ዩሮ መግዣ 110.9031 ፤ መሸጫው 124. 2115

➡️ ዳሸን ባንክ

💵 ዶለር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 112.0271
💷 ፓውንድ መግዣ 124.0748 ፤ መሸጫ 137.7230
💶ዩሮ መግዣው 109.4334 ፤ መሸጫው 121.4711
🇸🇦የሳውዲ ሪያል 24.3462 መግዣው ፤ መሸጫው 27.0243
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው በ24.8666፤ መሸጫው 27.6019

➡️ ንብ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0959 ፤ መሸጫው 111.2055
💷 ፓውንድ መግዣው 129.3521 ፤ መሸጫው 142.2874
💶ዩሮ መግዣው 110.3056 ፤ መሸጫው 121.3362
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው 27.5263 ፤ መሸጫው 30.2789
🇸🇦የሳዑዲ ሪያል መግዣው 26.9446 ፤ መሸጫው 29.6390

➡️ ኦሮሚያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.8445 ፤ መሸጫው 113.9543
💷 ፓውንድ መግዣው 128.5263 ፤ መሸጫው 145.2347
💶 ዩሮ መግዣው 108.8012 ፤ መሸጫው 122.9453
🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 329.8724 ፤ መሸጫው 372.7558

ፀደይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0348 ፤ መሸጫው 111.1383
💷 ፓውንድ መግዣው 123.2017 ፤ መሸጫው 135.5219
💶 ዩሮ መግዣው 110.2390 ፤ መሸጫው 121.2629

ብርሃን ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 96.1716 ፤ መሸጫው 110.5973
💷 ፓውንድ መግዣው 118.2188 ፤ መሸጫው 135.9516
💶 ዩሮ መግዣው 104.2746 ፤ መሸጫው 119.9158

ቡና ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0000 ፤ መሸጫው 113.6250
💷 ፓውንድ መግዣው 125.8698 ፤ መሸጫው 138.4568
💶 ዩሮ መግዣው 106.5545 ፤ መሸጫው 117.2100

ፀሐይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 115.0548
💷 ፓውንድ መግዣው 130.1137 ፤ መሸጫው 146.3779
💶 ዩሮ መግዣው 112.5666 ፤ መሸጫው 126.6375

#Floatingexchangerate #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብር ለኢትዮጵያ የ800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። @tikvahethiopia
#TsigeDuguma

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በ800 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ለሀገሯ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ፅጌ ዱጉማ ከውድድሩ በኃላ " JESUS IS LORD ! " የሚል ጽሁፍ አሳይታለች።

ፅጌ ስሟ ተጽፎ ደረቷ ላይ ከተለጠፈበት ወረቀት የጀርባ ክፍል ላይ ነው ይህን መልዕክት ፅፋ ገብታ ያስተላለፈችው።

የዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት በክርስቲያኖች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethsport