TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewTariff📈

" የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ይቀርባል " - የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያዘጋጁትን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በመገምገም በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ እንደሚያቀርበው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ታሪፍን በማሻሻል ላይ ያተኮረ ስብሰባ ዛሬ ተደርጎ ነበር።

በዚህም ስብሰባ ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት መከለስ የነበረበት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ያለ ማሻሻያ በመቆየቱ ተቋማቱን ለኪሳራ እንደዳረገ እና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና ማሳደሩ ተነግሯል።

" ለዚህም የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ተብሏል።

ሁለቱ ተቋማት በተናጥል እና በጋራ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ላይ ጥናት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በሌላ አማካሪ ድርጅት ተገምግሞ ማሻሻያው ወደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መቅረቡ ተጠቁሟል።

ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ኃይል ለማመንጨትና ለማሰራጨት የተሰጣቸው ባለፍቃድ መስሪያ ቤቶች ያቀረቡትን የታሪፍ ማሻሻያ ፕሮፖዛል ገምግሞ የውሳኔ ሃሳቡን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ የማጸደቅ ኃላፊነት አለበት።

በነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አህመድ ሰኢድ ሁለቱ ተቋማት ጥናት በማድረግ ያቀረቡትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አህመድ ሰኢድ ምን አሉ ?

" መንግስት በሰጠን ስልጣን መሰረት መመሪያ አለን። እነዛን መመሪያዎች ተከትለው ነው ወይ ታሪፉን ያወጡት ? ለምሳሌ ታሪፍ ከጨመረ ገቢ ይጨምራል። ያን ታሳቢ በማድረግ አላስፈላጊ ወጪዎችን ጨምረው ከሆነ እኛ ነን የምንቆጣጠራቸው " ብለዋል።

በተጨማሪ ሁሉቱ ተቋማት ያስጠኑትን የታሪፍ ተመን በባለስልጣኑ መመሪያ መሰረት እንደተሰራ እንደሚገመገም ገልጸው " በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክርቤት ለውሳኔ ይቀርባል ሲሉ " ተናግረዋል።

የታሪፍ ማሻሻያው አሁን ያለውን ታሪፍ በምን ያህል ይጨምራል ? የሚለውን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አንዱአለም ሲአ " አሁን ላይ እዚህ ላይ ይደርሳል ለማለት አይቻልም " ብለዋል።

" ባለስልጣኑ ነው ቁጥሩን መጨረሻ ላይ አይቶ መርምሮ ለሚኒስትሮች ምክር  ቤት አስገብቶ የሚያፀድቀው " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia