TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ #ቴፒ ግቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ የዓመቱን የትምህርት መርሀ ግብር ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቴፒ የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
TIKVAH-ETHIOPIA
የቴፒ ነገር... TIKVAH-ETHIOPIA ከቴፒ ከተማ ነዋሪ ቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እያስተናገደ ነው። ከተማይቱ አይሁንም ቢሆን አስተማማኝ ደህንነት የላትም፤ መንግስት ኃይሉን አጠናክሮ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል። በተለይም የከተማው መግቢያና መውጫዎች ላይ ከፍተኛ ወንጀሎች እንድሚፈፁ ገልፀዋል። "ከቴፒ ነው የምጽፍላቹ! N ነኝ ቴፒ ነዋሪ ነኚ ቴፒ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር አለ።…
#ቴፒ

"ከቴፒ የጻፍኩላቹ የናንተው ቤተሠብ ነኝ። ለ8 ቀን ተዘግቶ የነበረው የቴፓ መናህሪያ በመከላከያዎች ጥረትና አወያይነት ዛሬ ለመንገደኞች ክፍት ሁኖ እኛም መከላከያ ጫካውን አጅቦን ሸኚቶን ከቴፒ #ሚዛን ገብተናል መንገደኞችም ዛሬ ማንም ሣይዘረፍ ወደሚዛን ገብተናል! እድሜ ለፌደራልና ለመከላከያዋቹ ሁሉንም አመሥግኑልን የናንተው ቤተሠብ ከሚዛን ቴፒ!"

እኛ ደግሞ ይህን እንላለን...

የኢትዮጵያ መንግስት ለአካባቢው #ልዩ_ትኩረት ሰጥቶ ችግሮች በዘላቂነት የሚፈቱበትን መንገድ መፈለግ አለበት፤ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ላይ #ደህንነታቸው ተጠብቆ እንደልባቸው ወጥተው የሚገቡበትና ስራቸውን ያለእክል የሚሰሩበትን ሁኔታ መፍጠር ትልቁ የመንግስት ስራ በመሆኑ በተቻለ አቅምና ፍጥነት ይህን ማድረግ ይኖርበታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሸካ ዞን መቀመጫ ቴፒ እንዲሆን ተወሰነ።

ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም የሸካ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና መቀመጫ #ቴፒ_ከተማ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወሰኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ባካሄደው 9ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የአሠራር ቅልጥፍናና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የዞኑን ዋና ከተማ ከነበረበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ ለማዛወር የቀረበውን የውሣኔ አጀንዳ በመወያየት የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ውሳኔው በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት ህገ መንግስት አንቀፅ 81 ንኡስ አንቀፅ 2 ላይ የዞን ምክር ቤቶች በዞኑ ውስጥ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው ተብሎ በተገለፀው መሠረት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ካለው ህዝባዊ ጠቀሜታ እና ፋይዳ አንጻር የዞኑ ማዕከል አሁን ካለበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ እንዲዛወር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።

መረጃው የደረሰን ከሸካ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ቴፒ #አሽከርካሪዎች

° “ ከቴፒ ቡና ጭነን ለመውጣት ተከልክለን ከቆምን ወር ሊሞላን ነው ” - አሽከርካሪዎች

° “ ክልል ኮሚቴ አቋቁቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ”- ቡናና ሻይ ባለስልጣን

የጫኑትን ቡና ይዘው እንዳይንቀሳቀሱ በመከልላቸው ያለምንም መፍትሄ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለመቆም እንደተገደዱ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

“ ለሥራ የምንወጣው ቤተሰቦቻችንንም ለማስተዳደር ነው ” ያሉት አሽከርካሪዎቹ፣ “ ሥራ ፈትተን የቆምንበት ጊዜ ቀላል አይደለም። እንኳን ቤተሰብ ልናስተዳድር ለእኛም ለእለት ለምግብ ገንዘብ ተቸግረናል ” ብለዋል።

“ የተከለከልንበትን ምክንያት እንኳን #አላወቅንም። መንግስት ግን አሽከርካሪዎች እያስተናገዱት ላለው ተደራራቢ ችግር መፈትሄ የማይሰጠው እስከመቼ ነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

አንዳንዶቹ በወባ ተይዘው መተኛታቸውንም ለመስማት ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አሽከርካሪዎቹ ጉዳዩን በተመለከተ ይጠየቅልን ያሉት ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ችግር ለምን ተፈጠረ? ችግሩን ለመቅረፍስ ምን እየተሰራ ነው? ሲል ተይቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፋ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር፣ “ ቡና በአገር ኢኮኖሚ፣ የአገር ሀብት ነው። ይቺ ቡና ከሌለች አገርም የለችም ማለት ይቻላል። 40 በመቶ ገደማ ቡና ነው ይዞ ያለው ” የሚል ቃል ሰጥተዋል።

“ ግን ቴፒ ላይ እያደረጉ ያሉት የExport ቡናን በአፈር እያሹ፣ በውሃ እያሹ ወደ Local መልሰው ቡናው ለExport እንዳይሆን እያደረጉ ነው፤ አቅራቢዎቹ ” ብለዋል።

“ ጅምላ ነጋዴዎቹ ይሄ ቡና በውሃና በአፈር ታሸ እንጂ ንጹህ ስለሆነ ጥሩ ያወጣላቸዋል። ለመሸጥ ነው የሚፈልጉት ” ያሉት አቶ ሻፊ፣ “ ለዚህ ደግሞ ብዙ ጊዜ መመሪያ አውጥተን ችግሩ እንዲቆም ብዙ ጊዜ ተናግረን ሳይፈታ ቀረ ” ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለው፣ “ ይህ ብቻ ሳይሆን በአፈር የታሸ ቡናም መጋዚን ውስጥ አከማችተዋል። ይህ አገር ማጥፋት፤ አገርን ገቢ ማሻጣት ነው ” ብለዋል።

“ ላለፉት ስድስት (6) ወራት ቴፒ ብቻ ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ድረስ 34 በመቶ ንጹህ ቡና Local ነው የወጣው። ስለዚህ ምንም Local የማውጣት መብት የላቸውም። የሚያወጣው ማዘጋጃና ማከማቻም በአካባቢው የለም ” ነው ያሉት።

መፍትሄውን በተመለከተ ፤ “ አሁን ላይ ጉዳዩን ለክልል ሰጥተናል። ክልል ኮሚቴ አቋቁሞ ነገሩን እያጣራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህም አሽከርካሪዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የተደረጉት የExport ቡናን ወደ Local በሚለውጡ አቅራቢዎች መሆኑን ያስረዱት አቶ ሻፊ፣ “ እንደዚያ በሚያደርጉት ላይ ባለሙያዎች አጣርተው እርምጃ እንዲወሰድ ኮሚቴ ተቋቁሟል ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia