TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.3K photos
1.42K videos
206 files
3.94K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት በቅርብ ማስተካከያ ይደረጋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፓርላማ አባላት ለተነሱ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው። በዚሁ ወቅት በቅርቡ ፍራንኮ ቫሉታን በሚመለከት ማስተካከያ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ባለፉት ጥቂት ወራት ከሪፎርሙ ጋር ተያይዞ ከወሰናቸው አብሮ ከማይሄዱ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ…
" ሪፎርሙ ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው።

በተለይም ከኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጋር የተያዙ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል።

አንዱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚመለከት ነው።

" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ ሪፎርም በጣም ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ነው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፥ " በህዳሴ ምክንያት ፣ በቦንድ ምክንያት በጣም አስጊ ጉዳይ ውስጥ ከነበሩ ተቋማት አንዱ ንግድ ባንክ ነው " ብለዋል።

" ይሄ ሪፎርም ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባንኩ ያለበትን ዕዳ በቀላሉ ማኔጅ የሚያደርገው አልነበረም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " በዚህ ሪፎርም 900 ቢሊዮን ብር የተራዘመ ቦንድ አግኝቷል ባንኩ በከፍተኛ ደረጃ የነበረበትን ኢሚዴዬት አደጋ መከላከል የሚያስችል ሪሶርስ አግኝቶ ስራ ጀምሯል " ብለዋል።

" ንግድ ባንክ ወደቀ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ 30ውም ባንኮች ወደቁ ማለት ነው። ዋናው የኢትዮጵያ ባንክ ንግድ ባንክ ነው እሱን ማዳን የባንክ ሴክተሩን ማዳን ነው " ሲሉም አክለዋል።

" 900 ቢሊዮን ዶላር የተገኘበት መንገድ ብንነጋገር ብዙ አስደሳች ጉዳዮች ያሉበት ነው ግን አላነሳውም " ብለዋል።

ገንዘቡ የተገኘው ጠቃሚ በሆነ ድርድር እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምን አይነት ድርድር ይህ ሁሉ ገንዘብ እንደተገኘ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሪፎርሙ ባይሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርስ ነበር ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ናቸው። በተለይም ከኢኮኖሚ ሪፎርሙ ጋር የተያዙ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። አንዱ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚመለከት ነው። " የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚህ ሪፎርም በጣም ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ነው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ…
" በባንክ ስም የሚዘርፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

" የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

እነዚህ አካላት " በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ብለዋል።

" ባንኮች ኮሚሽን ስለለመዱ፣ በትክክለኛው ህጋዊ መንገድ ከሚሰራው ይልቅ የትይዩ ማርኬት ውስጥ ተዋናይ መሆን ስለሚጠቅማቸው የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ ፤ እነዚህ በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ሲሉ ነው የተደመጡት።

እነዚህ ላይ ከፍተኛ ክትትል እና እርምጃም ይወሰዳል ሲሉ ተናግረዋል።

" ባንኮች ህግ እና ስርዓት አክብረው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገትን በሚያረጋግጥ መንገድ ሊሰሩ ይገባል እንጂ በባንክ ስም የአራጣ ስራ የሚሰሩ ከሆነ ችግር ነው " ብለዋል።

" ባንክ በህጋዊ መንገድ የሚወዳደሩበት እንጂ በህገወጥ መንገድ በኮሚሽን ሃብት የሚሰበስቡበት መሆን የለበትም " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በባንክ ስም የሚዘርፉ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) " የኢትዮጵያ የፋይናሻል ስርዓት ጤናማ በሆነ መንገድ እንዳያድግ የሚያበላሹ ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። እነዚህ አካላት " በባንክ ስም የሚዘርፉ ናቸው " ብለዋል። " ባንኮች ኮሚሽን ስለለመዱ፣ በትክክለኛው ህጋዊ መንገድ ከሚሰራው ይልቅ የትይዩ ማርኬት ውስጥ…
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች

" ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል።

" አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ ኤምባሲዎች አሉ ስራቸው ይሄ የሆነ " ብለዋል።

" እነሱ ላይ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ ይወሰዳል። ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም እኛ የምንፈልገው ጤናማ ህጋዊ ስርዓት ያለውን መንገድ የሚከተል ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ያን ስራ (ብላክ ማርኬት) የሚሰሩ ነገር እንዳናበላሽ ብለን የታገስናቸው ስራቸው ግን የብላክ ማርኬት የማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " ሲሉ ተናገረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብላክ ማርኬት ላይ የተሰማሩትን ኤምባሲዎች ስማቸውን በግልጽ ከመናገር ተቆጠበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ብላክማርኬት #ኤምባሲዎች " ነገር እንዳናበላሽ ነው የታገስናቸው ስራቸው ብላክ ማርኬት ማሯሯጥ የሆኑ ኤምባሲዎች አሉ " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በስም ያልጠቀሷቸው ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ እንዳሉ ጠቁመዋል። " አንዳንድ ኤምባሲዎች ቀጥ ብለው የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍ እና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ የሚሰሩ…
#ብላክማርኬት #ፍራንኮቫሉታ

የተለያዩ ኩባንያዎች በኩባንያ ስም ፣ በፍራንኮ ቫሉታ ስም ፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

" ሹፌሮች ፣ ትናንሽ ስራ የሚሰሩ ሳይቀሩ የኢትዮጵያ ብላክ ማርኬት ዶላር ወደ አንዳንድ ሀገራት በባቡርና በቅጥቅጥ መኪና ይወጣል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከሀገር ወርቅ ይወጣል ፣ ዶላር ይወጣል ይሄን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል። ህገወጥነት ፣ ኮንትሮባንድ ዘራፊዎች በውስጣችን ያሉ ሰዎች ተጨምረውበት የሚደረግ ማንኛውም ህግ ያልተከተለ ዘረፋ መከላከል አለብን " ብለዋል።

" አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ አሉ ኢትዮጵያ ግን ከብሔራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ ግስላ የሚሆኑ እኛን መዝረፍና የኛን ብሔራዊ ጥቅም አለማክበር ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

" ከእኛ መውሰድ አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል " ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ ሀገራት እነማን እንደሆኑ ግን በስም አልገለጹም።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ፍራንኮ ቫሉታ " እርማት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

" ፍራንኮ ቫሉታ አላማውን ስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሃብት ማሸሻ እየሆነ ስላለ ለሱ እርማት ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#RedSea

" ዓለም ዛሬ ይስማ የቀይ ባህር አክሰስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

🟢 " ወይ እኛ ወይም ልጆቻችን ይህንን ያሳኩታል "🟢

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)  ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ኢትዮጵያ የማይናወጥ ብሔራዊ ጥቅም አላት ዓለም ዛሬ ይስማ የቀይ ባህር አክሰስ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል " ሲሉ በዛሬው ፓርላማ ላይ ተናግረዋል።

ይህንን ሲናገሩ የፓርላማ አባላት ዘለግ ያለ ከፍተኛ ጭብጨባ አሰምተዋል።

" በዚህ (ቀይ ባህር) ጉዳይ የምንደብቅ የሚመስለው ካለ ተሳስቷል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በጦርነት ፣ በኃይል አንፈልግም በቂ ሪሶርስ ነው በማንኛውም ህግ በማንኛውም የሀገር ልምምድ ኢትዮጵያ ይገባታል " ብለዋል።

" ብዙዎች እኮ ይላሉ 120 ሚሊዮን ህዝብ መቆለፍ ነውር ነው ይላሉ ፤ አንዳንድ የተገዙ ኢትዮጵያውያን ባይገባቸውም ወይ እኛ ወይ ልጆቻችን ያሳኩታል ፤ ይሄ ምንም ጥርጥር የለውም እውነት ስለሆነና ሎጂካል ነገር ስለሆነ " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ይህንን አስታኮ ' ነገ ውጊያ ይነሳል ' ብለው የሚያስቡ ሰዎች አንዋጋም ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' ኢትዮጵያን ሊወሩ ይችላሉ ሀገራት ' የሚል ስጋት ያለባቸው ሰዎች አልፎ አልፎ ስለሚነሱ ኢትዮጵያን ማንም ሰው ዛሬ በኃይል መውረር አይችልም ማንም !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለመመከት የሚያስችል በቂ አቅም አለን። ስንገዛ ስንሸምት የነበርናቸውን በውጊያ ክፍተት የገጠሙንን ነገሮች ማምረት ጀምረናል። እናመርታለን ፣ ሰው አለን ጀግኖች ነን ከነኩን ግን ለማንም አንመለሰም " ብለዋል።

ይህንን ሲናገሩም የፓርላማ አባላት በጭብጨባ አቋርጠዋቸው ነበር።

ኢትዮጵያ የወረራ ስጋት እንደሌለባት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " በአጼ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት ብዙ አቅም ባልነበረበት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን አድዋ ላይ ሄደው አሸንፈው ነጻነት ማስከበር ከቻሉ ያኔ 5 ሚሊዮን ነበሩ ዛሬ 120 ሚሊዮን ነው የጀግንነት ደሙ እንዳለ ነው ስጋት አይግባችሁ ማንም ቢመጣ አሳፍረን እንመልሳለን እኛ ግን ማንንም አንነከም " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በአስቸኳይ ተማሪዎቹ መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት ይካካስ " - ከፍተኛ ምክር ቤቱ ካለፋት 2 ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር…
ዛሬም ድረስ አንዳንድ ተቋማት ኢ-ህገመንግስታዊ የሆኑ የአለባበስ (ድሬሲንግ) ኮዶችን በመጥቀስ ብዙ ሙስሊሞችን በትምህርት፣ በስራ ገበታ ላይ አስተዋፅኦ እንዳያደረጉ እንቅፋት እየሆኑ እንዳሉ የፓርላማ አባሉ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ተናግረዋል።

ይህንን ያሉት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ነው።

ዛሬ እንኳን አሉ ኡስታዝ " ዛሬ እንኳን እኛ እዚህ ቁጭ ብለን ተማሪዎች በኒቃባቸው በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ተገለው አንዳንድ አካባቢዎች እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች አሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አይነት ድርጊት እጅግ ጎጂ መሆኑን በማንሳት መንግሥት መሰል ድርጊቶች እንዲታረሙ እንዲያደርግ የሚያስገነዝብ ሃሳብና ጥያቄ በይፋ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ቦትስዋና 👏 #ዴሞክራሲ

" ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " - ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

በአህጉራችን አፍሪካ የተረጋጋ የዲሞክራሲ ስርዓት ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደሟ ቦትስዋና ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አድርጋለች።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ለ58 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘውን ገዢ ፓርቲ ድምጻቸውን ነፍገውታል።

ፓርቲው አስደንጋጭ ነው የተባለ ሽንፈትን ተከናንቧል።

የፓርቲው መሪና የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫ መሸነፋቸውን አምነዋል።

ምንም እንኳን እስካሁን የምርጫው ውጤት በይፋ ባይታወጅም ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የከረመው ፓርቲያቸው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ ከፍተኛ ድምጽ አግኝቷል።

የፓርቲው እጩ ዱማ ቦኮ በዓለም ከፍተኛ አልማዝ አምራች ከሆኑት ሃገራት ውስጥ አንዷ የሆነችው ቦትስዋና ፕሬዝደንት ለመሆን ተቃርበዋል።

ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ለተቀናቃኛቸው ቦኮ ስልክ በመደወል በምርጫው መሸነፋቸውን ነግረዋቸዋል።

" በዲሞክራሲ ሂደቱ እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል። ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ብሻም፣ ገለል ብዬ በስልጣን ሽግግሩ ተሳትፎ አደርጋለሁ " ብለዋል ፕሬዜዳንት ማሲሲ።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ማሲሲ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ሂደት ደስ እንደተሰኙ ገልጸው " የህዝቡን ፍላጎት እና ምርጫ አከብራለሁ " ብለዋል።

ደጋፊዎቻቸውን ረጋ እንዳሉ በእርጋታቸው እንዲቀጥሉና ከአዲሱ የሀገሪቱ መንግስት ጀርባ ተሰልፈው እንዲደግፉ በይፋ ጥሪ አቅርበዋል።

ቦትስዋና በአፍሪካ የተረጋጋ ዲሞክራሲ ካላቸው ሃገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ነች በሚል ስትሞካሽ፣ በዓለም ከሩሲያ በመቀጠል ሁለተኛ የአልማዝ አምራች ሃገር ነች፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ ማግኘቱን ይገልጻል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#EarthQuake " በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ለ22 ቀናት ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት የመወጠር ሁኔታ አሁን ረገብ ብሏል " ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤልያስ ሊዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን/ኢቲቪ ተናግረዋል። " አሁን ባለን መረጃ ቅልጥ አለቱ ወደታች እየወረደ ነው ፤ በዚህም ምክንያት ባለፉት…
#Awash🚨

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር  " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

ዝርዝር መረጃ ከባለሞያዎችን እንደሰማን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦትስዋና

" የሀገራችንን የሰላም እሴቶች እናስቀጥል ፤ ... እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖር አረጋግጥላችኋለሁ " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ

ዱማ ቦኮ የቦትስዋና ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ።

ሞከዌትሲ ማሲሲ በምርጫው ተሸንፈዋል።

ላለፉት 58 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ‘ የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ ’ ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል። ፓርቲውን ህዝቡ በድምጹ ቀጥቶት ሸንፈትን ተከናብቧል።

ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ‘ አምብሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ’ በከፍተኛ ብልጫ አሸንፏል።

ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሞከዌትሲ ማሲሲ ፤ ለ2ኛ የስልጣን ዘመን መመረጥ ቢፈልጉም በሰላማዊ ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለዋል።

በሀገራቸው የዲሞክራሲ ሂደት ግን እጅግ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል። ገለል ብለው በሽግግሩ ላይ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።

ለተመራጩ ፕሬዜዳንትም ስልክ ደውለውላቸው በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው " እንኳን ደስ አለህ " ብለውታል።

መላው ህዝብም በአንድነት አዲሱን የመንግሥት አስተዳደር እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም በጋራ የሀገሪቱን #የሰላም እሴቶች እንዲያስቀጥል ፤ እንዲያስከብር ጥሪ አቅበዋል።

እንከን የለሽ የስልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አረጋግጠዋል።

ሀገሪቱን ለማገልገል ለተሰጣቸው እድልም ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት አመስግነዋል።

ቦትስዋና አፍሪካ ውስጥ በተረጋጋ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አስደናቂ ድል ተቀዳጅቻለሁ " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ " አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ " አሉ። የሪፐብሊካኑ ዕጩ ትራምፕ ድላቸውን ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት በፍሎሪዳ በተካሄደ መድረክ ነው። ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን እንደሚሆን ተናግረዋል። " ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ታላቅ ድል ነው፤ አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል " ብለዋል። በድንበሮች ያሉ ጉዳዮችን እልባት እንደሚሰጡ ቃል…
#USA

ስደተኞች በትራምፕ የስልጣን ዘመን ምን ይገጥማቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደም በምርጫ ዘመቻ ወቅት ዶላንድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በስደተኞች ጉዳይ ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር።

ትራምፕ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ነበር ያሉት።

ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

" ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው።

በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁንም ፕሬዜዳንት ሲሆኑ እንደሚያጠናክሩት ነው በዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ቃል የገቡት።

ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ነው የሚባለው።

ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር ግን እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ በተጨማሪም በዘመቻቸው ወቅት ፥ ለ4 አመት በስልጣን ሲቆዩ ህገወጥ ስደትን ከማስቆም ባለፈ በህጋዊ ስደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ ፥ " ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ ፣ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ፤ ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

ስደተኞችን " #የሀገራችንን_ደም_እየበከሉ_ነው " በማለት ተናግረውም ብዙዎችን አስቆጥተው ነበር።

በስደተኞች ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት መሆናቸው እርግጥ ሆኗል።

#TikvahEthiopia
#USA #deport

@tikvahethiopia