TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.68K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን መስጠት ተግባራዊ ተደርጓል።

በመቐለ ፣ አኽሱም ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና አጠቃላይ ከ54,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፈተናው ከሌሎች ክልሎች ለምን ቀድሞ ጀመረ ?

ፈተናውን የሚወስዱት በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች ናቸው።

በ2012 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል የነበሩ (code 01) ብዛታቸው ከ31 ሺህ የሆኑ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 2 እስከ 5 /2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

ከኮረም ፣ አላማጣ ፣ ዛታ ፣ ኦፍላ ፣ ራያ ጨርጨር ፣ ራያ ዓዘቦ፣ ማይፀብሪ፣ ላዕላይና ታሕታይ ፀለምቲ ሆኖው ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 3 አስከ 5 /2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 6 ና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ተጉዘው ከሀምሌ 9 እሰከ 11/2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 12 እና 13 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የነበሩ ( Code 07) የሶሻልና የተፈጥሮ ሳይንስ ብዛታቸው ከ23 ሺህ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው ከሀምሌ 9 አስከ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

#TikvahEthiopia
#TigrayEducationBureau

@tikvahethiopia
ልጆቻችን ... በማይናማር !

በርካታ የሀገራችን ልጆች ፦
- የወጣትነት እድሜያቸው ሳያልፍ ህይወታቸውን ለመቀየር፣
- ደክመው ያሳደጓቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንዲሁም፣
- እድሜያቸው ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተው ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሲሉ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰደዳሉ።

አንዳንዶቹ እጅግ አደገኛ ነው የተባለውን የህገወጥ ስደት በእግር ፣ በበረሃ ፣ በባህር አድርገው ይጓዛሉ።

አንዳንዶች ደግሞ እዚሁ ሀገር ውስጥ በየከተማው በተቀመጡ ደላሎች ማካኝነት ተታለው ምንም እንኳ በኤርፖርት በኩል ከሀገር ቢወጡም የሚሄዱት ግን መጀመሪያ ወደ ተባለው ቦታ ሳይሆን ሌላ እጅግ አደገኛ ቦታ ነው።

ለአብነት ማይናማር ይጠቀሳል።

የሀገራችንን ልጆች ' ታይላንድ ነው ለስራ የምትሄዱት ' ተብለው በደላሎች ተታለው ከሀገር የሚወጡ ሲሆን የሚወሰዱት ግን ወደ ማይናማር (ማያዋዲ) ነው።

ማይናማር ከደረሱ በኋላ የሚወሰዱት የቻናይና ማፊያ ቡድኖች ወደያዟቸው ቦታዎች እጅግ ደህንነት ወደ ሌለባቸው ስፍራዎች ነው።

በዛም የተለያዩ ህገወጥ ስራዎችን እንዲሰሩ በኃይል ያስገድዷቸዋል።

ከኢትዮጵያ ሲወሰዱ 1200 ዶላር እንደሚከፈላቸው ቢነገራቸውም እዛ ከደረሱ በኋላ ግን ለወራት ጉልበታቸውን ይበዘብዙታል። ስቃይና መከራ ይደርስባቸዋል።

ልጆቹ ድብደባ ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ፣ በሰንሰለት መገፈ ጭምር ነው የሚደርስባቸው።

ያለ ምግብ መጠጥ እስርም ይፈጽምባቸዋል።

ህይወታችንን እንቀይራለን ብለው የሄዱት ወጣቶች በስቃይ እና መከራ ውስጥ ያልፋሉ። ለወራት ያህል ስራ እያሉ እያሰሯቸው በኪሳቸው አንድም ብር የላቸውም።

በነገራችን ላይ በስፍራው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሌሎች በርካታ ሀገር ዜጎችም አሉ።

አንዳንድ ሀገራትም ልጆቻቸውን ያስወጣሉ።

በታይላንድ ጎረቤት፣ ማይናማር (በርማ፣ ማይዋዲ) የሚገኙ ' ድረሱልን ፍትህ እንሻለል ' ሲሉ ቃላቸውን የሰጡ የሀገራችን ልጆች፦

- ለስራ ተብለው ወደ ታይላንድ የሄዱ ከ1500 በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ፤

- በአሁን ሰዓት ላይ የሚገኙት ማይናማር (በርማ) ፤ ማያዋዲ (Myanmar-Myawaddy) በሚባል ቦታ እንደሆነ፤

- በህገወጥ የቻይና ጋንጎች ተይዘው በአሰሪዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈጸመ እንዳለ፤

- በግዴታ ህገወጥ ስራ (ሰዎችን በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል / Online Scamming) ስራ የሚያሰሯቸው እንደሆነ፤

- ከፍተኛ ድብደባ፣ የኤሌክትሪክ ቶርቸር፣ ሴቶችን መድፈር ፣ ምግብ መከልከል እንዲሁም እስከ መግደል የሚደርስ ግፍ እየተፈጸመ እንደሆነ፤

- እስከ አሁን በርካታ ሰዎች በድብደባና ቶርቸር ብዛት ህይወታቸው እንዳለፈ፤

- ካሉበት የስቃይ ቦታ ነጻ ወጥተው ወደ ሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ የህዝብንና የመንግስትን እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው፤

- በኤጀንሲዎች በኩል ወደ ታይላንድ ለስራ ለመሄድ ፕሮሰስ ላይ ያሉ ወገኖችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ

... ድምጻቸው አሰምተዋል።

በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መልዕክቶች በተከታታይ እናጋራለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደላሎችም ይሁኑ ' ወደ ውጭ ሀገር እንልካችሏለን ' የሚሉ ኤጀንሲዎች የት እና ለምን ስራ እንደሚልኳቹ በደንብ አጣሩ !! ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ወጣቶችን " ለብሩህ ተስፋ፣ ለጥሩ ህይወት ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በታይላንድ አለ " በማለት ወጣቶቻችንን ለከፋ የስቃይ ህይወት የሚዳርጉ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹ ጭራሽ ወደ አሜሪካ ፣ ካንዳ እና አውሮፓ ሀገራት ነው የምንልካችሁ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Myanmar

ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው።

የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው ማጭበርበር (Online Scam) ነው።

ቦታዎቹ ብዙ ናቸው።

ልክ እንደ ካምፕ አይነት ሲሆኑ ከነዛም ውስጥ ብዙ እንግልት እና ስቃይ የሚደርስባቸው አሉ።

ገና እንደሄዱ ስልካቸውን የሚቀሙ ፣ ፍጹም ኢሰብዓዊ አያይዝ የሚያዙ፣ ካልሰሩ የሚደበደቡ ፣ ስቃይ የሚፈጸምባቸው አሉ።

ከነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ይገኙበታል።

አንድ ለቲክቫህ መልዕክቱን የላከ ወጣት በደረሰበት ድብደባ ለወራት ያህል በክራንች ለመሄድ መገደዱን ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በዛው በማይናማር በስልክ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ወጣቶች በማይናማርና ታይላንድ ድንበር የሚፈጸሙ ጉዳዮች ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ እንደሚለያዩ አስረድተው እነሱ በሚኖሩበት ምንም አይነት ስቃይ ይሁን ችግር ደርሶባቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል።

ስልክም ሆነ ሌሎች አይነት ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን ተከልክለው እንደማያውቁ አስረድተዋል።

አሁንም የውጭ ፕሮሰስ ላይ ያላችሁ የት ሀገር ፣ በምን ስራ ዘርፍ እንደምትሄዱ በደንብ ጠይቁ።

በደላሎች ወደ ካናዳ ፣ አሜሪካ ፣ አውሮፓ ፣ ታይላንድ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለሚያስገኝ ስራ እየተባሉ ብዙ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የሆነ የኦንላይን የማጭበርበር (online scam) ስራ ወደ ሚሰራባቸው የማይናማር የተለያዩ አካባቢዎች ነው የሚወሰዱት።

ስቃይ ላይ ነን ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

ተጨማሪ ዶክመንተሪዎች እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች ፦
Al Jazeera - Rebels uncover scam centers in Myanmar
DW Shift - Scam Factories in Myanmar
Sea Today - Indonesian Scam Victims
WION - 900 scam factory Chinese Victims rescued near Myanmar
CNN News18 - Mynamar Cyber Crimes
CCTV - Major Criminal Suspects Transferred to China from Myanamar

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Myanmar ይህ የ ' DW ዶክመንተሪ ' #በማይናማርና #ታይላንድ ድንበር ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰዎችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በማዘዋወር ስለሚሰሩ ዓለም አቀፍ የኦንላይን ማጭበርበር (scam) ስራዎችን በግልጽ የሚያሳይ ነው። የሰው አዘዋዋሪዎች ሰዎችን የሚያዘዋውሩት በቅድሚያ ታይላንድ / የአውሮፓ ሀገራት እንደሆነ በመግለጽ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንደሚገኝ በመንገር ጭምር ነው በኋላ የሚሰራው…
" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች

ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል።

እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል የደላሎች ማታለያ ተታለው ነው በማይናማር የበየነመረብ ማጭበርበር (Online Scam) ላይ ተሰማርተው የሚገኙት።

ስሜን አይገለጽ ያለ በስፍራው ያለ ወጣት ፦

" ለምን ስራ አላመጣችሁም ? ለምን አልሰራችሁም (የኦንላይን ማጭበርበር) ተብሎ ሰው ይታሰራል።

እስር ቤት ይጣላል።

እኔ ለምሳሌ 5 ቀን ሙሉ እስር ቤት አድሪያለሁ። ያለ ምንም ምክንያት ።

ሽንት ቤት መሄድ የለም፤ ራስህ ላይ ነው የምትሸናው ፣ውሃ በግድ ያስጠጣሉ እምቢ ማለት አይቻልም ፣ የቁም እስር ነው ፣ መጮህ አይቻልም አፋችን ውስጥ ጨርቅ ይከታሉ በስነ ልቦና ሊጎዱን ነው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት።

እንደ ሰው አንታይም። በስነልቦና በጣም እየተጎዳን ነው። በሰንሰለት ይገርፋሉ፣ በኤሌክትሪክ ሾክ ያደርጋሉ፣ መሬት ውስጥ በሚቅበር ሽቦ ይገርፋሉ እራቁት።

ለዚህ ችግር አንደኛው መጠየቅ ያለበት የታይላንድ መንግስት ነው። የሱን ቪዛ መተን ነው ወደዚህ የመጣነው። አሳልፈው የሚሰጡን ከታይላንድ ነው።

ከባንኮክ ከኤርፖርት መጥተው በመኪና ሲወስዱን ያውቃል መንግስት ። የምንሰራበት ሲም ካርድ የታይላንድ ነው። ዓለም ሁሉ እየተጭበረበረ ያለበትን ስራ በታይላንድ ሲም ነው የሚሰራው።

እዚህ በካምፕ ላይ ያለው ቁሳቁስ ከታይላንድ ነው የሚመጣው ፣ ህንጻ የሚሰራበት እቃ ከታይላንድ ነው፣ መብራት እና ውሃም ከታይላንድ ነው፣ አልጋው ምኑ የታይላንድ ነው።

ቻይናም ስለ ሁኔታው የምታውቅ ሀገር ስለሆነች ማናገር ይገባል። በቻይናውያን ድጋፍ የተሰመረተ ኩባንያ ነው ያለው።

መጠየቅ ያለባቸው ታይላንድ እና ቻይና ናቸው።

ማይናማር ለራሷ ላለፉት በርካታ ዓመታት እስካሁን ድረስ በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ናት።

የኢትዮጵያ መንግስት ታይላንድን እና ቻይናን ይጠይቅልን።

የኢትዮጵያን ዜጎች ነው እንደ እቃ ነው የሚጠቀሙት። ቁሳቁስ ሲመጣ እንኳን የሚያሸክሙን እኛን ነው። እንደ አህያ ነው የሚጠቀሙን። ክትባት ሲመጣ ለኛ አይሰጥም። ጥቅም የለንም። እንደባሪያ ነው የምንታየው። እየኖርን አይደለም። ተስፋም የለንም።

እባካችሁ ጭሁልን ! " ብሏል።

ሪፖርት፦ አንድ የተመለከትነው ሪፖርት በማይናማር ፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የኦንላይን ማጭበርበር (Scam) ላይ የተሰማሩ ሰዎች አሉ። ማፊያዎች በሚመሯቸው በነዚህ አካላት በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ድረስ ይሰርቃሉ። በማጨበርበር ስራው ላይ የተሰማሩት ሰዎች እራሳቸውም የችግሩ የመጀመሪያ ሰለባዎች ናቸው።

#ጥንቃቄ፦ " እጅግ ጠቀም ላለ ስራ ነው " እየተባለ ወደ ታይላንድ የምትሄዱ ጥንቃቄ አድርጉ። ስራው ምንድነው በሉ ፣ ከታይላንድ ውጭ እንደማትወሰዱ እርግጠኛ ሁኑ ፣ ዶክመንት ተፈራረሙ የሚልኳቹን ሰዎች ማንነት አጣሩ፣ ኤጀንሲ ይሁን ደለላ ማስረጃቸውን ሁሉ ያዙ።

ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይደረስ !

#TikvahEthiopia
#Myanmar

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya #Update ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ። ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ። ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት። የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም…
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል።

ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል።

" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።

ከሥራቸው የማይባረሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የሚያገለግሉት የካቢኔው ዋና ፀሐፊ ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ።

ሌሎቹ በጠቅላላ የካቢኔያቸው አባላት ሚኒስትሮች ተባረዋል።

የፋይናንስ ረቂቅ ሕጉን ተከትሎ ፥ " ግብር ሊጨመርብን አይገባም በቃን ! ፣ ተጨማሪ ግብር አንከፍልም፣ ሕጉ ኑሮው ያስወድድብናል " በማለት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የጀመሩት ተቃውሞ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የ39 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ሩቶ ሕጉን ሰርዘውታል።

ምንም እንኳን ሕጉ ሙሉ በሙሉ ቢሰረዝም ተቃውሞው አላበቃም።

ፕሬዜዳንቱ ባልተለመደ ሁኔታ ከተቃዋሚ ወጣቶች ጋር በኦንላይን (X) ምንም አይነት ገደብ የሌለው ግልጽ ሕዝባዊ ውይይት አድርገው ነበር ፤ ያም ቢሆን ሕዝባዊ ጥያቄውን አላስቆመውም።

ፕሬዜዳንቱ በሙስና የተዘፈቁ ሚኒስትሮችን ጠራርገው እንዲያባርሩና ካቢኔውን እንዲበትኑ ጥሪ ሲቀርብ ነበር።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ፕሬዜዳንቱ ካቢኔያቸውን በትነዋል።  " የሕዝቤን ድምጽ በመስማት ነው እርምጃውን የወሰድኩት " ብለዋል።

#Kenya
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Internet

ትላንት ምሽት በተካሄደ የኢንተርኔት የመመለስ ስራ ለበርካታ ወራት ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኛታቸው ተሰምቷል።

ከሁነኛ ምንጭ በተገኘ መረጃ ኢንተርኔት ተቋርጦ በነበረባቸው 19 ከተሞች አገልግሎት ተመልሷል ተብሏል።

የትኞቹ ከተሞች ናቸው ?
- ባህር ዳር
- ጎንደር
- ደሴ
- ኮምቦልቻ
- ወልዲያ
- ሰቆጣ
- ደብረ ብርሃን
- ደብረ ማርቆስ
- ደብረ ታቦር
- ፍኖተ ሰላም
- ገንደውሃ
- ከሚሴ
- ጋሸና
- ቡሬ
- ባቲ
- ደጀን
- ደባርቅ
- ኢንጅባራ
- ሁመራ ናቸው።

በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን ስለ ተለቀቀው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመለከተ ጠይቀናቸው ፍጥነቱ ያን ያህል እንደሆነ እንዲሁም መጨናነቅም እንደሚታይ ነገር ግን እንደተለቀቀ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #ተጠንቀቁ ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ። " ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦ - ስራው ምንድነው ? - በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ? - የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን ! - ባለበት…
🔈#ይነበብ

ወጣቶችን ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ?

በኦንላይን ወይም በደላሎች አልያም በኤጀንሲዎች " እዚህ ሀገር ጥሩ ስራ አለ ፤ ክፍያውም ከፍ ያለነው " ተብለው ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ሀገራት ይዘዋወራሉ።

ለአብነት ያህል ወጣቶች ከሚዘዋወሩባቸው ሀገራት መካከል የሳይበር ማጭበበር ( Cyber Scam) ማዕከላት ተብለው ወደ ሚታወቁት ፦
• ማይናማር ፣
• ካምቦዲያ፣
• ላኦስ
• ማይናማር ታይላንድ ድንበር
• ቻይና ማይናማር ድንበር በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

እነዚህ አካባቢዎች ባሉ የተለያዩ ቦታዎች በኦንላይን ማጭበርበር ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች አሉ።

በእርግጥ መጀመሪያ ላይ ወጣቶቹን " እልካችኋለን " የሚሏቸው ሌሎች በኢኮኖሚና ደህንነት እጅግ ጠንካራ ፣ ጠንካራ ባይሆኑም እንኳን ያን ያህል የከፋ ሁኔታ ላይ ወደማይገኙ ሀገራት ነው።

እዛ ቦታ ከደረሱ በኋላ ግን የሚልኳቸው ወደ ጎረቤት ድሃ እና የህግ ስርዓት ወዳልጠነከረባቸው ሀገራት ይሆናል።

የሚሰራው ማጭበርበር ምንድነው ?

ስራ ብለው የሚልኳቸው መጀመሪያ ፦
- የኦላንይ ግብይት ስራ ማቀላጠፍ
- የኦንላይን ሴልስ ስራ
- የሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- የማርኬቲንግ ስራ ... ሌላም ሌላም ነው።

ነገር ግን ስራ አለበት ወደ ተባለው ስፍራ ሲሄዱ የሚሰሩት ስራ መጀመሪያ ላይ ከተነገራቸው ተቃራኒ ነው።

የየራሳቸው ጋንግ አለቆች ባላቸው እጃቸውም ረጅም በሆኑ ሰዎች በሚመሩ የማጨበርበር ተግባር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች ያስገቧቸዋል።

እነዚህ ሰዎች ስልክ / ኮምፒየተር የሚያቀርቡላቸው ሲሆን በዛም ዓለም አቀፍ የማጨበርበር ስራ ላይ ያሰማሯቸዋል።

🔴 ዴቲንግ 🔴

የመጀመሪያ ስራቸው ከኢንተርኔት ላይ ውብ የሆኑ ሴቶችን / ስኬታማ ሴቶችን / ስኬታማ ወንዶችን ታዋቂ ሰዎችን ፎቶ በማውረድ የውሸት አካውንት መክፈት ነው።

በመቀጠል የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ። ምናልባትም በቅርብ የሚያውቋቸውን ሰዎችንም ሊሆን ይችላል።

እነዛን ሰዎች ልክ እንደ ኖርማል ሆነው ያለ ማቋረጥ ጊዜ ወስደው ያናግሯቸዋል።

የትኛውንም ጊዜ ይፍጅ ማናገራቸውን ይቀጥላሉ።

ስለ ውሸት ስራቸው፣ ስለ ህይወታቸው እየፈጠሩ ያወራሉ። በዚህ ውስጥ ምንም ምልክት አያሳዩም።

ወደ ፍቅር ከወሰዷቸውና ከጣሏቸው እምነትም ካገኙ በኃላ መጨረሻው ወደሆነው ዓላማቸው ገንዘብ ማስላክ ይገባሉ።

" ለምን እኔ ምሰራው ስራ ላይ ኢንቨስት አታደርም / አታደርጊም " በማለት ለምሳሌ ክሪፕቶ  ላይ ብለው ገንዘብ ይቀበላሉ።

በቃ አለቀ ! ገንዘባችሁ ተበልቶ ይቀራል። በኃላም ብሎክ አድርገው ይሸኟችኋል። ቀጣይ ሌላ ሰው ታርጌት ያደርጋሉ።

ወጣቶቹ ይሄን ካላደረጉ ምናልባትም ኢ-ሰብአዊ ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይችላል።

⚫️ በጎ አድራጎት ⚫️

የውሸት ማንነት ፎቶ ተጠቅመው አካውንት ከፍተው (ሴትን በወንድ ወንድ ደግሞ በሴት ማንነት) አንድ ታርጌት ያደረጉትን ሰው ረጅም ጊዜ ያናግሩ እና ለእርዳታ / ለእርዳታ ድርጅታቸው ገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያሳምኗቸኣል።

እነዛ ሰዎች ላይ እምነት የጣሉባቸው ተጨበርባሪዎች በሀዘን ተሰብረው ገንዘባቸውን ይልካሉ። ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ይደረጋሉ።

🟡 ባለሃብት መምሰል 🟡

የውሸት ማንነት በመፍጠር ፣ ፎቶዎችን በመጠቀም በኦንላይን ሰው ያናግራሉ።

እንዲታመኑ ረጅም ጊዜ ሊወስዱም ይችላሉ።

ሰዎቹ ካመኗቸው በኃላ ገንዘባቸውን በጋራ አፍስሰው ስለሚሰሯቸው ስራዎች በማናገር ገንዘብ ያስልካሉ። ከዛማ ቀልጦ ይቀራል። ብሎክ ያደረጋሉ !

🟤 ደንበኞችን ማነጋገር 🟤

ይህም በተመሳሳይ በሀሰተኛ ማንነትና ስራ ከተለያዩ ሰዎች እያነጋገሩ በማጭበርበር ገንዘብ መቀበል ነው።

ለምሳሌ ፦ እቃ የሚሸጡ አስመስለው ብር ካስላኩ በኋላ የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ።

🔵 ' ኮሜንት/ሬት በማድረግ ገንዘብ አግኙ ' 🔵

እነዚ አጭበርባሪዎቹ የውሸት ማንነት ተጠቅመው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ ወይም በሌላ መንገድ ተጠቅመው የሚያጭበረብሩትን ሰው ማናገር ይጀምራሉ።

" ጎግል ላይ ግቡና ስለዚህ ድርጅት ጥሩ አስተያየት ጻፉ ይከፈላችኋል " ይላቸዋል።

ከዛም የመጀመሪያውን ክፍያ በመፈጸም እምነት ያሳድራሉ።

" ይሄን ያህል ብር ከላካችሁ ይሄን ያህል ታገኛላቹ " በማለት የሰዎቹን ማንነት ይገመግማሉ። እስከዛ ድረስ ግን ገንዘብ መላካቸውን አያቆሙም።

የሚጭበረበረው ሰው ብዙ ብር ካስላኩት በኋላ የውሃ ሽታ ይሆናሉ።


በተጨማሪም ...

እንደ ፖሊስ፣ደህንነት፣ ባንክ ሰራተኛ ፣ እንደ ድርጅት ኃላፊ ሆነው የሚያስመስሉ አጭበርባሪዎችም አሉ።

ስራውን የሚሰሩት ሰዎችም ተጠቂዎች ናቸው።

ስራውን ካልሰሩ አሰቃቂ ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል።

እንደ ባሪያ ለረጅም ሰአትም ያሰሯቸዋል።

እንደ ቅርብ ጊዜ ሪፖርት ፥ በማይናማር፣ ካምቦዲያ፣ ላኦስ፣ ቻይና በመሳሰሉ ሀገራት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በኦንላይ ማጭበርበር ላይ ተሰማርተዋል።

ስራዎቹንም የሚያሰሯቸው ሰዎች እጃቸው በጣም ረጅም ነው።

#TikvahEthiopia
#CyberScam

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#OnlineScam ባለፈው ወር ላይ የላኦ እና የቻይና ፖሊስ በሰሜን ላኦስ ጎልደን ትሪያንግል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በህገወጥ የጥሪ ማእከል የኦንላይን ማጭበርበር (Online Scam) ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያሏቸውን 280 ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ግለሰቦቹም ወደ ቻይና ዲፖርት ተደርገዋል። ፖሊስ ግለሰቦቹን በያዘበት ወቅት 460 ኮምፒዩተሮች እና 1,345 ስልኮችን ይዟል። እንዚህ አካላት…
#Update

ሕንድ በማይናማር እንዲሁም ካምቦዲያ በሳይበር ወንጀል / የኦንላይን የማጭበርበሪያ ማዕከላት (Online Scam Centers) ውስጥ ያሉ ዜጎቿን አስወጣች።

ሀገሪቱ በማይንማር፣ ማያዋዲ ' ሽዌ ኮ ኮ '  በሚገኝ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ 11 ተጎጂ ዜጎቿን እንዳስወጣች ገልጻለች።

ሕንዳዊያኑ ከማዕከሉ እንዲወጡ የተደረገው በማይናማር ባለስልጣናት እና በአካባቢው ወጣቶችን ከቦታው እንዲወጡ በሚረዱ ሰዎች ርብርብ ነው።

አሁን ላይ እነዚህ ሕንዳዊያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሕንድ እንዲመለሱ እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ የሕንድ መንግሥት ከካምቦዲያ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር በሳይበር ወንጀል / ኦንላይን ማጭበርበር ማዕከላት ውስጥ እንዲሰሩ ሲደረጉ የነበሩ 14 የሕንድ ዜጎችን አስወጥቷል።

በፍጥነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ስለመሆኑም ሰምተናል።

ሕንድ በርካታ ወጣቶቿ በማጭበርበሪያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙባት ሀገር ስትሆን ከዚህ ቀደም መሰል ዜጎቿን የማስወጣት እርምጃ የወሰደች ሲሆን አሁንም ቀጥላለች።

ሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ ተጠቂ ናቸው ያሏቸው ዜጎቻቸውን የማስወጣት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው።

በማይናማር፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ ፣ ቻይና ታይላንድ ድንበር፣ ታይላንድ ማይናማር ድንበር ባሉ የማጭበርበሪያ ማዕከላት እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ የሌሎች ሀገር ዜጎች ይገኛሉ።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች አሉ (ከተለያዩ ሀገራት)።

በስፍራው የሚገኙት ብዙሃኑ ወጣቶች ናቸው።

ወደዚህ ተግባር የገቡት እራሳቸው ተጭበርበረው ነው / ይህ ማለት እራሳቸውም ተጎጂዎች (ሰለባ) ናቸው።

ደላሎችና ኤጀንሲዎች ወጣቶች 'ወደ ታይላንድ / ወደ ሌላ ሀገር' ለ፦
- ሴልስ
- የማርኬቲንግ
- ለሆቴል እንግዳ ተቀባይ
- ለተቋማት ደንበኞችን ማነጋገር በሚል ነው የሚልኳቸው።

በኃላም ወደ ጎረቤት ሀገራት በመውሰድ የተደረጀ የኦንላይ ማጭበርበር ስራ ላይ እንዲሰማሩ ነው የሚደረገው።

ወጣቶቹ ከሚሰማሩባቸው ተግባራት ዋነኛው ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት በመክፈት ሰዎችን በተለይ ሴትን በወንድ / ወንድ በሴት አስመስለው በማነጋገር ገንዘብ ማጭበርበር ነው።

የታዘዙትን አድርገው ገንዘብ ካላመጡም የከፋ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል።

ወጣቶችን እንዲያጭበረብሩ የሚያሰሩ ማፊያዎቹ በቀጠናው እጃቸው ረጅም የሆነ ሰዎች ናቸው።

እጃቸው በረዘመ ማፊያዎች በሚመራው የሳይበር ወንጀል / የኦንላይን ማጭበርበር / ተግባር በየአመቱ እስከ 43.8 ቢሊዮን ዶላር ይዘረፋል።

ስለ ማጭበርበሪያ ስልቶቹ / ሰዎችን በምን መንገድ እንደሚያጭበረብሩ በዚህ ያንብቡ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88986

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ተገኝቷል " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ባለፈው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 7.02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ (Revenue) ማግኘቱንና ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ገልጿል።

ይህ ገቢ በኢትዮጵያ ብር ሲቀመጥ 402 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ምን አሉ ?

አየር መንገድ 577,746 የበረራ ሰዓቶችን እንደበረረና ይህም ቀደም ሲል ካለው 19 በመቶ እድገት እንዳሳየ ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ አየር መንገዱ 17.1 ሚሊየን ተጓዧችን እንዳስተናገደ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆነው አለም አቀፍ ተጓዦች እንደሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" የሀገር ውስጥ በረራ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል " ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ " ያለፈው በጀት ዓመት ማስተናገድ የተቻለው 2.7 ሚሊዮን የሀገር ተጓዦች ነበር " ብለዋል።

ከካርጎ ጋር ተያይዞ በዚህ ዓመት ካለፉት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ እንዳሳየ ተሰምቷል።

በዚህ በጀት ዓመት አየር መንገዱ ያጓጓዘው ጭነት መጠን ከ754, 681 ቶን ጭነት እንደሆነ ተናግረዋል።

" አየር መንገዱ ከካርጎ ያገኘው ገቢ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 8 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ " ቀደም ተብለው ከታዘዙ 20 የሚሆኑ አውሮፕላኖች ጋር ተደምሮ 125 የሚሆን አውሮፕላኖች እንደታዘዙ " ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።

ከቦይንግ የታዘዙ አውሮፕላኖች አለመገኘታቸውን ተከትሎ የአውሮፕላን እጥረት እንዳጋጠመ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia