TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ድርጅቱ ጉባኤውን እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ ከፍተኛ አመራር አለ " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ለሁለት የከፈለውና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ጉባኤ መክፈቻ ዛሬ ተደርጓል።

የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በመክፈቻው ባሰሙት ንግግር ምን አሉ ?

ሊቀመንበሩ " ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና እንዳያገኝና ጉባኤው እንዳያካሂድ እንቅፋት የሚሆን ከድርጅቱ የተፈለፈለ #ከፍተኛ_አመራር አለ " ብለዋል።

" በፓርቲያችን ውስጥ ተፈልፎሎ ያደገ፣ ፓርቲያችን ለመበተን እየሰራ ያለው የጥፋት ቡድን ያደረገውና አሁንም እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ፥ በየሰዓቱ እየፈጠረው ባለው ማደናገርያ ሁኔታችን ከመጥፎ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሯል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህንም ለማስቆም በዘላቂነት ለመቀየር ብቸኛ መፍትሔው 14ተኛ ጉባኤ ማካሄድ እና ማካሄድ ብቻ ነው " ብለዋል።

" ህወሓት አድኖ ህዝብ ከጥፋት መታደግ የጉባኤው ዋነኛ አላማ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የድርጅቱና የህዝቡ የተሟላ ድህንነት ማረጋገጥ በሚችል መልኩ በዴሞክራሲያዊ ውይይትና ክርክር ብቃት ያላቸው አመራሮች መምረጥ ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የአሁኑ ጉባኤ ለድርጅቱ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው " በማለት አክለዋል።

" ህወሓት ፈረሰ ማለት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ፈረሰ ማለት ነው " ብለው " በዚህ ግዜ ህወሓት ከፈረሰ የፕሪቶርያው ስምምነት አይኖርም ብቻ ሳይሆን ከነአካቴው ታሪክ ሆኖ ይረሳል ማለት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ከፈረሰ የትግራይ ህዝብ ለበይ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

" ስለዚህ እነዚህ ችግሮችና አደጋዎች ለመፍታት ነው ጉባኤአችን በዚህ ፈታኝ ወቅት ለማድረግ የፈለግነው ብቻ ሳይሆን የግድም ልናደርገው የተገደድነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia