#EOTC
ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል።
ቤተክርስቲያን ፈተናዋን እንዴት ማለፍ እንዳለባት በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቀዋለን ሲሉ ገልጸዋል።
" ባለፈው የተለያዩ አባቶች በተለያየ መንገድ ተናገሯቸው ስለተባሉት ጉዳዮች ተነስቶ መንግስት ቀየሜታውን ገልጾ ቤተክርስቲያን መልስ እንድትሠጥበት አሳስቧል " ያሉት ብፁዕነታቸው " ቤተክርስቲያንም በስፋት፣ በትኩረት ተወያይታበታለች (ቅዱስ ቋሚ ሲኖዶስ) ይሁን እንጂ የብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው የሚሆነው ፣ ምክንያቱም አንድ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ፤ ቀርቦ ተጠይቆ አውንታዊ መልስ ሰጥቶ ስህተት ነው ? እውነት ነው ? ብሎ የሚወሰን እንጂ ብግድ ተብሎ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በሌላ የተለያየ መልኩ እንዲህ ነው እንዲያነው ብሎ መናገር ህገ ቤተክርስቲያናችን አፈቅድም " ብለዋል።
" ቤተክርስቲያን ሰላምን መፈለግ ፣ መሻት ፣ መልካም ነገር ማድረግ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ አቋም የላትም " ያሉት ብፁዕነታቸው ፤ " እንደ ህግ እና ስርዓታችን በአባቶች ደረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ይወስናል። ይህ ቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚለውን እንዲል አልፎታል " ሲሉ አሳውቀዋል።
ብፁዕነታቸው ፤ " አሁን ግራ የሚያጋባው ትላንት ለበዓለ ጥምቀቱ የተሰየመው አብይ ኮሚቴ ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ፣ከታላላቅ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ ይህ ከባድ ፈተና እየተነሳ እንዳለና አሁንም በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነቱን ለይታ እንድታወግዝ ፣ የራሷን መልዕክት እንድታስተላልፍ በመንግሥት አቋም ተይዞ ለአብይ ኮሚቴው ተነግሯል " ብለዋል።
" ቤተክርስቲያን ያራሷ ነፃነት አላት ፣ የራሷ ክብር አላት ፣ የራሷ ነፃ መድረክ ፈላጊ ናት ሁሉም እየተነሳ ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም " ሲሉ ገልጸዋል።
" ክፉውን ክፉ፣ በጎውን በጎ፣ መልካሙን መልካም ፤ መልካም ያልሆነውን መልካም አይደለም ብላ ለማስተላለፍ የራሷ ህግ ስርዓት አላት " ብለዋል።
" የፈለገ የሚያዛት ፣ የፈለገ የሚያሽከረክራት ፣ ያልወደደ እንደ ወደደ ፍላጎቱን ምኞቱን እንድትፈፅምለት የሚጎትታት ቤተክርስቲያንን ኖራም አታውቅም ወደፊትም ልትኖር አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።
" ቤተክርስቲያን በራሷ ነፃ መድረክ ቆማ ችግሩን ችግር ነው ብላ መናገር አለባት እያደረገችም ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይሄ በፍፅሙ አይመጥነኝም። እንዲህ አይነቱ የኔ ቃል አይደለም ብላ #ታውጃለች ግን በግልፅ መጠየቅ ያለባትን ጠይቃ መናገር ያለበትን እንዲናገር ፈቅዳ ሁሉን ነገር በአግባቡ ታደርጋለች እንጂ በኩርፊያ በአላስፈላጊ ብሂል ይሄን ካላደረግሽ በዓል ለማክበር አልችልም ፣ ከናተ ጋር ግንኙነት የለንም እስከሚባል ድረስ የሚኖረው ነገር ከማንም ከምንም በፍፁም አይጠበቅም " ሲሉ አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia