TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ እና የኦነግ ፍጥጫ‼️

#በምዕራብ_ወለጋ የታየውን የሰላም መደፍረስና የግጭት ቀጠና መሆኑን አስመለክቶ በመንግስት በኩል የተለያዩ መግለጫዎች ሲሰጡ እንሰማለን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ እንደተናገሩት፣ ስምም ባይጠቅሱ ችግሩን የጎተተው ኦነግ መሆኑን የሚያመለክቱ መግለጫዎችን እየሰጡ ነው፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርስ ምን ይላል? ሸገር የኦነግን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጠይቋል፡፡


ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OromiaRegion

ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ።

በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹ ስለመኖራቸውን ገልፀዋል።

ከሟቾች መካከል ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ ፤ ቤቶች መንደዳቸውንም ፤ ጥቃቱ ሲፈፀም የነበረው በከባድ መሳሪያ ጭምር እንደነበር አመልክተዋል።

ለሚመለከተው የወረዳው አካል በሰዓቱ ጥቃት መኖሩን ጥቆማ ቢያደርሱም በቶሎ የደረሰ አካል እንዳልነበረ አስረድተዋል።

የዛሬውን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ክልሉም አምኖ አረጋግጧል። ጥቃቱን ጭካኔ የተሞላበትም ነበር ብሏል።

ክልሉ ባወጣው መግለጫ " የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

" ቡድኑ መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሷል " ሲል ገልጿል።

በቡድኑ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉም ብሏል።

ክልሉ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ እንዲሁም ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia