TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

" በአላማጣ ዙሪያ የነበረው ኃይል አከባቢውን ለቆ ወጥቷል " - የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትላንትና ከምሸቱ 4:00 ባወጣው መግለጫ ፥ " በአላማጣ በቅሎ ማነቂያና ገርጃለ የነበረው #የተወስነ የትግራይ ተዋጊ ኃይል አከባቢውን ለቆ ወጥቷል " ብሏል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትን በማስመልከት በአዲስ አበባ በወጣው የአተገባበር ኦፕሬሽን ፕላን መሰረት በማድረግ ተዋጊ ኃይሉ አከባቢውን እንዲለቅ መደረጉን ገልጿል።

ለአላማጣ ህዝብ ደህንነት ተብሎ የተወሰነ ተዋጊ ኃይሉ ከቦታው ለቆ ቀድሞ ወደ ነበረበት ቦታ መመለሱን አመልክቷል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትም አቶ ጌታቸው ረዳም ይህኑን አረጋግጠዋል።

አቶ ጌታቸው ራዳ ፤ " የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ትግበራ አካል ሆኖ የትግራይ ተፈናቃዮች በቀላሉ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ከፌዴራል መንግስት እና ከአማራ አስተዳደር ጋር ያለውን መግባባት ለማክበር በአላማጣ አቅራቢያ ከሚገኙት ገርጀለ እና በቅሎማናቂያ አካባቢዎች የትግራይ ሃይሎች እንዲወጡ ተወስኗል " ብለዋል።

ተጨማሪ የትግራይ ተፈናቃዮችን ለመመለስ ተመሳሳይ አይነት እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ም/ፕሬዝዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ የትግራይ አስተዳደር ወደ አላማጣ እንደሚገባና በአከባቢው  የሚገኘው የትግራይ ታጣቂ ኃይል ይወጣል በማለት ተናግረው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
                                       
@tikvahethiopia