TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በአሁኑ ሰዓት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አስከሬን ወደ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እየተሸኘ ይገኛል - EHRC @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፕ/ር መስፍን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ተወካዮቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አፍቃሪዎቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

#ኢሰመጉ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኢሰመጉ #ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ( #ኢሰመጉ ) ፤ መንግስት ከፍተኛ ጥቃትና ጫና እየፈጸመበት እንደሆነ ይህም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ትላንት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ጉባኤው በተለያዩ ጊዜ ተፈጽመውብኛል ያላቸው ጥቃቶች እና ከፍተኛ ጫናዎች ምንድናቸው ?

- ኢሰመጉ አመራር ላይ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የሚፈጸም ክትትል ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ፤

- የሰብዓዊ መብት ክትትል ስራችሁን ካላቆማችሁ ፤ መንግሥትን በሰብዓዊ መብት ጥሰት መወንጀል ካላቆማችሁ  ' ዋጋ ትከፍላላችሁ ' የሚል ዛቻ፤

- የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ስራ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ የመንግስት ጸጥታ አካላት አካላዊ ጥቃት ማድረስ ፣ መሳደብ፣ ማንገላታት፣ ከስራቸው እንዲቆጠቡ ማስፈራራት

- ምንም እንኳን ኢሰመጉ ላለፉት 32 ዓመታት በሀገሪቱ ህግ አግባብ ተመዝግቦ እየሰራ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ሰዎች " ፍቃድ የላችሁም " በማለት ማስፈራራትና የእስር ዛቻ መሰንዘር፤

- በአባላት ላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ህገወጥ እስር መፈጸም፤

- በአዲስ አበባ ተገቢ ያልሆኑ ክሶችን ለመመስረት እንቅስቃሴ ማድረግ ከፍተኛ ጫና ለማሳደር መሞከር ፤

- የኢሰመጉ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከሀገር ውጭ ካሉ ስራዎችና ስብሰባዎች ወደሀገር ቤት ሲመለሱ ማንገላታት ፣ ማዋከብ ፣ክትትል ማድረግ ፤

.... የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር " 13/2011 " መሠረት ሐገር በቀል ድርጅት ሆኖ በ1984 ዓ.ም የተመሠረተ እና በምዝገባ ቁጥር " 1146 " ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳግም ተመዝግቦ በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት መሆኑን አስገንዝቧል።

(የኢሰመጉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia