TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.5K photos
1.41K videos
203 files
3.84K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia            
#Mekelle

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ " በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ " ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
            
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ። ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል። ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ…
#Update

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጥያቄያችን ለመመለስ ቃል ስለገባ የስራ መልቅቅያ ጥያቄያችን ትተነዋል " - የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት ያስገቡትን የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደተውት አሳወቁ።

ፕሬዜዳንቱና ምክትል ፕሬዜዳንቱ ይፋ ባደረጉት መግለጫ ፤ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ተከትሎ ሰኔ 18 /2016 ዓ.ም ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ውይይት ማደረጋቸውን ገልጸዋል።

በዚ ውይይት ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ለመመለስ ቃል በመገባቱ ስራ የመልቀቅ ጥያቄያቸውን እንደተውት አሳውቀዋል።

ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ በግልፅ ያላብራሩ ሲሆን ከላይ እስከ ታች የሚገኘው የፍርድ ቤት አካል ስራውን ተረጋግቶ እንዲሰራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዜዳንቱና  ምክትል ፕሬዜዳንቱ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተከትሎ የወረዳና የዞን ፍርድ ቤቶች ስራ የማቆም አድማ መምታት ጀምረው ነበር

ከክልሉ ፕሬዜዳንት ከተደረገው ውይይት በኃላ ችሎቶች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በአካል ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ከመቐለ ውጪ በመላው ክልል ያሉ ፍርድ ቤቶች መደበኛ አገልግሎት መስጠት መቀጠላቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የፕሮቶኮል ሹም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

" በ9 ወር 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 261 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል " - የትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ

የትግራይ የትራንስፓርትና የመገናኛ ቢሮ ከሰሞኑን አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

በዚህም በክልሉ ባለፉት 9 ወራት (ከመስከረም እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም) በትራፊክ አደጋ ምክንያት ብቻ 270 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

261 ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በንብረት ላይ የደረሰ ውድመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ተነግሯል።

በጥናት የተለየው የትራፊክ አደጋ መነሻ ምንድን ነው ?
- ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ መንዳት
- ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት
- ከተፈቀደ መስመር ውጪ ማሽከርከር
- ርቀት ጠብቆ አለማሽከርከር
- የአሽከርካሪዎች አቅም ማነስ ናቸው።

እግረኞች ዜብራ ተጠቀመው መንገድ አለማቋረጥ እና ቀኝ መስመር ይዘው መጓዝ በተጨማሪነት የአደጋ መነሻዎች ሆነው ተጠቅሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "

" የአንድ ዓመት ውዙፍ ደመወዝ አልተከፈለንም "  ያሉ የቀድሞ የትግራይ ኃይል አባላት ድምጻቸውን ለማሰማት ሰልፍ ወጡ።

የቀድሞ አባላቱ ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ አካሂደዋል።

በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- " የሰማእታት ቃል የሚከበረው የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው በማገዝ ነው ! "
- " መስዋእት ስለከፍልንና ከሰራዊት ስለተሰናበትን ደመወዛችን ማጣት አይገባንም ! "
- " ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "
- " ፍትህ ይሰጠን ! "
- " መብታችን ይከበርልን ! "
- " ድምፃችን ይሰማ ! " የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አስምተዋል። 

ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንዱ የሆነው ፀጋይ ገ/ስላሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጀምሮ ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችን አቅርበን የተሰጠን ምላሽ የለም " ብሏል።

" ፍትሃዊ ጥያቄያችን እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ ሳንታክት እንጠይቃለን " ሲል አክሏል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ለማቀረብ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ያመሩ ሲሆን በስብሰባ ምክንያት ጥያቄያቸውን ሰምቶ ያስተናገዳቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ትግራይ

ባለፉት 3 ወራት በዘራፊዎች ጥቃት ለደረሰባቸው 482 ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱን መቐለ የሚገኘው የዓይደር ሰፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አስታወቀ።

በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ብርሃነ ገ/ሚካኤል ለትግራይ ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ ከሚያዝያ እሰከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ባሉት ወራት በቢላዋ ሌሎች መሳሪዎች በዘራፊዎች ጥቃት የደረሰባቸው 482 ሰዎች በሆስፒታሉ የድንገተኛ የህክምና ክፍል ታክመዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች የ9 ዓመት ዕድሜ ካለው ህፃን አስከ የ70 አመት አዛውንት የሚያካትት እንደሆነ  ተናግረዋል።

ከነዚሁ ተጠቂዎች 69ኙ ሴቶች ናቸው።

የሆስፒታሉ የህክምና ተገልጋዮች የመቀበያ ሰነድ እንደሚያመላክተው፦

- በሚያዝያ 183 ሰዎች
- በግንቦት 136 ሰዎች
- በሰኔ 163 ሰዎች በዘራፊዎች ጥቃት ደርሶባቸው ታክመዋል።

ሆስፒታሉ ያለው ውስን የመድሃኒት ፣ የህክምና ቁሳቁስና ባለሙያ ለእርጉዝና የሚወልዱ እናቶች እንዲሁም ለሌሎች የቆየ ህመም ላለባቸው ተገልጋዮች የቅድምያ አገልግሎት ከመስጠት ፈንታ የዘራፊዎች የጥቃት ሰለባዎች ለሆኑ ድንገተኛ ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት በመስጠት መጠመዱ ሌላ ጫና እንደፈጠረበት ተገልፀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#TigrayRadio

@tikvahethiopia            
" ከ2013 ዓ/ም በፊት በአከባቢው ሰላም እና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ " - ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " ለአመታት ከቄያቸው ተፈናቅለው በትግራይ የተለያዩ ከተሞች እና በሱዳን የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ወደ አከባቢያቸው ለመመለስ የተያዘው የጋራ እቅድ የዘገየው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተፈጠረ ችግር አይደለም " ብለዋል።

" የነበረ ክፍተት ተገምግሞ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ም/ፕሬዜዳንቱ ፥ " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ አከባቢያቸው የመመለስ ስራ የራያ እና ፀለምቲ ተፈናቃዮች በመመልስ የተገኘው ልምድ መስረት በማድረግ ይፈጸማል " ብለዋል። 

" ተፈናቃዮችን የመመለስ ተግባሩን የሚያቆም አካል የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የምዕራብ ትግራይ የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ ያለመ የሰፈራ ስራ በአማራ መንግስት ተካሂደዋል " ያሉት ሌ/ጀነራሉ " ከሌሎች አከባቢዎች ወደ ምዕራብ ትግራይ ገብተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ታጣቂዎች እንዲወጡ ይሰራል " ብለዋል።

" ከ2013 ዓ.ም በፊት በአከባቢው ሰላምና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ "  በማለትም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ቀላል እና ከባድ ወንጀሎች በመፈፀም ላይ እንዳሉ ተናግረው በአጭር ጊዜ ወንጀል ፈጻሚዎችን ወደ ተጠያቂነት ለመሸጋገር የሚስችል ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል።

በከባባድ ወንጀል በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አመልክተዋል።

እነማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ? የሚለውን በዝርዝር አልተናግሩም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Mekelle

መቐለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 14 የመኪና የማደሪያ ቦታዎች (ፓርክ የሚደረግበት) 140 ባለቤትነታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ማግኘቱ የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ በመቐለ ከተማ የመኪና ማደሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ አድርጎ ነበር።

በዚህም140 ባለቤታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ሊገኙ እንደቻሉ ገልጿል።

የተገኙት ተሽከርካሪዎች ባለቤትነታቸው ለማወቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

" ባለንብረት ነኝ " የሚል አካል ማረጋገጫ ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይችላል ተብሏል።

የመቐለ ፓሊስ ከተሽከርካሪ ፣ ብረታብረትና ሌሎች ንብረቶች ጋር ተያይዞ የማጣራት ስራ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

የሚካሄደው ምርመራ ግኝቶች በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሐምሌ 4 ባወጣው መግለጫ በክልሉ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ መግለፁ መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia