TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የማህበራዊ ሚዲያ ህግ እየተዘጋጀ ነው‼️

በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚለጠፉ መረጃዎች #ትክክለኛነታቸውንና በህዝቦች መካከል #ግጭት የማይፈጥሩ መሆናቸውን #ለማረጋገጥ መንግስት ህጋዊ አሰራርን ሊተገብር ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ አክለውም ህጉ ትክክለኛነታቸው ሳይረጋገጥ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሚሰራጩ መረጃዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችና #አለመግባባቶችን ከማስቀረቱም ባሻገር የዜጎችን #ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ተቋምወርቅ አሰፋ ይህን ብለዋል፦

"ፌስቡክ እውነትም ውሸትም አለው፤ በአሁኑ ሰዓት አልጠቀምም ብትል ከሚዲያ #ትርቃለህ እጠቀማለሁ ስትል ደግሞ #እውነታነቱ የቱ ጋር ነው ፌስቡክ አዘጋጆቹ ራሳቸው እነርሱ ናቸው የሚያውቁት መረጃውን የሚሰጠው አካል እውነታነቱ የቱጋ ነው ብሎ ሲያበቃ ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉትን መንግስት #በህግ ሊከታተላቸው ይገባል˝ ብለዋል።
.
.
በሌላ በኩል...

በኢትዮጵያ ከማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስርዓት ያለው አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል ህግ #እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አህመድ በዚህ ሳምንት በህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የሚዲያ ነጻነት ሲባል በውሸት ስም ገፅ በመክፈት፣ ማንነትን በመደበቅ፣ ያልተገቡ ተግባራትን በማከናወን አይደለም” ሳይሆን ለአገርና ለህዝብ ግንባታ የሚውሉ ቁምነገሮችን በማሰራጨት መሆን ይገባልም ብለዋል።

ህጉ “በተደራጀ መልኩ ደመወዝ እየተከፈላቸው፤ አንዴ ኦሮሞ ሌላ ጊዜ ደግሞ አማራ፤ አንዱ ቦታ ሴት ፣ ሌላ ቦታ ደግሞ ወንድ ሌላም ሌላም በመሆን የሚሰሩ ሰዎችንም” #ተጠያቂ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።

የዚህ ዓይነቱን የማሕበራዊ ሚዲያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለመከላከልም ዋነኛው መፍትሔ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛውን መረጃ ፈጥነው ለህዝብ ማድረስ መቻል መሆኑንም በአጽንኦት ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia