TIKVAH-ETHIOPIA
1.49M subscribers
56.5K photos
1.41K videos
203 files
3.84K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። መረጃው  የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው። @tikvahethiopia
#Update

" አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው " - በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ

በጋሞ ዞን፣ ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካማአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ በደረሰ የናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይወቃል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ከሰላሳ ሰባት በላይ የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ 15 ቤቶችም መፍረሳቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የሟቾችን ቀብር ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በክብር አስፈጽመናል " ብለዋል።

በአካባቢዉ ችግር ይከሰታል የሚል ቅድመ ትንበያም ይሁን ግምት ፈጽሞ እንዳልነበር ይልቁኑ በቀርከሀ የተሞላ ደን እያለ አደጋዉ መከሰቱ ሁኔታዉን አስደንጋጭ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል።

አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል መሆናቸዉን የገለጹት አስተዳዳሪው በአንድ ቤት ዉስጥ ከነበሩት ሰባት ሰዎች ውስጥ በጓዳ የነበሩት አራቱ ሞተው ሶስቱ ከጓዳ ወጭ የነበሩት መትረፋቸውን ነግረውናል።

የሟቾች ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመ በኃላ ወደ ቀጣይ ተግባር ተገብቷል ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ የዝናቡ መጠን ከፍ እንደሚል መረጃ ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት እንቅስቃሴ መጀመሩንና የአካባቢውን ሰው በማሸሽ በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የጤና ኬላዎችና የእምነት ቦታዎች ማሳረፍ መጀመሩን አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? ዛሬ መቐለ ሁለት ስብሰባ ሲካሄድ ውሏል። አንዱ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚገኙበት 14ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን ሌላኛው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ጉባኤውም የተቃወሙ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ የክልል፣ የዞን እና ወረዳ አመራሮች የተገኙበት…
#Update

በህወሓት ምትክል ሊቀመንበር እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው የዛሬው የመቐለው ስብሰባ ቁጥራቸው አንድ ሺህ መሆኑ የህወሓት አባላትና አመራሮች ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የአንድ ቀን ስብሰባቸውን ከምሽቱ 2:30 አጠናቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ካወጡዋቸው ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አራቱ ነጥቦች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈጠረው አንፃራዊ ምቹ ሁኔታ እንዲቀጥል የሚያስታውስ ነው።

" ሰላም አማራጭ የሌለው አማራጭ መሆኑ በመቀበልና በመረዳት ማንኛውም ወደ ግጭትና ጦርነት የሚመራ የውስጥና የውጭ ተንኮል በፅኑ እንቃወማለን " ይላል።

በአቋም መግለጫው ከተገለፁ አራት ነጥቦች  በህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው ጉባኤ ኢ-ህጋዊነት የሚያትት ሆኖ " ተደናግረው በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የህወሓት አባላት ወደ ቀልባቸው በመመለስ ከህዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ " ሲል ያሳስባል።

ዘጠነኛው ነጥብ ደግሞ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው የክልሉ ተወላጅ ፣ የድርጅቱ አባልና ደጋፊ ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ማህበራት ፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ደግፈው እንዲቆሙ ጥሪ ያቀርባል።

" የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች በድርጅታችን ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብ ልዩነት እንደ ሁሉ ጊዜ በጥሞና በማየት በማያዳላ መንገድ የህዝቡ ፀጥታና ሰላም ማስከበር ይገባል " ያለው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስረኛ ነጥብ የአቋም መግለጫ የፀጥታ ሃይሎች አሁን የያዙት የማያዳላ አቋም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርበዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

Via @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል በማለት በቁጥጥር ስር አውሎ የሽብር ወንጀል ምርመራ የከፈተባቸውን 6 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ማንነት የሚያሳይ ፎቶ ይፋ አድርጓል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው በሀገራችን ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት " ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ አውሮፕላን…
#Update

የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ ፈጥረዋል የተባሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ ፈጥረዋል የተባሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው…
#Update

የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።

የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አሜሪካ በህወሓት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ጠየቀች። ትላንት ትግራይ ፣ መቐለ የገቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያይተዋል። በዚህም ወቅት በህወሓትና በጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት መርገብ እንዳለበት አሳስበዋል።  አምባሳደሩ ውጥረቱ እንዲረግብ ከሰጡት…
#Update
 
የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የህወሓት ቡድን ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል።

በህወሓት የማህበራዊ  የትሰስር ገፅ የተሰራጨው መረጃ እንዳለው ፤ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያና በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር (ማለትም በቅርቡ በተካሄደው ጉባኤ ከተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ) እና ሌሎች አመራሮች ጋር ተወያይቷል። 

አምባሳደሩ በውይይቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲፈፀም አገራቸው አሜሪካ እንደምትደግፍ ተናግረዋል።

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ትላንት " በህወሓት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ " በማስመልከት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር መወያየታቸውን መዘገባችን ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሪልስቴት #አዲስአበባ ° “ ብራችንን እኔ አውጥተን ተሰቃየን ” - የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዥዎች ° “ የመብራት፣ የውሃ፣ የውሃ ታንከር ጥያቄ አለ ትክክል ነው ” - ኖህ ሪልስቴት በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በኖህ ሪልስቴት ' የኖህ አያት ግሪን ፖርክ ቤት ' ገዢዎች ኖህ የገባውን ውል በመዘንጋት የቤት መሠረተ ልማቶችን እያሟላ እንዳልሆነ እና በጠበቃቸው በኩል ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ…
#ሪልስቴት #Update

" ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል " - የኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች

"...ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም  " - ኖህ ሪልስቴት

የኖህ ሪልስቴት ሀያት ግሪን ቤት ገዢዎች ድርጅቱ በውሉ መሠረት የቤቱን መሠረተ ልማት እንዳላሟላላቸው በድጋሚ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ቅሬታቸውን ያቀረቡ በርካታ ገዢዎች፣ ድርጅቱ በገባው ውል መሠረት መብራት፣ ውሃ፣ ጀነሬተር መሠረተ ልማቶች ባለሟሟላቱ ችግር ላይ እንደወደቁ ገልጸዋል።

መሠረተ ልማቱ ሳይጠናቀቅ የቤት ኪራይ ሽሽት ቤታቸው የገቡ ገዢዎች ያለ መሠረተ ልማት ከ1 ዓመት በላይ እንተቀመጡ በምሬት ተናግረዋል፡፡

መሠረተ ልማቱ እስከሚጠናቀቅ በኪራይ ቤት ሆነው እየጠበቁ ያሉ ገዢዎችም፣ ቤቱን ለመግዛት እስከ 4 ሚሊዮን ብር አውጥተው ሳለ መሠረተ ልማቱ ባለመጠናቀቁ አሁንም በቤት ኪራይ ወጪ እየተበዘበዙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ወደ ቤታቸው ያልገቡበትን ምክንያት ሲያስረዱም፣ " ቤት ገብተው የሚኖሩ ሰዎች አሉ በጣም ነው የሚያሳዝኑት መብራትና ውሃ ስለሌለ እንጀራ ጋግረው አያውቁም እሱን እያየን ለመግባት ተቸግረል " ነው ያሉት።

ከዚህ ቀደም መሠረተ ልማቱን በወር ከ15 ቀን ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ በሚዲያ በኩል ቃል ገብቶላቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ግን ምንም ሳይሰራ ወራቶች እንደጠቆጠሩ ተናግረዋል።

ውሃው ግቢ ውስጥ ገብቷል ከተባለ ብዙ ጊዜ እንዳስቆጠረ፣ ነገር ግን አገልግሎት ላይ እንዳልዋለ፣ በዚህም የከፋ ችግር ለማሳለፍ እንደተገደዱ ነው የገለጹት፡፡

ድርጅቱ ይባስ ብሎ ቤቱ ሳያጠናቅቅ ጥበቃዎችን እያስወጣ መሆኑን፣ የከተማዋ ከንቲባ ሳይቱን የመረቁት ሳይጠናቀቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

ላደረባቸው ቅሬታ ምላሽ ቢሮ ድረስ ሂደው ቢጠይቁም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አስረድተው፣ አሁንም መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅናቸው የኖህ የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ የሴፍ ደስታ፣ አጭር የመከላከያ ሀሳብ ከመስጠት ውጪ በቀጥታ ለቅሬታው ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

" በጠበቃቸው አማካኝነት እየተከታተሉ ስለሆነና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመሄድ ዕድል ስላለው የድርጅቱን የመከራከር መብት የሚያጣብብ ስለሚሆን ለፕሬስ መግለጫ አልሰጥም " ነው ያሉት።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ስለቅሬታው ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ፣ " ትክክል ነው የመብራት፣ የውሃ፣ ታንከር ጥያቄ አለ " ብሎ ይህ የገጠመው በተለያዩ ችግሮች እንደሆነ ገልጾ ነበር።

በወቅቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤቱን መቼ አጠናቃችሁ ታስረክቧቸዋላችሁ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡት ምሌሽ፣ " ነገ ቢሆን ደስ ይለኛል፡፡ 654 ቤቶችን ሰርተን መብራት ለማስገባት የምንዘገይበት ምክንያት እኔ ራሱ አልገባኝም " ነበር ያሉት።

" ስለዚህ በጣም በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለመስራት እየሞከርን ነው " ማለታቸው ይታወሳል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ትኩረት🚨

ዛሬም ድረስ የሰው ህይወት የሚቀጠፍባቸው የመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች " በፈጣሪ ስም መፍትሄ ይፈለግልን ፤ ተሰቃየን ህይወታችን በሰቀቀን መግፋት ደከመን " ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርበዋል።

" ተደጋጋሚ እርቅ ይፈጸማል ግን ሳይቆይ ያገረሽና ደም ይፈሳል፣ ሰው ይገደላል የምንገባበት አጣን ድምጻችን ይሰማ " ብለዋል።

ከሰሞኑን በመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የአካባቢዉ ባለስልጣናት መታሰራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ባለፉት ጊዜያት የነበረዉ የንጹሀን ግድያ  ለተወሰነ ጊዜ ረገብ ቢልም ከሰሞኑ እንደገና ባገረሸ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 4 ሰዎች ደግም ቆስለዋል።

ይህን ተከትሎ አካባቢዉ ውጥረት ዉስጥ በመግባቱ አሁን ላይ በአካባቢዉ የሚኖሩ ንጹሀን በፍርሀት ውስጥ ናቸው።

" ኢንሴኖ ከተማና አካባቢው በየጊዜው በሚነሳው ግጭት ገጠራማው ቀበሌ የሚኖረው ምስኪን ግድያ ሲፈጸምበት ቆይቷል " የሚሉት ነዋሪዎቹ " በአካባቢው ሲስተዋል የነበረዉ የበቀል መጠፋፋት አሁንም በከፋ ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል በሚል ተጨንቀናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑ በማረቆ ልዩ ወረዳ በሌሊት በተፈጸመ ጥቃት የ7 ሰዎች ህይወት (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት) እንዲሁም በመስቃን ደግሞ 2 ሰዎች ህይወታቸው መቀጠፉን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ ሁኔታውን የመንግስት አካላት ቶሎ ካልተቆጣጠሩት ግጭቱ ከፍ ሊል ይችላል ሲሉ ፍርሀታቸውን አስረድተዋል።

ስለሁኔታዉ የጠየቅናቸዉ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዉ አቶ ተካልኝ ንጉሴ ስለሁኔታው መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ይሁንና በልዩ ወረዳዎቹ ግድያ መፈጸሙን ተከትሎ አካባቢውን ለማረጋጋት ወደቦታው ያቀናው የጸጥታ ኃይል ጥቂት የአካባቢው ግለሰቦችን ጨምሮ ግጭት በተፈጠረባቸዉ አካባቢዎች ለጊዜዉ ስማቸዉ አይጠቀስ የተባሉ የወረዳ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

አሁን ላይ ኢንሴኖን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት ተሰማርተው ህዝቡን እያረጋጉ ሲሆን የህዝቡ እንቅስቃሴ ግን በጅጉ መቀዛቀዝ ይስተዋልበታል።

ይህ አካባቢ በተደጋጋሚ የሰዎች ህይወት የሚቀጠፍበት ፣ ዜጎች የሚፈናቀሉበት ሲሆን ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ ሳይገኘ ዛሬም በዛው ቀጥሏል።

#Update : ከመሸ ስልክ ያነሱልን የምስራቅ ጉራጌ ወንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር መሀመድ ሀሰን " አሁን ላይ ሁሉም አካባቢ ሰላም " መሆኑን ጠቅሰው ስለሁኔታው አሁን ላይ መረጃ መስጠት ከባድ መሆኑን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በረራውን ለማቋረጥ የተገደድኩት ገንዘብ እንዳላንቀሳቅስ በመታገዴ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 20፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ ጽፎ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ አየር መንገዱ በሰጠው መግለጫ ውሳኔው ይሻሻላል በሚል ሲጠብቅ እንደነበር እና የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንን ለማናገር በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ አለማሳካቱን አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመግለጫው እንደጠቀሱት በአስመራ የሚገኘው ተወካያቸው ከሽያጭ የተሰበሰበ ገንዘብ ለማስገባት ሲል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላክ እንደማይቻል ተነግሮታል። ይህ የሆነው ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አማካኝነት ነው።

" ' ከነሐሴ 25/ 2016 ዓ.ም በኋላ ሂሳባችሁ ታግዷል ለሀገር ውስጥ ወጪም (oppration fee) መጠቀም አትችሉም ' መባሉን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ በረራውን ለማቋረጥ ተገደናል። የበረራ ወጪያችንን መሸፈን ባለመቻላችን ተገደን ወጥተናል " ሲሉ ነው የገለጹት።

አየር መንገዱ እንዳያንቀሳቅስ የታገደበት ገንዘብ መጠን ስንት ነው ?

ይህ ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የገንዘቡን መጠን ከመግለጽ ተቆጥበው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ በኤርትራ ሁለት አካውንት እንዳለው የገለጹት አቶ መስፍን፥ አንዱ የናቅፋ አካውንት ሲሆን የቆየ እንዲሁም ወደ ዶላር መቀየር ያልተቻለ የማይንቀሳቀስ የሂሳብ አካውንት መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው የባንክ አካውንት ደግሞ የዶላር ሲሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኬት ሲሸጥ የነበረው በውጭ ምንዛሬ መሆኑን ገልጸው ይህንን ገንዘብም እገዳው እስከተላለፈበት ቀን ድረስ በተለያዩ ጊዜዎች ገንዘቡን ሲያንቀሳቅስ እንደነበረ ገልጸዋል።

" የበረራ እገዳውን ካወጡብን በኋላ ነው Block ያደረጉብን " ሲሉ ነው የገለጹት።

አቶ መስፍን አክለውም ፥ "ለእኛ ገንዘቡ ካልተለቀቀልን ከዚህ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ ነው የሚሆነው " ሲሉ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ለሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን እና ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን ገልጸዋል።

" አየር መንገዱ ከኤርትራ የወጣው ተገዶ ነው " ያሉት አቶ መስፍን ዋናው ችግሩ ለምን እንደታገድን አለማወቃችን ነው፤ በተጻፈው ደብዳቤም ላይ ምንም የተገለጸ ነገር የለም ብለዋል።

" ከዚህም በተጨማሪ በደብዳቤም በስልክም ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም " ሲሉ ገልጸዋል።

የአየር ቀጠናውን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሁን ባለው ሁኔታ በኤርትራ የአየር ክልል መብረር እንዳልተከለከሉ ገልጸው የሚያስገድድ ጉዳይ ካለ ግን አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ አንስተዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#UPDATE

በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ የተደረገው ማስተካከያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13/2016 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት የታሪፍ ማሻሻያው ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ የታሪፍ ጭማሪው የደንበኞችን የኃይል የአጠቃቀም መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም፦

የቤት ደንበኞች፤ የንግድ ተቋማት፤ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፤ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።

የቤት መብራት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ " እንደ አጠቃቀማቸው አሁን ከሚከፍሉት እና ጭማሪ ከተደረገበት መካከል ያለውን ልዩነት ሲከፍሉ እንደ አጠቃቀማቸው ድጎማ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

ድጎማው ምን ይመስላል ?

50kW በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

ከ50kW - 100KW ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

200kW - 300 Kw ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

400kW - 500 KW የሚሆነውን ማሻሻያውን ያለምንም ድጎማ ይከፍላሉ

ከ500kW በላይ የሚሆነውን ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።

የአከፋፈሉ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ይህ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያው (የተጨመረው 6 ብር) የሚከፈለው በአንድ ጊዜ ሳይሆን በ16 ዙር በሚደረግ የሂሳብ ማስተካከያ [ከመስከረም 1 /2017 ጀምሮ] በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ሽፈራው ይሄንን ሲያስረዱ 50KW የሚጠቀሙ ደንበኞች አሁን የሚከፍሉት 27 ሳንቲም እንደሆነ ገልጸው ከመስከረም ጀምሮ የሚከፍሉት 35 ሳንቲም ይሆናል ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ [በ16 ዙሮች በሚደረግ ማስተካከያ] 1.56 ብር መክፈል ይጀምራሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ያለው ጫና ተጠንቷል ወይ ?

ይህ ጥያቄ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ሲሆን በሰጡት ምላሽ በዚህ ላይ ጥናት መደረጉን ጠቅሰው ይህም #ከአራት_ዓመት በኋላ የሚኖረው ተጽዕኖ 2 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል።

" ከአከራይ ተከራይ ጋር ያለው ተጽዕኖም በጣም አነስተኛ ነው፤ የሚያጣላቸው ነገር አይኖርም " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ይህ የታሪፍ ማሻሻያው በዋነኛነት የወጣበትን ወጪ ለመሸፈን (A cost reflective tariff) መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

#ማብራሪያ: ከላይ የተያያዘው ሰንጠረዥ ድጎማ የተደረገበት የሂሳብ ታሪፍ ሲሆን። በዓመት 4 ጊዜ በ4 ዓመት ደግሞ 16 ጊዜ የሚተገበር የሂሳብ ማስተካከያ የያዘ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል። ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል። ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት…
#UPDATE

" የጤናዬ ሁኔታ ብዙ የሚያሳስብ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም በ X ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት በማስቀደም " የጤንነት ሁኔታየና ድህንነቴ ያሳሰባችሁና ያስጨነቃችሁ ሁላችሁም ደህና ነኝ " ብለዋል። 

" ተደጋጋሚ ረጅም መንገድ በመኪና መጓዝና ደካም ተደራርቦ የፈጠረው ጊዚያዊ ችግር እንጂ በሚያሳስብ ሁኔታ እንዳልሆንኩ በፈጣሪና በፅዮን ማርያም ስም እገልፅላችኃለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።   

ቀጣይ ህዝባዊ መድረኮች ከተወሰኑ ቀናት በኋላ እንደሚቀጥሉ የገለፁት አቶ ጌታቸው " በመድረኩ ለመሳተፍ አክሱም ድረስ ለተንገላቱ ተሳታፊዎች ደግሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ " በማለት አክለዋል።   

ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም ከጊዚያዊ  አስተዳደሩ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የወጣ መግለጫ ፕሬዜዳንቱ የጤና እከለ እንደገጠማቸው በመግለፅ በአክሱም ከተማ ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉና ይቅርታ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia