TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
° “ ልጄ በሕይወት ስለመኖሯ እርግጠኛ አይደለሁም ” - ልጄ ተጠለፈች ያሉ አባት

° “ የልጅቷን አባት መስለው ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉ አሉ ” - የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ 

° “ በ2015 ዓ/ም ብቻ 23 ሴቶች ጠለፋና አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል ” - የዞኑ ፍትህ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጠለፋና እየተስፋፋ መሆኑን፣ በዚህም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንዳልቻሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

አቶ ወንድሙ ወዬሳ የተባሉ የዞኑ ነዋሪ ባለፈው ወር የማርያም የተባለች ልጃቸውን “ ጉልበተኞች ምሽት 3 ሰዓት በራቸውን ሰብረው ጠልፈው ዱልኬ ” ወደሚባል ቦታ እንደወሰዷት፣ ጠላፊዎቹ ከተያዙ በኋላ ከእስር እንደተለቀቁ በማህበራዊ ሚዲያ ሲገልጹ ተስተውለዋል።

“ ልጄ በሕይወት ስለመኖራ እርግጠኛ አይደለሁም ” ያሉት እኝሁ አባት፣ የጠላፊ ቤተሰቦች ይባስ ብለው ሽምግልና እንደላኩ፣ በዚህም እኝሁ አባት ለጸጥታ አካላት አሳውቀው ቢያሳስሯቸውም እንደተለቀቁ ፣ የጠላፊ ቤተሰቦችም #ፌዝ እና #ዛቻ እያደረሱባቸው በመሆኑ የዞኑ አካላት ፍትህ እንዲሰጧቸው ጠይቀው ነበር።

ይህች ልጅ በጠላፊዎች እጅ 2 ወር በላይ ሆኗታል።

ከዚህ ባለፈ ደስታ ደመቀ የተባለች ልጃገረድ ተጠልፋ የተወሰደች ሲሆን በጠላፊዎች እጅ ከወር በላይ እንደሆናት ተሰምቷል።

እንደ አጠቃላይ ያለውን የጠለፋን ወንጀል በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸውና ስሜ ባይጠቀስ ያሉ የዞሬ ዞን ፍትህ መምሪያ አካል፣ “#ችግሮቹ አሉ። ጠላፋዎቹ ከትምህርት ቤት መልስም ይፈጸማሉ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ለሚስትነት የሚጠለፉ አይመስልም። ጠላፊዎቹ ወደ ሱዳን በኩል ወርቅ አለ በጅማ በኩል የሚጓዙበት ‘በዚያ አካባቢ የሚመጡ ሎሌዎች ናቸው’ ነው የሚባለው። ይህ የሚሆነው ጎርካ ወረዳ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የየማርያምን ጨምሮ በ2016 ዓ/ም የተፈጸሙትን የጠለፋ ወንጀሎች በተመለከተ ገና መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ገልጸው፣ “ በ2015 ዓ/ም 23 ሴቶች የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል ” ብለዋል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ በበኩላቸው፣ “ ሚዲያ ላይ የሚባለው መሬት ላይ አለ ወይስ የለም ? የሚለውን በሚባለው ክላስተር ላይ ሂጄ የሃይማኖት አባቶችን፣ አረጋዊያንን ለማማከር ሞክሬአለሁ። አሁን በሚባለው ልክ አይደለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ‘ከፓሊስ ጣቢያ ሰው እየተለቀቀ ነው’ የሚለው ነገር ስም ለማጥፋትና ዞኑን ለማጠልሸት እየተደረገ ያለ ነው ” ያሉት አቶ ታረቀኝ፣ “ የልጅቷን አባት መስለው ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉ አሉ። ቃለ መጠይቅም ራሱ አርሶ አደር መስሎ የሚሰጥ አለ ” ነው ያሉት።

የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንደሮ በበኩላቸው፣ ከወረዳው ወደ ዞን የቀረበላቸው ቅሬታ እንደሌለ፣ ጎርካ ወረዳ ለመረጃ ሩቅ በመሆኑ ጉዳዩን እንዳልሰሙ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia