" ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈተ ህይወት ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ ነው " - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ህይወቷ አልፏል።
ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን ሞት 'ድንገተኛ ህልፈት' በማለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክት አሰራጭቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዋ ' #በጩቤ_ተወግታ ህይወቷ እንዳለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎችን ተመልክቷል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯል።
በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራር፤ " ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈት ጋር በተያያዘ የጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያደረገ ይገኛል " ብለዋል።
" በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ ጉዳዩ ገና በፖሊስ የተያዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን አስክሬን ወደቤተሰቦቿ አሸኛኘት ማድረጉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
Via @tikvahuniversity