TIKVAH-ETHIOPIA
1.41M subscribers
55K photos
1.37K videos
199 files
3.67K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #TPLF

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ።

አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል።

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ህወሓት / TPLF / ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለውን መንገድ የሚጠርግ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት አገልግሎት መስጠት የጀመረው በመቐለ ከተማና አከባቢዋ ነው።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎት መስጠት ስለመጀመሩ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በ2 ምዕራፎች 16 የትግራይ ከተሞች የ4G እንዲሁም የ5G የሞባይል ዳታ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Axum #Tigray

" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "

ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦

" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው።  ብርሃን አየን።

በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።

ብዙ ለውጥ ነው ያለው።

በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን  መተኛት እንችላለን።

ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "

#Ethiopia #TigrayRegion #Peace

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው #ሰኔ_ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል። አየር መንገዱ #ከሰኔ_10_ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል። በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል። ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።…
ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ  ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል።

በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር።

የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

በረራው እንዲጀመር በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በረራው እንዲጀመር የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አክሱም መደበኛ በረራ እንደሚጀመር ማሳወቁ ይታወሳል።

#Ethiopia #Tigray #Axum

Photo Credit - Tigray TV

@tikvahethiopia            
 #Tigray

በአንድ ቀን ብቻ የ 7 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ ሲቀጠፍ ከ20 በላይ ሰዎች የአከል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከሟቾቹ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

የትራፊክ አደጋው ያጋጠመው ግንቦት 28/2016 ዓ.ም በአንድ ቀን በሁለት የትግራይ አከባቢዎች ነው።

ከዓድዋ ከተማ ወደ ጥንታዊትዋ የይሓ የቱሪስት ማእከል በየዓመቱ የሚከበረውን የቤተክርስትያን ዝክር ለማክበር በግል መኪና ሲጓዙ የነበሩት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ አራቱ ለህልፈት ሲዳረጉ ፤ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

በዚያው በተመሳሳይ ቀን በሓውዜን ወረዳ ሙሽሮች የጫነ መኪና ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

የአደጋዎቹ መነሻ በማይመች ቦታ ከሚፈቀደው በላይ መፈጥንና መጫን መሆኑ የትራፊክ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለሰው ደህንነት ትኩረት ሰጥተው እንዲያሽከርክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Axum የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።  በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ  የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል። እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ  አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ…
#Axum #Update
 
የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ ከሶስት ዓመት በኃላ ዛሬ እሁድ ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት የመጀመሪያውን ይፋዊ የአውሮፕላን  በረራ አስተናግዷል።

የዳግም በራራ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የክልል እና የፌደራል ባለስልጣናት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በቦታው የሚገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከው መረጃ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አዲስ አበባ ተነስቶ ከቀኑ 6:00 ላይ አክሱም የደረሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-700 አውሮፕላን 140 ተጓዦች ይዟል።

ከተጓዦቹ ውስጥም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ  አስተዳደር ፕረዜዴንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Axum #Ethiopia #Tigray

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል። ዛሬ ዓርብ ግንቦት 16 / 2016 በተጣለ ተተኳሽ ባል እና ሚስት ህይወታቸው አልፏል። አደጋው ያጋጠመው በትግራይ ክልል ፣ በማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ምረረ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲሆን በተተኳሹ ምክንያት የባል ህይወት ወድያው አልፏል። የሟች ሚስት ወደ…
#Tigray🚨

በሓውዜን ወረዳ በተጣለ ተተኳሽ #የ4_ሰዎች ህይወት ጠፋ።
 
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

ሰኔ 1/2016 ዓ.ም በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ፤ ሓውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በፈነዳ ተተኳሽ የ4 ወገኖች ህይወት #ተቀጥፏል

ከአራቱ የአደጋው ሰለባዎች ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሓውዜን ወረዳ ኮሙኒኬሽን ባገኘው መረጃ  ፥ ሟቾቹ ከ 9 እስከ 14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ገና ትንንሽ ልጆች ናቸው።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የሰኔ 1/2016 ዓ/ም አደጋን ጨምሮ በትግራይ የተለያዩ ወረዳዎች በተጣሉ እና በተቀበሩ  ተተኳሾችና ፈንጂዎች ከ107 ሰዎች ላይ የሞት ፣ የአካል መጉደል አደጋ ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#Tigray

ህዝቡ በህብረት ስራ ማህበራት ስም ከሚፈፀሙ #የማደናገር እና #የማጭበርበር ተግባራት ራሱ እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ።

ይህን የማስጠንቅያ ጥሪ ያቀረቡት የትግራይ ፍትህ ቢሮና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ ሆነው ነው።

መንግስታዊ ተቋማቱ  " አቦ " በሚል ስያሜ በቤቶች ግንባታና ልማት " ተሰማርቻለሁ ... ተመዝገቡ የቤት ባለቤት ሁኑ " በሚል እንቅስቃሴ በማካሄድ የሚገኘው የህብረት ስራ ማህበር እውግዘዋል ፤  እግድም ጥለዋል።

መንግስታዊ ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ ፥ " አቦ " በሚል ስም የሚታወቀው የህብረት ስራ ማህበር ፥ " ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ በጋራ በትግራይ 5 ከተሞች ቤቶች ገንብቼ አስረክባሎህ " ብሎ ከሰነ 3/2016 ዓ.ም ያስጀመረው የምዝገባ እንቅስቃሴ ህጋዊ አይደለም  ብለዋል።

" አቦ " የተባለ የህብረት ስራ ማህበር በ5 የትግራይ ከተሞች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ የተሰጠው መሬት የለም ያለው የትግራይ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲታቀብ አስጠንቅቋል።

የመኖሪያ የቤቶች ግንባታ በህብረት ስራ ማህበር የማደራጀት ስልጣን የተሰጠው ለፍትህ ቢሮ ነው ያለው የክልሉ ፍትህ ቢሮ ፥ " አቦ የቤቶች ግንባታ ህብረት ስራ ማህበር " በህግ ባልተፈቀደለት የስራ ዘርፍ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ እግድ እንደጣለበት አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia            
#Tigray
 
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከነገ ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ የ8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አመልክቷል።

እንደ ቢሮው መረጃ ፈተናው ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም ምኞታቸው ገልጸው ተረጋግተው ፈተናቸው እንዲሰሩ አደራ ብለዋል።

@tikvahethiopia