TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦብነግ አቋም በአይኤስ/IS/ ላይ...

"ማንኛውም የውጪ ኃይል፤ የውጪ #ጠላት ሀገራችን ውስጥ ቢገባ አብረን ሆነን ነው #የምንዋጋው።...ከአሁን በፊትም የነሱ /Affiliates/ተባባሪዎች/ የሆኑትን ተዋግተን አስወጥተናቸው ነበር ድሮ ከ15 ዓመት በፊት፤ የተፈጠረው ሰላም እንዳይደፈርስ ከክልሉ መንግስት ጋር ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ሆነን አብረን እገዛ እያደረግን፤ እየተጋገዝን እንደዚህ አይነት ነገር በሀገራችን እንዳይፈጠር እንሰራለን" የኦብነግ/#ONLF የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ተጠሪ አቶ #ሀሰን_ሞኣልን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ONLF

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ከምርጫ ቦርድ በአገር አቀፍ ደረጃ መንቀሳቀስ የሚያስችለውን ህጋዊ እውቅና አግኝቷል።

@tsehabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ጥዋት የONLF ሊቀመንበር አብድራህማን ማሃዲ ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ሙሃመድ ፣ የሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ (PP) እና የONLF ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አድርገዋል ፤ በውይይታቸው የሱማሌ ክልልን ሰላም ፣ መረጋጋት እና መልካም አስተዳደር #ለማጠናከር መስማማታቸው ተሰምቷል - #ONLF

@tikvahethiopiaOfficial
#ONLF

የቀብሪደሃር ነዋሪዎች በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሁለተኛ (2) ዓመት አክበረዋል።

በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሰላም ስምምነቱ የተደረገው እንደእኤአ ጥቅምት 21/2018 በአስመራ ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ONLF

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ሶስት (3) ከፍተኛ አመራሮቹ መታሰራቸውን የፓርቲው ቃለ አቀባይ የሆኑት አብዱልከድር ሀሰን ኢርሞጌ አዳኒ ለBBC ሶማሊኛ ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ፦

- መሃመድ ጂግሬ ገመዲድ (የቆራሄ ዞን ሊቀመንበር)
- ተማም መሃመድ ማህሙድ (የቆራሄ ዞን ም/ሊቀመንበር)
- መሃመድ ኢብራሂም ሙርሳል (የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ለረዥም አመታት በስራ አስፈፃሚነት የሰሩ) ናቸው።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኡመር ፋሩቅ ወርፋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አረጋግጠዋል።

ኦብነግ ፣ ከክልሉ መንግሥት እና ከፌደራል መንግሥት ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጿል ፤ ችግሩ በድርድር እንደሚፈታም ተስፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

More : telegra.ph/ONLF-10-22

Via BBC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማስታወሻ📌ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል። *ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል። #ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ONLF

ኦብነግ ከሶማሊያ የሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ተሰረዘ።

የሶማሊያ ካቢኔ እ.ኤ.አ. በ2017 ( የቀድሞው ካቢኔ ) የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ን “አሸባሪ ድርጅት” ሲል ያሳለፈው ውሳኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሽሮታል።

ኦብነግ ከ5 ዓመት በኃላ ከሽብረተኛ ድርጅትነት ተሰርዟል።

ካቢኔው የኦብነግ ኮማንደር አብዲከሪም ሼክ ሙሴን ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠትንም “ህገወጥ” ሲል ገልጿል።

አብዲከሪም ሼክ ሙሴ እ.ኤ.አ. በ2018 በኢትዮጵያ ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ መንግስት ከእስር ነፃ መደረጋቸው ይታወሳል።

የዛሬው የሶማሊያ ካቢኔ ውሳኔ በ23 ድምጽ ድጋፍ ፣ በ1 ተቃውሞ እና በ1 ድምፀ ተአቅቦ ነው የፀደቀው።

ኦብነግ በትዊተር ገፁ በጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ እና በካቢኔያቸው ዛሬ የተላለፈውን ውሳኔ በደስታ መቀበሉን ገልፆ ውሳኔውን " ታሪካዊ ነው " ብሎታል።

ኢትዮጵያ እንደ እ.ኤ.አ. በ2018 የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)ን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ዝርዝር መሰረዟ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ONLF #SOMALIREGION

ከሰሞኑን ተቃዋሚው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ' የሶማሌ ክልል የዜጎች መብት የሚጣስበት እየሆነ ነው " ሲል ከሷል።

ፓርቲው ክልሉ ሶማሌዎች ማንነታቸውን እንዲክዱ የሚገደዱበት እየሆነ ነው ብሏል።

የክልሉን ስያሜና ሰንደቀላማ የመቀየር እቅድ እንዳለ ከአሉባልታ ከፍ ያለ መረጃ አለን ሲሉም፣ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዲራህማን መሀዲ ተናግረዋል።

ባለፉት 6 አመታት በክልሉ የጎሳ ግጭቶች ጨምረዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል።

የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች " እኛ ሶማሌዎች እንጂ ሶማሊያውያን አይደለንም " ማለታቸው ማንነትን እንደመካድ ሊወሰድባቸው አይገባም ብለዋል።

በቀድሞው አስተዳደር ህግን ባልተከተለ መንገድ ተቀይሮ የነበረውን ስያሜና ሰንደቅ አላማ በመተው በህገመንግስቱ የተቀመጠውን ስያሜ መጠቀም የጀመረው የእርሳቸው አስተዳደር መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሙስጠፋ የኦብነግ ሊቀመንበር የሚመሩት ቡድን ይህንን መግለጫ ያወጣው በክልሉ ችግር ስላለ ሳይሆን " ሰሞኑን በአፍሪካ ቀንድ እየተስተዋለ ያለውን ጂኦፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ ጥቅም በመፈለግ ነው " ሲሉ ተችተዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia