TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቡሬ

➡️ “ 15 ተፈናቃዮች ናቸው በሚሊሻ የተወሰዱት ” - በአማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች

➡️“ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” - አቶ ኃይሉ አዱኛ

በ2013 ዓ/ም ከኦሮማያ ክልል #ተፈናቅለው በአማራ ክልል ቡሬ ፣ ቻግኒ ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ባሕር ዳር የነበሩ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ወደ ወለጋ ለመመለስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ሰንቶም ቀበሌና ጣቦ የገጠር ከተማ ላይ ድንገተኛ ችግር እንደገጠማቸው አሳውቀዋል።

ተፈናቃዮቹ ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፣ “ እየሄድን እያለ ሶንቶምና ጣቦ ላይ አደጋ አጋጠመን። የሕዝብ ማዕበል መጣብን። ኬላ ላይ ተይዘን በ1ዐ ተሽከርካሪዎች የተሳፈርን ተፈናቃዮች አወረዱን እና ተሰቃየን በጣም ” ብለዋል።

“ ወጣቶች ድንጋይ፣ መሳሪያ ይዘው (ያልያዙት መሳሪያ የለም) ወጡ፣ ልክ አሸባሪ እንደሄደ እንጂ ተፈናቃይ አልመሰልናቸውም። ‘ከዚህ ቀደም በጦርነት ሲሳተፉ የነበሩ ናቸው’ እየተባለ ተፈናቃዮቹ እየተመረጡ ተያዙ ” ነው ያሉት።

“ 15 ተፈናቃዮች በሚሊሻ ተወስደዋል ፤ ሊገድሏቸው ሲሉ መከላከያ ወደ ካምፕ ወስዷቸዋል። ቀሪዎቹ ጫካ አድረን ወደ #ቡሬ_ተመልሰናል። በድንጋይ የተመቱ አሉ። ሰዎቹ ' እንደምትመጡ ማወቅ ነበረብን ጠብ እንዳንፈጥር ' ነው ያሉት ” ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈናቃዮቹን ወደ ምሥራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገር መከላከያ አጅቦ ሊመልሳቸው ፣ የወለጋ ኃላፊዎች ደግሞ ሊቀበሏቸው ቅድሚያ ቢነገራቸውም የሸኟቸው ሚሊሻዎች መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ አስረድተዋል።

ሚሊሻዎቹ ከዓባይ ወደዛ ለመሻገር ስላልቻሉ፣ የወለጋ ዞኖች ኃላፊዎችም ‘ ትዕዛዝ አልተሰጠንም ’ በማለት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከሞት አምልጠው ወደ ቡሬ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ለምን ጥበቃ እንዳልተደረገላቸው ጥያቄ የቀረበላቸው የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም፣ “ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” ነው ያሉት።

“ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ ካምፕ ያሉትን ቅድሚያ ተሰጥቶ በ1ኛው ዙር 1,600፣ በ2ኛው ከ400 በላይ ሰዎች ተመልሰዋል” ሲሉ አስታውሰው ፣ “ በሶስተኛው ዙር ለመመለስ ደግሞ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM