TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን ለመስቀል #ደመራ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕመናን ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት ይኖርባቸዋል " - ቤተክርስቲያን በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች። የደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ…
ፎቶ ፦ የመስቀል #ደመራ_በዓል በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ ፤ ብፁዓን አባቶች ፣ ምዕመናን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ እየተከበረ የሚገኘውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚያሳዩ ፎቶዎች / ቪድዮዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ የምንስቀምጥ ይሆናል።

የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን / ቪድዮዎችን በእጅ ስልካችሁ እያነሳችሁ የምትገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት @tikvah_eth_BOT ላይ ከስማችሁ ጋር መላክ ትችላላችሁ።

Photo Credit - EOTC TV

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
#ደመራ

ዛሬ ከሰዓታት በኃላ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቶች ወደመጠናቀቃቸው ነው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትላንት በዓሉን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

በዚህም በዓሉ በድምቀት ፣ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በሕብረት በመሆን ከጸጥታ አካላትና ቤተክርስቲያኒቱ ለዚሁ ዓላማ ካቋቋመቻቸው የኮሚቴ አባላት ጭምር በመተባበር እንዲሰራ አደራ ብለዋል።

የመንግሥት የጸጥታ ተቋማት በዓሉ ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ተከብሮ መዋል እንዲችል ከጠቅላይ ቤተክህነት ዐቢይ ኮሚቴ ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በበዓሉ ወቅት ለሚደረግ ፍተሻ ፍፁም ክርስቲያናዊ ትብብር እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።

የጸጥታ አስከባሪዎችም ጨዋነት በተሞላና ክብርን በሚገልጽ አግባብ የፍተሻ ሥርዓቱን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ ከበዓላችን መንፈሳዊ ሥርዓት ውጪ የሆኑ መልዕክቶች፣ አለባበሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫ ከሆኑ ዓርማዎች ውጭ መያዝ አይገባውም ብለዋል።

በዓሉ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያኒቱን ከማይገልጹ ሆታዎችና ጭፈራዎች እንዲርቅ አሳስበዋል።

" የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸው ቦታዎች ሁሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት ፍጹም መንፈሳዊ የሆነውን በዓላችንን የሚያደበዝዘው ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል " ብለዋል።

" ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችን ከሚያቀርቡት መንፈሳዊ ትርኢትና ዝማሬ ጎን ለጎን አካባቢያቸውን በመቆጣጠር በዓላችንን በሰላም እንዳናከብር የሚያደርጉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ በጥንቃቄ መጠበቅ ይኖርባቸዋል " ብለዋል።

" ብፁዕነታቸው ከንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ወዲህ ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሦስተኛ ጊዜ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የስቴጅ፣ የድምጽ ማጉያና የክብር እንግዶች ማስተናገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት ተሳትፎ አድርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህን ተሳትፎም አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

" በዓሉን ስናከብር ፍቅር ሰላምንና አንድነትን እንዲሁም መግባባትን መርሕ ባደረገ አግባብ መሆን አለበት " ያሉ ሲሆን " በዓሉ ሥጋዊ ፈቃዶቻችንን የምንፈጽምበት ሳይሆን ፦
- ንስሐ ያልገቡ ንስሐ የሚገቡበት
- የተጣሉ የሚታረቁበት
- የተለያዩ አንድ የሚሆኑበት
- የተራራቁ የሚቀራረቡበት
- ፍፁም የደስታና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲከበር ማድረግ ይኖርብናል " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia