TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሪሜዲያል
ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?
ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል።
በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ተወስኗል።
- በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።
- ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ፈተና ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ እንዲደረግ ተወስኗል።
- በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።
- የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።
ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ መልዕክት እያስተላለፉ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከየተቋማቱ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።
#TikvahFamily
More : @tikvahuniversity
@tikvahethiopia

#ኢትዮጵያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች። በውድድሩ ሀገራችን ፦ - በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ - በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ - በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች። መልካም ዕድል ! @tikvahethiopia
#ተጠናቋል
በዚህም ድል አልቀናንም !
በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ ድል አልቀናትም።
ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
ሎሜ ሙለታ 12ኛ ፣ ሲምቦ አለማየሁ 13ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ሀገራችን በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ስታካሂድ የነበረውን ውድድሮች ሁሉ #አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም 6ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 3 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ነው ያገኘችው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዋና ገፅ / @tikvahethiopia ስፖርት በተለይ አትሌቲክስ #ሀገራዊ ስሜትን ፣ አብሮነትን ፣ አንድነትን ያጠነክራል የሚል እምነት ስላለው የሀገራችን ልጆች የተካፈሉባቸውን ውድድሮች ሁሉ #ከስፍራው ከፎቶ ጋር ሲያደርስ ቆይቷል።
ስፖርታዊ መረጃዎችን በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ።

#ETHIOPIA
የ2016 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።
መልካም በዓል!

" መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " - አቶ ሞገስ መኮንን
ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እንዲሁም ከደብረ ብርሃን - ሸዋሮቢት - ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ በሰመና መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እነዚህ ሁለት መስመሮች የተበጠሱበትን ምክንያት የጠየቅናቸው ሲሆን ፤ " መስመሩ መበጠሱን ነው እንጂ ያረጋገጥነው በምን በምን ምክንያት እንደተበጠሰ ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁለቱ መስመሮች መቼ ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ? ሲል ጥይቄ አቅርቧል።
አቶ ሞገስ መኮንን ፦
- በቀላል የሚገናኙ መስመሮች ይኖራሉ ፤ በቀላል ሊገናኙ የማይችሉ እና የተበጠሰበትን ቦታ ብቻ ሳይሆን መስመር መቀየር የሚያስፈልጉም ሊኖሩ ስለሚችሉ እነዚህን እርግጠኛ ባልሆንንበት በዚህ ቀን ሊባል አይችልም ብለዋል።
- ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በኋላ ከደብረ ብርሃን- ሸዋሮቢት ኮምቦልቻ የተዘረጋው መስመር በሸዋ ሮቢት ከተማ አቅራቢያ የተበጠሰውን መስመር አገልግሎቱን ለማስቀጠል ግብዓቶችን የማሰባሰብ ስራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
- ከባህር ዳር - በደብረታቦር - ንፋስ መውጫ - ጋሸና - አላማጣ የተዘረጋውን መስመር በተመለከተ የተበጠሰው ዛሬ ረፋድ ላይ መሆኑን በመግለፅ ከባህር ዳር ያለው ርቀት ከ100 ኪሎ ሜትሮች በላይ በመሆኑ ለጥገና ጊዜ የሚፈልግ መሆኑንና አገልግሎት ለማስጀመር ይሄ ነው የሚባል ቀን ማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል።

#ዒድ_አልፈጥር
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !
በዓሉ #የሰላም፣ #የአንድነት፣ #የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️

#ኢትዮጵያ
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል።
ይህን እጅግ አሳፋሪና በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሚያሳይ ቪዲዮ ያጋሩት ደግሞ እራሳቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ናቸው።
ድርጊቱ ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል። በርካቶች ስለ ነገ በማሳብ ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል።
በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው ይበቃናል ? በፍጹም !
ከዚህ በፊትም እንደምንለው በቪዲዮዎች ተቀርጾ የምናየው ምናልባትእድለኞች ሆነን ከብዙ አንዱ እንጂ ስንት ያላየነው ይኖራል።
ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል።
ይህን ተግባራቸውን እንደ በጎ ስራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል።
የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ?
ይህ ተግባር በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነዛ ያለው የጥላቻ ስብከት ምን ያህል ስር እንደሰደደ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ነገን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል።
ግልጽ የሆነ የብሄርና የግለሰቦች ጥላቻ ፣ ልብም አእምሮም በጥላቻ መሞላት፣ አይንም በጥላቻ መታወር ፦
- ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር
- ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን
- ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ
- ለህግ እና ስርዓት ቅንጣት ታክል ደንታ እንዳይኖረን
- ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን
- ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል።
ሰዎች ወደው ሳይሆን በስርዓት፣ በግለሰቦች፣ በአንቂዎች ፣ በሚዲያዎች... አማካኝነት ነው ጥላቻ እንዲውጣቸው እና ማገናዘብ ፣ ቆም ብሎ ማሰብ የሚባለውን መሰረታዊ ነገር እንዲያጡት የሚሆነው።
ሰዎች ከመሰል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አብሮነት ፣ ፍቅር ፣ መግባባት፣ መከባበር ፣ ህግ ፣ ስርዓት፣ ወንድማማችንነትን ከማስተማር ባለፈ በህግ ማረም ፣ ነገ መዘዙ የከፋ እየሆነ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲገታ በአንድ ላይ ማውገዝ ፣ ተበዳይን መካስ ፣ እውነት ህግ የበላይ ነው የምንል ከሆነም ለራሳችን ስንል ህግን ሁሌም ማስከበር ነው።
ዛሬ ላይ እንዲህ ያሉና ከዚህ ቀደምም በየሀገሪቱ ክፍሎች የሰማናቸው ፍጹም አደገኛ የሚባሉ ጉዳዮች የሳምንት አጀንዳ እየሆኑ እያለፉ ይመስለን ይሆናል ግን በእርግጠኝነት መዘዛቸው የከፋ ሊሆን ይችላል።
ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው።
በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል።
#TikvahFamily
#Ethiopia

#Humanity❤️
ይህ የሆነው በአሜሪካ ሀገር ሚኒሶታ ነው።
በሚኒሶታ በሚገኝ #ፈጣን_መንገድ ላይ አንድ አሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወጥቶ ከመብራት ፖል ጋር ተጋጭቶ እዛው መኪና ውስጥ እያለ መኪናው በከፍተኛ እሳት መያያዝና መንደድ ይጀምራል።
በመንገዱ ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ይህን አይተው አላለፉም።
መኪናቸውን አቁመው ከሚነደው መኪና ውስጥ አሽከርካሪውን ለማውጣትና ለማዳን ርብርብ ጀመሩ።
ከእሳት ነበልባል ጋር #እየታገሉ ፤ በሹፌሩ በር በኩል ያለውን መስታወት ሰብረው ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል በኃላ አሽከርካሪውን በእሳት ተያይዞ ከሚነደው መኪና ውስጥ በህይወት አወጡት።
በኃላም ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ።
አሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል።
ከከፍተኛ እሳት ጋር ተጋፍጠው የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ሲያደርጉ ከነበሩት አንዱ ከድር ቶላ ይባላል። (ጥቁር ጁንስ ሱሪ በነጭ ጫማ ያደረገው)
ወደ ስራ እየሄደ በነበረበት ሰዓት ነው ይህ ክስተት ያጋጠመው።
ከድር የነፍስ አድን ስራውን ፥ " በህይወቴ እጅግ በጣም አስፈሪው ቅጽበት ነበር። ይህንን መቼም ቢሆን አልረሳውም ሁሌም ቢሆን አስታውሰዋለሁ " ሲል አስረድቷል።
አሽከርካሪው በህይወት እንዲተርፍ ቦታው ላይ የነበሩ ሁሉም ሰዎች ላደረጉት ፍጹም #ሰብዓዊ ተግባርና ርብርብ ፈጣሪን አመስግኗል።
የነበረውን የህይወት አድን ርብርብ የሚያሳይ ቪድዮ ከድር ቶላ መኪና ላይ በነበረ የዳሽቦርድ ካሜራ የተቀረጸ ነው።
Video Credit : Kadir Tolla / ከድር ቶላ

#ጥንቃቄ🚨
" ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው።
" ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው።
" ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም።
ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ።
ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው።

#አረፋ
መልካም በዓል !
" ይህን የተባረከ #የአረፋ_ቀን እምነታችንን በልባችንና በተግባራችን የምናድስበት ፤ ስላጠፋነው ጥፋት / ስህተት ከልብ አዝነን ዳግመኛ ወደዛ ላለመመለስ ቃል የምንገባበት እና ወደ ሁሉን ቻይ አምላካችን #አሏህ🤲 የምንቀርብበት ቀን ነው። " - ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር)
#መልካም_በዓል !!
#TikvahFamily ❤️
@tikvahethiopia
መልካም በዓል !
" ይህን የተባረከ #የአረፋ_ቀን እምነታችንን በልባችንና በተግባራችን የምናድስበት ፤ ስላጠፋነው ጥፋት / ስህተት ከልብ አዝነን ዳግመኛ ወደዛ ላለመመለስ ቃል የምንገባበት እና ወደ ሁሉን ቻይ አምላካችን #አሏህ
#መልካም_በዓል !!
#TikvahFamily ❤️
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነዋሪዎች እጅግ እያማረረ ነው።
በርካቶች የኃይል የመቆራረጡ ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ፈተና ሆኖባቸዋል።
" የሚሰሩት የመንገድ ስራዎች እየተጠናቀቂ ሲመጡ የኃይል የመቋራረጥ ነገሩ ይቃለለል ብለን ብናስብም አሁንም ያው ነው " ብለዋል ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች።
በተለያዩ ቦታዎች ላይም የኃይል መቆራረጡ ንብረት እስከማቃጠል የደረሰ ጭምር ነው።
ከኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ባለፈ ውሃም ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን ጠቁመዋል።
በተለይ ብዙ ነዋሪዎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውሃ አለመኖር የሚፈጥረው ችግር ይታወቃል።
" በየጊዜው ያለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተደጋግሞ ቢነሳም ዛሬም ድረስ ይኸው ጥያቄ ቀጥሏል ፤ ዘላቂ መፍትሄ መቼ እንደሚመጣ ግራ ነው የገባን !! " ብለዋል።
#AddisAbaba #TikvahFamily
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM