TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጤናባለሙያዎች

" ቀን ፣ ምሽት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ ነው " - ጤና ባለሙያዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲዩቲ ክፍያ አልተከፈለንም ያሉ ከ 80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

በከምባታ ዞን ፤ አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የ6 ወር የዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ) ስላልተከፈላቸው ከማክሰኞ 12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

በአመት ከ120 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ በቁጥር ከ80 በላይ ይሆናሉ የተባሉት የጤና ባለሞያዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ስራ ያቆሙ ሲሆን የሆስፒታሉ አስተዳደር በበኩሉ እስከ ትላንት ድረስ ወደ ስራቸው ካልተመለሱ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በደብዳቤ አሳውቋቸዋል።

ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ወደስራ ገበታው የተመለሰ ባለሞያ አለመኖሩን ሰምተናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው በሆስፒታሉ የሚሰሩ ባለሞያዎች " ከዚህ በፊትም በስራ ላይ ሆናችሁ ጥያቄያችሁን አቅርቡ ተብለን ተስማምተን ጀምረን ተታለናል ሳይከፈለን የመጀመር ፍላጎት የለንም " ሲሉ ገልጸዋል።

ክፍያው ያልተከፈለው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ወር የ2016 ዓም የመስከረም፣ ጥቅምት፣ ጥር እና የነሀሴ ወር የ2017 ዓ/ም የመስከረም ወር በአጠቃላይ የ6 ወር የዲዩቲ ክፍያ ነው።

" ከዚህ በፊት የ4 ወር ክፍያ ባልተከፈለን ወቅት በወረቀት በዞን እና በክልል ደረጃ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀን ነበር ነገር ግን ችግራችን አልተፈታም ከዚህ በላይ በትዕግስት መጠበቅ አልቻልንም ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች እየተዳረግን ነው " ብለዋል።

አክለው " ቀን ፣ምሽት ፣ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ በመሆኑ እና ' እየሰራችሁ ጠይቁ እንጂ ሥራ ማቆም አትችሉም ' በማለት እንዲሁም የሚያስተባብሩትን አካላት ' በህግ እንጠይቃለን ' የሚል ማስፈራሪያ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች እየደረሰን ነው " ብለዋል።

ባለሙያዎቹ " አምና ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ ስራ አቁመን የነበረ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጭምር አመልክተው ' እናንተ በስራ ላይ ተገኙ እንጂ እንዲከፈል እንነግራለን ' በማለታቸእ ወደ ስራ ተመልሰን ነበር ፤ ምንም ምላሽ ሳይሰጠን ቆይቶ በኋላ የአንድ ወር እንዲከፈለን ተደርጓል ፤ ከዚያ በኋላ ግን በተለመደው መቆራረጥ ነው የቀጠለው " ሲሉ ገልጸዋል።

ክፍያው እየተቆራረጠ ነው የሚገባው ወደ ኋላ ተመልሶ ያልተከፈለንን ክፍያ የመክፈል ምንም ፍላጎት የለም ነው ያሉት።

" የፊቱን እንከፍላለን ወደ ኋላ ተመልሶ ለመክፈል ግን ዞኑ በጀት የሌለው በመሆኑ በጀት ሲለቀቅልን ነው የምንከፍለው " የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ቀናት ሁለት ነብሰ ጡር እናቶች ምጥ ይዟቸው ወደ ሆስፒታል መጥተው የነበረ ሲሆን ባለሞያ በሆስፒታሉ ባለመኖሩ ወደሌላ ሆስፒታል በግል ትራንስፖርት በሚጓዙበት ወቅት የህፃናቱ ህይወት እንዳለፈ አክለዋል።

ሀኪሞች ሥራ በማቆማቸው ታካሚዎችም ከሆስፒታል በር እየተመለሱ መሆኑም ተነግሯል።

ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ሆስፒታሉ የወሰደው እርምጃ ያለምንም የቅጥር ማስታወቂያ 17 ሰዎችን መቅጠሩን የተናገሩት ጤና ባለሙያዎቹ " አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ከሌሎች ቦታዎች ባለሞያ አምጥተን እንቀጥራለን በሚል እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።

" ' ባለሞያ እንቀጥራለን እንደለቀቃቹ ቁጠሩት መጥታቹ ቁልፍ አስረክቡ ንብረት ላይ ቆልፋቹሃል ' በሚል ከፖሊስ ማዘዣ በማውጣት ማስፈራሪያ እየተደረገ ነው ፤ እኛ ሥራ እንለቃለን እላልንም እንሰራለን ግን ክፈሉን ነው ያልነው ተርበናል፣ ገንዘብ አጥተናል፣ ልጆቻችንን ማስተማር አልቻልንም የወተት እና የቤት ኪራይ መክፈል ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ የባለሞያዎቹን ቅሬታ ይዞ የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራን ትላንት ቢያነጋግርም ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ለጊዜው ምላሽ አልሰጡም።

ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " በድጋሚ ቢሮ ሂደን ጠየቅናቸው ግን የተስፋ ቃል ከመስጠት ውጪ መሬት ላይ ምንም ተጨባጭ ነገር አይሰሩም  " - ቤት ገዢዎች ከ600 በላይ የሚሆኑ የአያት ግሪን ኖህ ሪልስቴት ቤት ገዢዎች፣ በውላቸው መሠረት ድርጅቱ የመብራት፣ የውሃ፣ የታንከር መሠረተ ልማቶችን ባለሟማላቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው ከገዙት ቤታቸው መግባት እንዳልቻሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡…
#AddisAbaba

“ ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” - ኖህ ሪልስቴት

ኖህ ሪልስቴት ሰሚነት አካባቢ “ ኤርፓርት ድራይቭ ” በተሰኘ ሳይቱ የገነባቸውን ሱቆችና ቤቶች ዛሬ ለገዢዎቹ ማስረከቡን ገልጿል።

የድርጅቱ የሕግ ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ደስታ፣ “ ዛሬ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው 'ኤርፓርት ድራይቭ' የተሰኘ ሳይት ቤቶችን ስላጠናቀቅን የምረቃት ሥነ ስርዓት አካሂደናል ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ሱቅን ጨምሮ ወደ 750 ቤቶች እንዳስረከቡ ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር፣ “ በዛሬው እለት እያስመረቅናቸው ያሉ 750 ቤቶቾና 43 ሱቆች ከተማችንን የሚመጥኑ ሆነው ለምተዋል ” ብለዋል።

እስከዛሬ ባስረክባችኋቸው ቤቶች የመሠረተ ልማት ቅሬታ ይነሳል (ለምሳሌ አያት ግሪን ሰይት ተጠቃሽ ነው) በአሁኑ ሳይትስ ተመሳሳይ ቅሬታ እንዳይኖር መሠረተ ልማቱ ተሟልቷል ? ሲል ቲክቫህ ለአቶ ዮሴፍ ጥያቄ አቅርቧል።

ምን አሉ ?

ከአያት ግሪን ፓርክ ልምድ ወስደናል። ሁሉም ፕሮጀክቶቻችን ላይ መዘግዬት የተፈጠረው ከኮቪድ ጀምሮ ባለው ችግር ነው። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ያለውን ነገር እንዴት እንፍታ ? በሚል ግሪን ፓርኩ ላይ ልምድ ወስደናል።
 
ከወሰድነው ልምድ አንጻር ለዚህኛው ፕሬጀክት አስፈላጊው ጀነሬተር ገብቷል ፤  ትራንስፎርመር ገብቷል። የመብራት ፓሎችም ተተክለዋል። ከህንጻዎቹ ጋር የማገናኘት ሥራ ብቻ ነው የሚቀረን።

ውሃን በተመለከተ ፤ ቦታው ላይ የከርሰ ምድር ውሃ ቆፍረን ለነዋሪው አዘጋጅተናል። ስለዚህ የውሃ ችግር አይኖርም። 

መብራትን በተመለከተም ከመንግስት የፓወር ችግር የለም። በኛ በኩል የሚያስፈልገውን ትራንስፎርመር፣ ጀነሬተር፣ ሌሎቹን ኢንፍራስትራክቸሮች በሙሉ አዘጋጅተናል። ስለዚህ እሱን የማገናኘት ሥራ እንሰራለን ”
ብለዋል።

በአጠቃላይ በገዢዎች የሚነሱ የመሠረተ ልማት ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ኖህ ምን እየሰራ ነው ? ዛሬ ያስረከባችኋቸው ቤቶች መሠረተ ልማቶች መቼ ይጠናቀቃሉ ? የሚጠናቀቁበትን ጊዜስ ከገዥዎቹ ጋር ተነጋግራችኋል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ማብራሪያቸው ምንድን ነው?

ትልቅ እንቅፋት የነበረው የትራንስፎርመር ችግር ነው። ከመንግስት (ከኤሌፓ) ነው የሚገዛ የነበረው። ከዚያ ብቻ በሚገዛበት ጊዜ ወረፋ እንጠብቅ ነበር። አሁን ግን ተፈቅዶልናል ከገበያ እንድንገዛ። ያ እንቅፋት የለም።

ውሃን በተመለከተ ፤ የከተማውን የውሃ እጥረት ስለምናውቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው በከርሰ ምድር ላይ ነው። ውሃም ቶሎ የሚገኝበትን መንገድ እንሰራለን።

ህንጻዎቹ ያልቃሉ ከዛ የመሠረተ ልማት ጥያቄ አለ። ይሄ ጥያቄ የኛ ብቻ አይደለም። ዋናው ሆኖ እያለ በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይም የውሃ እጥረት አለ። ለመቅረፍ እየሰራን ነው


መሠረተ ልማቱ በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ያልቃል ? ሁሉም እቃ ቀርቧል። የቀረው ነገር መብራት በሚሰራው ኮንትራክተር መገጣጠም ነው። ከቆጣሪ ጋ የመገጣጠም ሥራው ግፋ ቢል ከዚህ በኋላ አንድ ወር ቢፈጅ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

የአያት ግሪን ፓርክ የገዢዎች የመሠረተ ልማት ከምን እንደደረሰ ጠይቀናቸው በሰጡን ቃል አቶ ዮሴፍ ፤ “ ተመሳሳይ እምጃዎችን ወስደን የመብራት አገልግሎቱ አሁን በዬቤቱ ቆጣሪ የማስገባት ሥራ ተጀምሯል” ነው ያሉት።

“ ስለዚህ እዛም ያለውን ችግር አቃለናል። ውሃን በተመለከተ ለውሃ የሚያስፉፍገው የታንከር ማስቀመጫ ቦታ ችግር ነበረብን እሱን ፈትተን ውሃውን ግቢ ውስጥ አስቀምጠን ወደ ፊት እየተራመድን ነው ያለነው ” ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" የአንድ አመት ከሁለት ወራት በላይ እልቂት ቀላል እልቂት አይደለም  !! "

በአማራ ክልል ከአንድ አመት በላይ የሆነውን ጦርነት ዛሬም መቋጫ አላገኘም።

በየጊዜው በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በሚካሄዱ ውጊያዎች የበርካታ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው።

ንጸሃን የጦርነቱ ሰለባ መሆናቸው ቀጥሏል።

የሰብዓዊ መብት ተቋማት በሚያወጧቸው ሪፖርቶች በድሮን ጭምር በሚፈጸም ጥቃት ንጹሃን ሰለባ እየሆኑ ነው።

ሴቶችና ህጻናት ፣ በእድሜም የገፉ ዜጎች ከፍተኛ ጉዳትና ዋጋ እየከፈሉ ናቸው።

በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ በተለያዩ ከተሞች ' የፋኖ ' ደጋፊ ናችሁ በሚል ለእስር ለእንግልት የተዳረጉ ዜጎች በርካቶች ናቸው።

ጤና ተቋማት ስራ መስራት አልቻሉም።

የጤና ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው። የመድሃኒት ችግር በስፋት አለ። በተለይ ግጭት ሲኖር ከከተማ በወጡ አካባቢዎች ፤ ከተማ ውስጥ ሳይቀር መድሃኒት እና የጤና አገልግሎት ማግኘት ፈተና ሆኗል።

ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን ለመከታተል አልቻሉም። ላለፉት ተከታታይ አመታት የአማራ ተማሪዎች እጅግ በስቃይ ውስጥ እያለፉ ናቸው።

ዘንድሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን  ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪ ይመዘገባል ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካለፈው መስከረም 8 የተመዘገበው 2 ሚሊዮን 295 ሺህ 150 ተማሪ ብቻ ነው።

በክልሉ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የግቢ ጥሪ ተራዝሞባቸው ያለ ትምህርት ቤታቸው ቀጭ ብለው ይገኛሉ።

በሰሜኑ ጦርነት ክፉኛ የተዳከመው የክልሉ ኢኮኖሚ አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል።

ገንዘብ ያላቸው ስራ መስራት አልቻልም በሚል ወደ አዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ብዙ ተነግሯል።

ከቱሪስቶች ብዙ ገቢ ያስገባ የነበረው የአማራ ክልል አሁን ላይ ለጉብኝት ብሎ ወደ ክልሉ የሚጓዝ ተጓዥ አጥቷል።

የክልሉ አሁናዊ ፀጥታ ሁኔታ ሰዎች በማገት ገንዘብ ለሚቀበሉ አካላት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ በርካቶች ታግተው ከፍለው ወጥተዋል። አንዳንዶች ከፍለው ሁሉ ተገድለዋል። ህጻናት ሳይቀሩ እየታገቱ ገንዘብ ይጠየቃል።

በክልሉ በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች ተጠያቂነት እና ስርዓት የሚባለው ነገር ከጠፋ ሰነባብቷል።

በአጠቃላይ ክልሉ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው።

ለመሆኑን በአማራ ክልል ያለውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈታ ያመቻቻል ተብሎ የተሰየመው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል እስካሁን ምን አደረገ ? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው።

ሰሞኑን የሰላም ካውንስሉን አግኘትን ምን እየሰራችሁ ነው ? ህዝቡ ከዚህ መከራ የሚወጣበት ተስፋስ አለው ወይ ? ችግሩ በሰላም ይፈታ ይሆን ? ስንል ጠይቀናል።

ካውንስሉ ምን አለ ?


➡️ችግሮቹ በአንድ ጀንበር የሚያልቁ ስላልሆኑ ጊዜ እየወሰደ ነው የመጣው። የፋኖ ታጣቂዎችም አንድ አመራር ፈጥረው የክልሉን ህዝብ ጥያቄ ማስመለስ የሚችሉት በድርድር ነው። ' ለአማራ ህዝብ ጥያቄ ነው የቆምነው ' ካሉ ጥያቄው ሊመለስ የሚችለው በጦርነት አይደለም።  በድርድሩ በፋኖም በኩል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ ሁሉ ፍላጎት የሌላቸው ወገኖችም አሉ። ከመንግስት ጋር ለመደራደር ፍላጎት የሌላቸው ወገኖች ‘ በጦርነት እንገፋለን ’ የሚሉ ናቸው። ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ደግሞ ‘ አንድ ሆነን ለመምጣት ሁኔታዎችን እያመቻቸን ነው ’ የሚሉ፣ የመንግስትን ቁርጠኝነትም የሚጠይቁ ናቸው።


➡️ ለድርድሩ መንግስት ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? የሚሉ ወገኖች አሉ። መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለን ለማለት ፈቃደኝነቱ በክልል ደረጃ የታዬ ቢሆንም፣ በፌደራል ደረጃም እንድምታ በመግለጽ ረገድ የሚገለጽ ነው። ነገር ግን በመግለጫ ደረጃ በፌደራል መንግስት አለመሰጠቱን ግምት ውስጥ አስገብተን ችግሮቹ በሂደት ይፈታሉ። ሁለቱንም ወገኖች ለውይይቱ ዝግጁ ሆናችሁ በፈለጋችሁት ቦታ፣ በመረጣችሁት አደራዳሪ፣ በራሳችሁ ማኒፌስቶ ጥያቄያችሁን አቅርባችሁ ችግሩ ይፈታ ብለን አሳስበናል።

➡️ ችግሩ በድርድር እንዲፈታ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ ከኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ጋር (ከአሜሪካ፣ ከኢጋድ ከካናዳ መንግስት) ግንኙነት አድርገናል። ‘ሁለቱም ኃይሎች ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የበኩላችን እገዛ እናደርጋለን’ ብለዋል።


ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አማራ ክልል ያለው የተኩስ ልውውጥ ጠንከር ብሎ ታይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ድርድር በመምጣት ፋንታ ወደ ጠንካራ ጦርነት ያስገባቸው ያልተስማሙበት ጉዳይ ምንድን ነው ? በሚል ለካውንስሉ ጥያቄ ቀርቧል።

ካውንስሉ ምን ምላሽ ሰጠ ?

" ድርድር በየትኛውም መንገድ ሊከናወን ይችላል። እየተዋጉ መደራደር፣ ተኩስ እያቆሙ መደራደር፣ የበላይነትን ይዞ መደራደር የድርድሩ አንድ ፕሪንሲፕል ነው።

ምናልባት እየተዋጉም ቢደራደሩ ፣ ተኩስ አቁመውም ቢደራደሩ ይሄ ድርድርን በውስጥ ያዘለ ድርድር ማድረግ የሚያስችላቸው ሁኔታ ሊኖረው ይችላል።

አሁን ላይም እየተዋጉም ቢሆን ' እንደራደር ' ሊሉ ይችላሉ። ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም። ሁሌም ይዋጋሉ። 14 ወራት ሆናቸው። ይሄ ውጊያ ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ከዚህ በፊት የነበረ ነው። 

እኛ አሁን ይሄ እንዳይቀጥል ነው እየነገርን ያለነው። ሁለቱም ወገኖች በየጊዜው ውጊያ  ያውጃሉ በሚዲያቸው እንሰማለን። ፋኖዎቹም ያውጃሉ፤ በመንግስትም አዲስ ነገር አይደለም። "


ድርድር ለማድረግ 2ቱም አካላት በሙሉ ሥምምነት ያልቀረቡባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ካውንስሉ ተከታዩን መልሷል።

“ በህዝብ ዘንድ ያለውን የከፋ ስቃይ እንዲያዩ ነው የምንመክረው። ሁለቱም ወገኖች ደግሞ ማዬት ያልቻሉት ነገር ህዝብ አሁን ያለበትን ስቃይ ነው። 

እኛ ደግሞ ህዝቡ በየቀኑ እየሞተ ፣ እየደቀቀ ፣ ህልውናውን ጭምር ፈተና ውስጥ የከተተበት ጊዜ መሆኑን እናያለን። 

ህዝቡን አብረነው ስለምንኖር በስሚ ስሚ አይደለም የምንሰማው በዓይናችን የምናየው መጥፎ ተግባር ከአጠገባችን ነው ያለው።

ስለዚህ ህዝቡ ችግር ላይ መውደቁን ሁለቱም ማዬት አለባቸው።
" ብሏል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መንግስት እና በታጠቁ ኃይሎች ለአብነት ከ " ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ሸኔ " ጋር ድርድር ተሞክሮ ያለ ውጤት ተቋጭቷል ፤ በአማራ ክልል ድርድር ቢደረግ ተመሳሳይ የሆነ እጣ ፈንታ እንዳያጋጥመው ምን ይሰራል በሚል ለቀረበው ጥያቄም ካውንስሉ ምላሹን ሰጥቷል።

ካውንስሉ ፦

“ አንዳንዶቹ ችግሮቹን በውይይት ለመፍታት ቶሎ ብለው ወደ ድርድር ይመጣሉ። መንግስት የኃይል የበላይነትን ባገኘ ጊዜ የዓለም ኃያላን የመጡበትና ትብብር የተደረገበት፣ ፈጥነው የመጡበት ሁኔታ ነበር።

ምክንያቱም መንግስት የኃይል የበላይነት ስላገኘ ነው። 

‘ ህዝብ የሚፈልገው ጦርነት ነው ’ ብሎ ካመነ ‘ ድርድርም አልፈልግም ’ ይልና ሲዋጋ ይቆያል። ይሄ የስልጣኔ አካሄድ አይደለም።

ካለፈው ድርድር መማር፣ ከዚህ በላይ ህዝቡ ሳያልቅ ወደ ውይይት መምጣት ያስፈልጋል። የአንድ ዓመት ከሁለት ወራት በላይ እልቂት ቀላል እልቂት አይደለም። የደረሰብን ፈተናም ቀላል አይደለም።

አለመታደል ነው እኮ። መማር አለብን። ሕዝብ እየተመታ፣ ህዝብ እየወደመ፣ ህዝብ ልጁን እያጣ፣ ትምህርት ቤት እየተዘጋ…‘ህዝብ ይደግፈኛል’ ማለት ካለመረዳት የሚመነጭ እንጂ መፍትሄው በእጃቸው ነው። ሁለቱም ኃይሎች ለድርድር ይቅረቡ
"

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈#የመምህራንድምጽ

" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - ቃላቸውን የሰጡ መምህራን

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

የማህበሩ ስብሰባ ላይ ፦

መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣

ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣

ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣

የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል።

ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።

ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።

" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 545 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላልፈ ጨረታ አውጥቶ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ቤቶቹን " በተለያዩ ሳይቶች ያስገነባኋቸው ናቸው " ብሏል።

የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 1000 ብር ነው በ6 የመሻጫ ጣቢያዎች እየሸጠ ያለው።

የመኖሪያ ቤቶቹ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ግራር (235 ቤቶች) እና አየር ጤና (110 ቤቶች) እንዲሁም በጉለሌ ክ/ከተማ እንጦጦ (200 ቤቶች) እንደሚገኙ ተሰምቷል።

የአንድ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 80,000 (ሰማንያ ሺህ ብር) እንደሆነም ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ተችሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጤናባለሙያዎች " ቀን ፣ ምሽት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ ነው " - ጤና ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲዩቲ ክፍያ አልተከፈለንም ያሉ ከ 80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል። በከምባታ ዞን ፤ አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የ6…
#Update

" የጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም " - የሆስፒታሉ ሰራተኞች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሲሆን ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸውልናል።

ስራ አቁመው በቆዩባቸው ቀናት ከወሊድ ጋር በተገናኘ ወደ ሆስፒታሉ መጥተው የነበሩ እናቶች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው ባለሞያዎች እና ከሆስፒታሉ አመራር ተረድቷል።

ጉዳያቹ ከምን ደረሰ ? ስንል በድጋሚ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የጤና ባለሞያዎች " የስራ ማቆም አድማውን አስተባብራቹሃል " በሚል 14 በሚሆኑ ባለሞያዎች ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶ እየተፈለጉ መሆኑን እና ይህንንም ፍራቻ ከአካባቢው ርቀው መደበቃቸውን ተናግረዋል።

" እኛ ስራ ካቆምን በኋላ የምንጠብቀው የሚመለከታቸው አመራሮች ችግራቹ ምንድነው ? እንዴት ዘጋቹ ? ምንድነው ችግሩ ? ብለው መጠየቅ እና መሰብሰብ ሲገባቸው ጭራሽ ወደ ማሳደድ ገብተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሸሽተን ነው ያለነው በፖሊስ ማዘዣ ወጥቶ በተገኙበት ይያዙ ተብሏል እየተፈለግን ነው። ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽተናል " ሲሉ አክለዋል።

" ተቋሙ በቂ መድኃኒት እና የህክምና ግብአቶች የሉትም ለበርካታ ጊዜያት የመድኃኒት ግዢ አልተፈጸመም ሆስፒታሉን የምናገለግለው ባለው ነገር ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን ስብሰባ ላይ ያለውን ችግር የሚናገሩ ሰዎች '" አድመኛ እና ሌላ አላማ ያላቸው ተብለው እየተፈረጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ " ይህንን ችግር ችለን እየሰራንም የሰራንበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ደሞዛችን ለምንም የሚበቃ አይደለም ነው " ያሉት።

" ስራ በማቆማችን የኛን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ በማህበረሰቡ ዘንድ እንድንጠላ ሥራ እየሰሩ ነው " ያሉ ሲሆን " እየተሰቃየ ቀን እና ማታ የሚሰራ ሰው የ2016 ዕዳውን ሳይከፍል ፣ የቤት ኪራይ ክፈል ወይም ልቀቅ እየተባለ በስቃይ ነው ያለው ባለሞያው ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መጥቶ ነው ስራውን የሚሰራው እረፍት ወጥቶ ሄዶ እናቱን እና አባቱን እንዳይጠይቅ የህክምና ስራ እረፍት የለውም " ብለዋል።

" ችግርህ ምንድነው ተብሎ አይጠየቅም ? ሲሪንጅ (Syringes) የለም ብለን ማውራት የለብንም እንዴ ? ማቴሪያል ለዚህ ተቋም ያስፈልጋል ህዝቡ መንገላታት የለበትም ብለን መጠየቅ የለብንም ? ይህንን ባወራን በፖሊስ መጥሪያ መውጣት የለበትም አግባብ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም ይሄንን ሌላ ቦታ አላወራንም ስብሰባ ላይ ነው ያወራነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለሙያዎቹ ፥ " እኛ ስራውን ከማቆማችን በፊት ሁሉም ባለሞያ ቀደም ብሎ ተኝቶ ታካሚዎችን ወደ ሌላ ቦታ ሪፈር አድርገን ነው የወጣነው " ያሉ ሲሆን እነሱ ግን ታካሚዎችን ትተን እንደወጣን በማስመሰል በማህበረሰቡ ዘንድ የማጥላላት ሥራዎችን እየሰሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፥ " ለመንግስት የስራ ሰዓት ብለን ለምንሰራው ሥራ የሚከፈለን ደሞዝ ለእኛ በቂ አይደለም ኢኮኖሚውን መቋቋም አልቻልንም። " ብለዋል።

" የቆየ ችግር ነው ከ2015 ጀምሮ እየተቆራረጠ ነው የሚመጣው እያቃተን ነው ። የሚገባልን ደሞዝ እዳችንን ራሱ መክፈል አልቻለም። አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ' ለሌላ ሆስፒታል ሰራተኞች ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ ይወሰድባቸው ' ተብሎ እየተፈለግን ነው ሲሉ ነግረውናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን አመራር አግኝቶ ስለ ችግሩ ጠይቋል። የአመራሩ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የጤና ባለሞያ ወንጀለኛ አይደለም " - የሆስፒታሉ ሰራተኞች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ከ80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ለ6 ወራት የሰሩበት የተጠራቀመ የዲዩቲ ክፍያ ስላልተከፈላቸው ከ12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የጤና ባለሞያዎቹ እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው…
#Update

" ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው " -የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ

ከክፍያ ጋር በተያያዘ የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ዘግተው ስለወጡና ስራ ስላቆሙ ጤና ባለሞያዎች በተመለከተ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኔ እንደ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ ይከፈላቸው ብዬ እየጠየኩ ነው በዕለቱም ይህንን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ለመነጋገር ስሄድ ነው ዘግተው የወጡት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስመጣ ሁሉም ክፍል ዝግ ሆኖ ነው የጠበቀኝ ታካሚው ውጪ ሲጉላላ ነው የደረስኩት " ብለዋል።

ወረዳውም የተጠየቀውን ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነው ያሉት አቶ ተሰማ " ነገር ግን ' የገንዘብ እጥረት አለብኝ 'ታገሱ ' ብሏል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ጤና ጣቢያ ለአንድ ደቂቃም መዘጋት የለበትም " የሚሉት ሃላፊው " እነሱ ግን ዘግተው ወጡ እንደዚህ ሲሆን ማስታወቂያ አወጣን ' ወደ ስራቹ ተመለሱ ' የሚል አልመጡም በመሃል ወሊድ ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ የመጡት እናቶች ሪፈር በሚደረጉ ወቅት ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል " ብለዋል።

" ላብራቶሪ ፣ ማዋለጃ ፣ መድሃኒት ክፍል ሁሉንም ዘግተው ነው የሄዱት ቁልፍ አስረክበው ቢሄዱ አንድ ነገር ነው ትልቅ ወንጀል ነው ሰርተው የሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጁ አምናም በተመሳሳይ ከዲዩቲ ክፍያ ጋር በተያያዘ ሆስፒታሉ ተዘግቶ እንደነበር ገልጸዋል።

" ያኔ ምንም እርምጃ አልተወሰደም በዚሁ ከቀጠለ ጤና ተቋማት እየተዘጉ ህዝብ ያልቃል እርምጃ ካልተወሰደ ነገም ቢሆን እየዘጉ ይወጣሉ በዚህ መሃል ሰው ይሞታል የሞተ ሰውን ደግሞ መመለስ አይቻልም " ብለዋል።

በተቋሙ ዘግተው የወጡትን ሰዎች በህግ እንዲፈለጉ እያደረግን ነው የዘጓቸውን ክፍሎች ግን በህጋዊ መንገድ ሰብረን ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለጊዜው ከሌሎች አካባቢዎች ባለሞያዎችን አምጥተው ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከ80 በላይ ባለሞያዎች በአንድ ጊዜ ነው ስራ ያቆሙት ምን ያህል ባለሞያዎችን አግኝታቹሃል ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ " ባሉት ዋና ዋና ጊዜ የማይሰጡ የወሊድ እና የድንገተኛ ህክምና ቦታዎች ላይ 7 ባለሞያዎች አምጥተናል ኦፕሬሽን ላይ ግን ሰው ማግኘት አልተቻለም " ብለዋል።

እነዚህ ባለሞያዎች ክፈተቱን ለመሸፈን የመጡ እንጂ ቋሚ ተቀጣሪዎች አይደሉም ሲሉ አስረድተዋል።

ስራ ያቆሙት ባለሞያዎች ተመልሰው ቢሙጡ ትቀበላላቹ ወይ ? ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄ  " እስካሁን የመጣ ባለሞያ የለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ' በሌሎች ተገፋፍተን አስፈራርተውን ነው ' የወጣነው የሚሉ ባለሞያዎች አሉ የሚመለሱ ከሆነ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ነገር ግን አስቀድመን ከማህበረሰቡ ጋር ውይይቶችን አድርገን ነው የሚሆነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሃላፊው ፥ " ስራ በማቆማቸው ቀዳሚ ተጎጂ ማህበረሰቡ መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ በኋላ ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግረን ይመለሱ አይመለሱ የሚለውን የምንወስን ይሆናል " ሲሉ አክለዋል።

ወደ አመራርነት ከመጡ 2 ወራቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተሰማ " በሆስፒታሉ ውስጥ የአከፋፈል ስርዓት ችግር አለ ከታካሚው አንጻር ትርፍ ባለሞያ ነው ያለው አንዳንድ የማሻሻያ ስራዎች እየሰራን ነው ተቋሙ ላይ መድኃኒት መኖር አለበት መድሃኒት በህገወጥ መንገድ የሚወጣበት ተቋም ነው። ይህ እንዳይሆን አንዳንድ ስራዎችን መስራት ጀምረናል ይህ ያስቆጣቸው ሰዎች አሉ " ብለዋል።

ቲክቫክ ኢትዮጵያ ሰራተኞቹ የጠየቁት የተጠራቀመ እና የሰሩበትን ክፍያ ነው በምን ያህል ጊዜ ችግራቸውን ትፈታላቹ ? የሚል ጥይቄ አንስቷል።

ስራ አስኪያጁ ፤ " እኔ ያሰራኋቸውን የሁለት ወር የዲዩቲ ክፍያ ለመክፈል 1.4 ሚልዮን ብር ያስፈልጋል ይህንንም ለመክፈል ቀኑን መወሰን አይቻልም ወረዳው ' ያለውን ነገር ተነጋግረን እንፈታለን ' ብለዋል ይከፈላቸዋል " ሲሉ መልሰዋል።

" ያልተከፈላቸውን ክፍያ ሁሉ ለመክፈል ወረዳው ዝግጁ ነው " ያሉ ሲሆን ነገር ግን የበጀት እጥረት በመኖሩ ቀኑን መወሰን እንደማይቻል ገልጸዋል።

በ2016 የጥር ወር ላይ የ4 ወር የዲዩቲ ክፍያ ባለመከፈሉ በተመሳሳይ ሰራተኞች ስራ አቁመው እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ነው።

በወቅቱ ሆስፒታሉ ከወረዳው ከሚገኙ የጤና ጣቢያዎች 17 ያህል ባለሞያዎችን ቀጥሮ ስራ አስጀምሮ ነበር።

ከዚያ በኋላም የአንድ ወር እንዲከፈላቸው ተደርጎ ወደ ስራ ተመልሰው የነበረ ሲሆን በጊዜያዊነት ተቀጥረው የነበሩት 17 ባለሞያዎች አብረው እንዲቀጥሉ ተደርገዋል።

አቶ ተሰማ እኚህ 17 ባለሞያዎች አሁን የስራ ማቆም አድማ ካደረጉት ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ባለሞያዎች ወደመጡበት እንዲመለሱ በወረዳው አስተዳደር መወሰኑን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሆስፒታሉን ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ እና የአንጋጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ማርቆስ ማሞን በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#መምህራን በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል። እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል። ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን…
#Update

🔵 “ መምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን ” - የወላይታ ዞን መምህራን

🔴 “ ከ10,500 በላይ መምህራን ደመወዝ አልተፈጸመላቸውም ” - የዞኑ መምህራን ማኀበር

በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን ያልተከፈላቸውን ደመወዝ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ “ በፓሊስ መታሰራቸው ” ተሰምቶ ነበር።

የደመወዝ ቅሬታቸው ባለመፈታቱ የመብት ጥያቄ ለማንሳት ባደረጉት ፒቲሽን የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ነበር ፓሊስ “ አመጽ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል። የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል ” በሚል ያሰራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የታሰሩት መምህራን ተፈቱ ? የደመወዝ ቅሬታችሁስ መፍትሄ አገኘ ? ሲል ዛሬ ቅሬታ ያላቸው መምህራንን ጠይቋል።

ምን መለሱ ?

ምህራኑን ስምንት ቀናት አስረው ነው የፈቷቸው። ሦስቱም መምህራን ተፈትተዋል። በሕግ አምላክ አሁንም ደመወዛችን ይከፈለን። 

‘ መንግስትን ከሕዝብ አጣልታችኋል ’ የሚለው ክስ በፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም መረጃ የላቸውም። ከዚያ ጋር ተያይዞ ነው ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው።

የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።

አሁንም ደመወዝ እንዲከፈለን እንፈልጋለን።

መምህራን ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ሥራ ስለሚሰሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በትክክል እንዲተገብሩ ደመወዝ መከፈል አለበት።

የሐምሌ ደመወዝ እስካሁን አልተከፈለም። ለመምህራንና ለጤና ባለሙያ 40 በመቶ፣ ለፓሊስ 20 በመቶ እንጂ ከዚህ ውጪ ደመወዝ አልተከፈለም።

አሁን እንደገና አጠቃላይ የትምህርት ባለሙያም ወደታች ወርዶ ‘የሐምሌን ደመወዝ እንከፍላለን’ በማለት አመራርም በአጠቃላይ ተረባርቦ መምህራን ወደ ስራ አስገብተዋል።

ፍርድ ቤትም ገና የራሱን ቀጠሮ እየሰጠ ነው የሐምሌ ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት
” ብለዋል።

ደመወዛቸው በወቅቱ አለመፈጸሙ ትልቅ ጥፋት ሆኖ እያለ ይህንኑ ቅሬታ መምህራን ታስረው መቆዬታቸው ግፍ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም በዚሁ ቅሬታ ላይ ምን እየሰሩ እንደሆነ የክልሉና የዞኑን መምህራን ማኀበር ጠይቋል።

የክልሉ መምህራን ማኀበር የመምህራንን መታሰር በተመለከተ እስካሁን ሪፓርት እንዳልተደረገለት/ቅሬታ ያደረሰው አካል እንደሌለ ገልጾ፣ በይበልጥ የዞኑ መምህራን ማኀበር እንዲጠየቅ አሳስቧል።

ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የወላይታ ዞን መምህራን ማኀበር ሊቀ መንበር መምህርት ባዩሽ ዘውዴ፣ “ በቅርቡ ታስረዋል ስለተባሉት መምህራን ለኛ ኦፊሻሊ የቀረበልን ምንም መረጃ የለም ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ያመለከተልን አካል የለም። ከውጪ ወሬ ነው እየሰማን ያለነው። ወደ አክሽን እንዳንገባ የመጣልን መረጃ የለም ” ያሉት ሊቀመንበሯ፣ “ እንነጋገርበት ወደኛ መምጣት ይችላሉ ” ብለዋል።

የደመወዝ ክፍያን ቅሬታ በተመለከተም በሰጡን ምላሽም፣ ከ10 ሺህ 500 በላይ መምህራን ደመመወዝ እንዳልተፈጸመላቸው ገልጸው፣ ማኀበሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

የክፍያ አለመፈጸምን በተለመከተ ምላሽ እንዲሰጡ ከዚህ ቀደም የጠየቅናቸው የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎደና፣ “ አራት ወረዳዎች ላይ መሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው። የሐምሌ ወር ክፍያ ላልተፈጸመላቸውም ወረዳዎች ገቢ ሰብስበው እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው ” ብለው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" የከንቲባዋ ቃል አሳዝኖናል " - የ97 ተመዝጋቢዎች

" የ1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች 20 አመት ሙሉ የጠበቅነዉን ተስፋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ' 97 ሰጥተን ጨርሰናል ' ማለታቸዉ በጣም አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቁጠባችንን በአግባቡ እየቆጠብን የነበርን በሺዎች የምንቆጠር ዜጎች አለን " ብለዋል።

" እኛም ዜጎች ነን በኪራይ ቤት እድሜችን አለቀ " ሲሉ አክለዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " ለሕዝብ ዕንባ ጠበቂ ተቋም ደብዳቤ አስገብተናል አዲስ አበባ ቤቶች ኤጀንሲ ግን መልስ አልሰጣቸውም " ሲሉ አስታውሰዋል።

" ከዚህ ባለፈ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮም መፍትሄ እንዲፈልግልን ብለን ነበር ጋር ግን ምላሽ ተነፍጎናል " ብለዋል።

" ወዴት እንደምንሄድ ጨንቆናል ፍትህ ተጓሎብናል ፤ አሁን ካለው የኑሮ ጫና አንጻር የቤት ኪራይ ትልቁ ፈተና ነው እባካችሁ መፍትሄ ፈልጉልን " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ዶክተርነቢያትተስፋዬ 👏 #ኢትዮጵያ

ከስፓይና ቢፊዳ የጤና እከል ጋር የተወለዱት ግለሰብ በማሌንዢያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረንስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኑ።

ከ30 ዓመታት በፊት ከህመሙ ጋር የተወለዱት ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ፣ በማሊዥያ የስፓይና ቢፊዳ ዓለም አቀፍ ኮንግረስ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሕይወት ዘመን ተሸላሚ የሆኑት፣ ያሳለፉትን የሕይወት ውጣ ውረድ ሌሎች ልጆች እንዳያልፉ በሕይወት ልምዳቸውና በሙያቸው ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል በሚያደርጉት ጥረት ነው።

ለኢትዮጵያውያን የሚሰጡትን አግልግሎት አድማስ ለማስፋት “ አለያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት ” የተሰኘ በስማቸው ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት በመመስረት አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል።

ድርጅታቸው ከሀገር ውስጥና ውጭ ካሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በስፓይና ቢፊዳ እና ተያያዥ የጤና ችግር ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሟላ ድጋፍ ለማድረግ ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ቃል ገብተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት በዓመት ከስፓይና ቢፊዳና ተያያዥ የጤና እክሎች ጋር አብረው የሚወለዱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በርካታ ሕፃናት ከዚህ ችግር ጋር አብረው ከሚወለድባቸው ሀገሮች ግንባር ቀደም መሆኗን አስረድተዋል።

በመሆኑም ከጤና ሚንስቴር ፣ ከሆስፒታሎችና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በዚህ ችግር የተጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የክትትልና የማገገም አገልግሎት እንዲያገኙ በትጋት እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

የተሸላሚው የሕይወት ጉዞ ምን ይመስላል ?

ከ30 ዓመታት በፊት ከዚህ የጤና ችግር ጋር ተወልደዋል። ከዚህ ችግር ጋር አብረው በመወለዳቸው በሕይወታቸው ውስጥ ብዙ ውጣውረዶች አሳልፈዋል።

የተለያዩ ቀዶ ጥገና ሕክምናዎችንም አድርገዋል።

በልጅነት ጊዜያቸው በዚሁ በሽታ ሳቢያ ትምህርታቸውን ቤት ተቀምጠው እስከመከታተል ተገደዋል። በተለያዩ የጤና ችግሮች ውስጥም አልፈዋል።

እነዚህን ሁሉ ችግሮች በትጋትና በጥንካሬ ከቤተሰቦቼ ጋር በመሆን አልፈው የህክምና ትምህርት መማር ችለዋል።

ለአምስት አመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው ከጨረኩበት ማግስት ጀምረው እንደሳቸው ሁሉ ከዚህ የጤና ችግር ጋር ለሚወለዱ ሕፃናት የተለያዩ ድጋፎችና የህክምና አገልግሎቶች እንዲያገኙ በማድረግ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች ተስፋ ለመሆን በቅተዋል።

ልጆች ከዚህ ከባድ የጤና ችግር ጋር አብረው እንዳይወለዱና መከላከል እንዲቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ፎሊክ አሲድ በምግብ እንዲበለፅግ የማስተማርና የማስተዋውቅ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ።

ለሁለት አመታት Reachanother foundation በሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ የአገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 8 ሆስፒታሎች ሕፃናት ጥራት ያለው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት  እንዲያገኙ ባለሙያዎች ማስልጠን እና ግብቶችን የሟሟላት ሥራ በመስራት ላይም ይገኛሉ።

ስለ ስፓይና ቢፊዳ ይወቁ ፦
https://t.me/tikvahethiopia/74429?single

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM