TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኩሽ #ሴራሊዮን

የሴራሊዮን መንግሥት በአገሪቷ በተንሰራፋው ‘ #ኩሽ / Kush ’ እየተባለ በሚጠራው የአደንዛዥ እፅ ምክንያት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።

' ኩሽ ' የተለያዩ ሱስ የሚያስይዙ ግብዓቶችን በመደባለቅ የሚሰራ አደገኛ እፅ ሲሆን ለዓመታት በአገሪቷ ተንሰራፍቶ ይገኛል።

በአደንዛዥ እጹ ውስጥ ከሚጨመሩ ግብዓቶች መካከል አንዱ የተፈጨ #የሰው_አጥንት ነው።

በዚህም ምክንያት #ከመቃብር ውስጥ አፅም ለማውጣት የሚቆፍሩ #ሱሰኞችን ለማስቆም የጸጥታ አካላት በመካነ መቃብር ሥፍራዎች የሚያደርጉትን ጥበቃዎች አጠክረው ቆይተዋል።

የሴራሊዮን ፕሬዚደንት የሆኑት ጁሊየን ማዳ ባዮ አስተዳደራቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ ያስገደደውን ይህንን እፅ / ኩሽ “ የሞት ወጥመድ ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን በአገሪቷ ላይም የህልውና ቀውስና ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ፕሬዚደንት ባዮ ፤ በእፁ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እንዳሻቀበ ተናግረዋል።

በመሆኑም በ ' ኩሽ ' እፅ ምክንያት የሚደርሰውን ቀውስ ለመከላከል በሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፤ ብሔራዊ ግብረ ኃይል እንዲቋቋምም መደረጉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ፎቶ/ቪድዮ ፦ ቻናል 4 እና አፍሪካ ኒውስ (ፋይል)

@tikvahethiopia