TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

በቀጣዮቹ 10 ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን በተሻለ መልኩ ይጠናከራሉ።

በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
  
በቀጣይ 10 ቀናት ....

አዲስ አበባ

ከኦሮሚያ ክልል ፦
- ቡኖ በደሌ
- ኢሉባቦር
- ጅማ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም ወለጋ
- ምዕራብ ሀረርጌ
- አርሲ እና ምዕራብ አርሲ
- ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ)
- ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች

ከአማራ ክልል ፦
- ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር
- ሰሜን እና ደቡብ ወሎ
- የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን
- አዊ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋህግምራ

ከትግራይ ክልል ፦ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፤ ምስራቅ፤ ደቡብ፤ እና ምዕራብ ዞኖች

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፦ መተከል፣ ፓዌ፤ አሶሳ ፣ ካማሺ ዞኖች

ከጋምቤላ ክልል ፦ ማዣንግ እና አኝዋክ ዞኖች

ከሱማሌ ክልል፦ ሲቲ እና ፋፋን ዞኖች

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጉራጌ፣ ሀላባ ፣ ስልጤ ፣ ጠምባሮ ፣ ሃዲያ ፣ የየም ልዩ ዞን

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦ ቤንች ሸኮ ፣  ዳውሮ ፣ ከፋ ፣ ሸካ ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጎፋ ፣ ጋሞ ፣ ኮንሶ ፣ ወላይታ ፣ ጌድኦ ፣ አማሮ ፣ አሪና ደራሼ ዞኖች

የሲዳማ ክልል ዞኖች

ሀረር እና ድሬዳዋ

... ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

ከዕለት ወደ ዕለት ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ፦
° ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤
° ከሱማሌ ክልል ጀራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች፤
° ከአፋር ክልል ቅልበቲ፣ ፈንቲ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች፤
° ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን፤
° ከጋምቤላ ክልል ንዌር እና የኢታንግ ልዩ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

#EthiopianMeteorologyInstitute

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

 በየዓመቱ ከ8 ቢሊዮን እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር በጀት ሊመደብለት ይችላል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ በየዓመቱ ከአገር ውስጥ ገቢ ምንጭ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ0.5 በመቶ እስከ አንድ በመቶ ያህል ለአረንጓዴ አሻራ እና ለተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ እንዲሰጥ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቅ አዋጁ ፤ " የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ለማቋቋም እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ " የሚል ስያሜ አለው።

ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?

ለም/ ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ በልዩ ፈንድ ከ2.8 ቢሊዮን ብር እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ በጀት ከመንግሥት ብቻ ሊቀርብለት ይችላል።

ልዩ ፈንዱ ዘጠኝ ዓላማዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ፦
- የተጎሳቆለ መሬት በተፈጥሮና በመልሶ ማልማት መርህ በመታገዝ እንዲያገግም ማድረግ፣
- የደን ልማትና የደን መልሶ ማልማትን መደገፍ፣
- የአገሪቱን የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግብ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
- የከተማ ማስዋብ እና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን መደገፍ የሚሉ ይገኙበታል።

የልዩ ፈንዱ የፋይናንስ ምንጮች ፦
1ኛ. የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው በጀት፣
2ኛ. የልማት አጋሮች፣
3ኛ. የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣
4ኛ. የግል ዘርፍ የሚሰጡት ድጋፍ ነው።

የፌዴራል መንግሥት ለፈንዱ ከሚመድበው በጀት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለልዩ ፈንዱ በተከፈተው የባንክ ሒሳብ በየ3 ወራቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ተቀማጭ ይሆናል። የሌሎች ምንጮች ድጋፍ የሚተዳደርበት አኳኋን የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያና የአሠራር ሥርዓት ይወሰናል።

መንግሥት የሚመድበው ዓመታዊ በጀት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መሥፈርት መሠረት ለፌዴራል መንግሥትና ለክልሎች ይደለደላል።

ለክልሎች ከሚደለደለው በጀት ላይ የእያንዳንዱን ክልል ድርሻ ለመወሰን የሚያገለግለውን የገንዘብ ሚኒስቴር አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይቀርባል። ሆኖም ለመሸጋገሪያነት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ቀመር በጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ከተደለደለው ዓመታዊ የሀብት ድርሻ ላይ በየ3 ወሩ ወደ ተጠቃሚ አካላት ገንዘብ ሊተላለፍ የሚችለው የሥራ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ፣ ክልሎች ተጓዳኝ በጀት ሲመድቡና በክልሉ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ፈሰስ ሲያደርጉ ይሆናል።

ክልሎች የሚመድቡት ዝቅተኛ ተጓዳኝ በጀት ተፈጻሚ የሚሆነው በተጓዳኝ በጀቱ መጠን ላይ በረቂቅ አዋጁ የልዩ ፈንዱ አስፈጻሚ አካላት በሚል የተዘረዘሩት ፦
° የገንዘብ ሚኒስቴር፣
° የግብርና ሚኒስቴር፣
° የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣
° የኢትዮጵያ ደን ልማት በክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች መካከል በሚደረግ ምክክር የጋራ ስምምነት ላይ ሲደረስና በየክልሉና በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤቶች ሲፀድቅ ነው።

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሳይተላለፍ የቀረ ገንዘብ በቀጣዩ ዓመት ለልዩ ፈንዱ ከሚመደበው በጀት ጋር ተደምሮ ይደለደላል።

የልዩ ፈንዱ ዓብይ ኮሚቴ አስፈጻሚ አካላት፦
° ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣
° ከኢትዮጵያ ደን ልማት
° ከክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች የበላይ ኃላፊዎች ይዋቀራል። የገንዘብ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ይሆናሉ።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከተጠቃሚ አካላት ሚቀበለውን የሒሳብ ሪፖርት በማጠቃለል የልዩ ፈንዱን ሒሳብ ዘግቶ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወራት ውስጥ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሚወክለው ኦዲተር እንዲመረመር የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ  እቃዎችን ለመወሰን በወጣው  መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ፦
➡️ ጤፍ፣
➡️ ስንዴ፣
➡️ ገብስ ፣
➡️ ማዳበሪያ ፣
➡️ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ይገኙበታል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ተቸ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፤ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

ሊቀመንበሩ በነበራቸው ቆይታ  ፦
- የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ
- የኑሮ ውድነት
- የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ
- ከሰሞኑን እየወጡ ስላሉ አዳዲስ አዋጆች
- ስለ ፖለቲካ ህዳሩ
- የመልካም አስተዳደር እጦት
- የኢኮኖሚ ጉዳይ ... ሌሎችም ተነስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም " መፍትሄው ምንድነው ? " ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፓርቲው ምላሽ ሰጥቷል።

ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ምን አሉ ?

“ የMacro Economy መናጋት አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የከፋ ሁኔታ ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው።

ይልቁንም ትኩረት የሚሹት ፦
➡️ ኢንፍራስትራክቸር፣
➡️ መብራት፣
➡️ ጤና፣
➡️ ውሃ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፤ ዜጎች በእነዚህ ነገሮች ተቸግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚል የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መቃኘት አለባቸው።

ከፍተኛ የሆነ የንግድ ጉድለት አለ። የምንሸጠው እና የምንገዛው ልዩነቱ የሰፋ ነው። የበጀት Deficit አለ።

መንግስት የሚሰበስበውና የሚያወጣውን ገንዘብ ለዚያውም አስፈላጊነታቸው አጠራጣሪ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘቡ ወጪ ይሆናል።

ይሄ ኢኮኖሚው እንዲናጋ አድርጓል ብለን እናምናለን።”

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-24

#ነእፓ #ኢትዮጵያ #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

#EMA
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ስፖርት #ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ።

ቡድኑ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ፍጻሜውን እስካገኘበት የሊጉ የመጨረሻ መርሃግብር ድረስ ከመቻል የእግር ኳስ ቡድን ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ነው ሻምፒዮን የሆነው።

ዛሬ በተካሄደ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

በዓመቱ 64 ነጥብ በመሰብሰብም ከመቻል በ1 ነጥብ በልጦ አጠናቋል።

መቻል በዓመቱ የፍጻሜ መርሃግብር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ተፋልሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም በ1 ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ተነጥቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ…
🔈#መልዕክት

" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦
- ሰላምን፣ 
- መረጋጋትን
- ፍቅርን
- አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ " - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ


#ኢትዮጵያ🙏

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል። ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ…
🔈#ማስታወሻ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ

" ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ፦
- ሰላምን፣ 
- መረጋጋትን
- ፍቅርን
- አንድነትን ለማስፈን ጾም እና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ "


ቋሚ ሲኖዶስ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም ማወጁ አይዘነጋም።

#ኢትዮጵያ🙏

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM