TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ENDF : ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ፥ " አሸባሪው ህወሀት የጀመረውን ማጥቃት ፤ በማያዳግም ሁኔታ እንቀለብሳለን " ብሏል።
ሚኒስቴሩ ከ3 ቀናት በፊት TPLF ጦርነት አውጆ በሁሉም ግንባር ውጊያ መክፈቱን ይህንንም በራሱ አባላት አንደበት መግለፁን ፤ እራሱ በከፈተው ውጊያም እየተቀጠቀጠ መሆኑን በመግለጫው ላይ ገልጿል።
መከላከያ ሚኒስቴር፤ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ከሠኞ ጀምሮ ውጊያ መክፈቱንና እራሱ በጀመረውም ውጊያ አይቀጡ ቅጣት እየደረሰበት መሆኑንም አክሏል።
ሰራዊቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህወሓትን ጥቃት የመመከት ውጊያ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ፥ የጠላትን ወራሪ ሀይል መመከት ብቻ ሳይሆን እየደመሰሰ የኢትዮጵያን ደህንነት እና ህልውና የማስከበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ በጠላትም ላይ ከባድ ኪሳራ እያደረሰና ሽንፈት እያከናናበ መሆኑ አሳውቋል። ይህንንም ገድል አጠናክሬ ቀጥላለሁ ብሏል።
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

#Mekelle : በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ ዘግቧል። የዛሬው ጥቃት በአራት ቀናት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተፈፀመ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐሙስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። የዛሬው የአየር ድብደባ ኢላማ ያደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዞታ የነበረ (ሰሜን ዕዝ)ና በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር…
#ENDF: የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈፅሟል።
ጥቃቱ በዚህ ሳምንት ብቻ 4ኛው ነው።
የዛሬው የአየር ድብደባ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል።
ገፁ የአየር ድብደባው የት እንደተፈፀመ በግልፅ ባይጠቅስም " ሌላው የአሸባሪው ቡድን የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆኗል" ሲል ገልጿል።
አክሎም ፥ " ይህ ማዕከል ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል ነበር በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በዚህ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚሠጥበት፤ የዉጊያ ግንኙነት ኔት ወርክ ያለበት ነው" ብሏል።
ሮይተርስ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪሎች እንዲሁም የሀገር ውስጡ ኢዜአ የዛሬው የአየር ድብደባ በመቐለ የተፈፀመ መሆኑን ዘግበዋል።

#ENDF : የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዛሬ በምእራብ ግንባር የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተገለፀ።
ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል።
ፎቶ : ፋይል
@tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ ዛሬ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ እና የሰው ኃይል ማደራጃ የሆነው ማይጠብሪ በአየር ተመቷል ሲል አሳውቋል።
ፎቶ : ፋይል
@tikvahethiopia
#ENDF
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የአየር ኃይል አዲሀገራይ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አዲቡክራይ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ ማዕከል ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።
በዚህ ማሠልጠኛው በአሁኑ ወቅት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ለሽብር ተልዕኮው የመለመላቸው በርካታ ታጣቂዎች እያሠለጠነበት የሚገኝበት ቦታ ነው ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

በመከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ በተመለከተ የመከላከያ ጀነራል ኢንስፔክተር ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ ምን አሉ ?
ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ (በኢቲቪ ቀርበው የተናገሩት) ፦
" ... ከሰሞኑ የማዕረግ ሹመት ጋር ሲታይ ትኩረቱ የተወሰኑ ብሄሮች ላይ ነው.. ሌሎች ተረስተዋል ... ምናምን የሚባሉ ነገሮች አሉ።
ውትድርና ከባድ ሞያ ነው ፤ የሰው ልጅ ያክል ጭንቅላት አሳምነህ ውጊያ ውስጥ አስገብተህ እንዲሞት አሳምነህ የምትመራበት ስራ ነው ፤ ቢቻል ሳይሞት እንዲወጣ አድርገህ የምትመራበት ስራ ነው ያ ልምድን ችሎታን፣ ብቃትን ይጠቃል እንጂ ዝም ብለህ የብሄር ተዋፅኦ ለመጠበቅ ብለህ ከግራም ከቀኝም ሰብስበህ መሾም ሀገርንም ተቋምንም ይገድላል።
ሰሞኑ በነበረው የማዕረግ ሹመት እንደ አንድ የካውንስል አባል ስለሚመለከተኝ የነበረውን ሂደት ስለማውቀው በተቻለ መጠን የብሄር ተዋፅኦ በጠበቀ መንገድ ለመስራት ተሞክሯል።
አንዳንዶቹ በጣም Junior ሳሉ የብሄር ተዋፅኦውን ለማምጣት ሲባል ከ Senior ዎች ጋር እንዲሾሙ የተደረጉ አሉ።
... መከላከያ የሚያስቀድመው አሁንም ስራን ማዕከል ያደረገ፣ የተቋሙን ተልዕኮ ሊያስፈፅም የሚችል፣ በሚመራው አሀዱ ተቀባይነት ያለው፤ በሚሰራው ስራ ብልጫ ላሳየ ኦፊሰር ቅድሚያ ይሰጣል። "
ያንብቡ : https://telegra.ph/ENDF-01-15

Telegraph
ENDF
#ENDF በሀገር መከላከያ ሰራዊት የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ በተመለከተ የመከላከያ ጀነራል ኢንስፔክተር ቢሮ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ ምን አሉ ? ሜጀር ጄነራል ክንዱ ገዙ (በኢቲቪ ቀርበው የተናገሩት) ፦ " ... የብሄራዊ ተዋፅኦን የማመጣጠን ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ አይደለም፤ ህገመንግስታዊ ነው። ህገ መንግስታዊ ስለሆነ በተቻለ መጠን የብሄራዊ ተዋፅኦን የማካተት ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ…
#ENDF
" የአልሸባብ ታጣቂዎች ያሉበት ቦታ በአየር ተደበደበ " - የሶማሊያ ሚዲያዎች
የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የትላንቱን የአልሸባብ አሻባሪ ቡድን የ " አቶ "ን ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላኖች የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ባሉበት ጋራስዌይን ላይ የአየር ድብደባ መፈፀማቸውን ዛሬ ምሽት እየፃፉ ይገኛሉ።
ቦታው ከሁዱር ወረዳ ከባኮል ክልል ዋና ከተማ በስተሰሜን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ስለደረሰ ጉዳት ያሉት ነገር የለም።
መረጃውን በተመለከተ እስካሁን በመከላከያ በኩል የተባለ ነገር የለም።
የኢትዮጵያ መከላከያ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሀገርን ሊዳፈር የሞከረውን እና አጠቃላይ የቀጠናው ስጋት የሆነው አልሸባብ ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት እስከወዲያኛው እርምጃ ሲወሰድባቸው በህይወት የተያዙም አሉ ፤ በርካታ የጦር እና የመገናኛ መሳሪያዎችም መያዝ ተችሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ለህ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ተወሰነ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አሁን በሥራ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል።
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ውሳኔ ካሰለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ ነው።
ምክር ቤቱ ፤ መከላከያ ሠራዊቱ የሪፎርም ስራ ውስጥ እንደሚገኝ አስታውሶ ይህን ሪፎርም የበለጠ ለማጎልበት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ከመከላከያ ሠራዊቱ ወቅታዊ እና የወደፊት ግዳጆች ጋር የሚጣጣም የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ መቅረቡን አመልክቷል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል #ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሙሉ ድምጽ እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
(የዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል)

#Update የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት፣ በመግባባት መፈታቱን አሳውቋል። ከዚህ ስምምነት በኃላ የፋኖ አባላቱ ምንድነው ያሉት ? ፋኖ ምሬ ወዳጁ ፦ " ያላሰንብነው መከላከያ ጋራ የሆነ accident ተፈጠረብን፤ መከላከያ ማለት በዚህ ትግል ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገ እጅግ የምንወደው የምናከብረው…
#ENDF
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ ሜጄር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን በሰሜን ወሎ ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት ምን አሉ ?
" ይሄ ችግር መረገብ አለበት። ለማንም ለምንም አይጠቅምም ፤ አሁን ደግሞ ችግር በውይይት ነው መፍታት የምትችለው ወይስ በጠብመንጃ ነው በጠብመንጃ የፈቱ ሀገሮች የትም የሉም። ህይወት ጠፋ ስለዚህ ሌሎችም ቢሆን ረጋ ብለው ይዩ ሁኔታውን ትክክል አይደለም ፤ በስተጀርባ ያለውን በትክክል ማየት አለባቸው።
ይሄ ግጭት ፤ ይሄ ንትርክ፣ ይሄ በየመንገዱ የነበረውን ሁከት ያቆመው ማንም አይደለም የሀገር ሽማግሌ መሃል እየገባ ነው ያቆመው ነፍሥ እንዳይጠፋ፣ ህፃናት እንዳይጎዱ ፣ የመንግስት እና የግል ንብረት እንዳይወድም ፣ ቤት እንዳይቃጠል ፣ ወንጀለኛ ያለአግባብ ተፈቶ እንዳይወጣ ከፍተኛ ስራ የሰራው የሀገር ሽማግሌ ነው።
ሌላው እዛ ያለው የፀጥታ ኃይልም ከሀገር ሽማግሌ ጋር ሆኖ መስራት አለበት ፣ ችግሩን ማስረዳት አለበት።
ሀገርን የሚጠቅም፣ ህዝብን የሚጠቅም መመሪያ ነው የወረደው ስለዚህ ያልተረዱና በጀርባ ሌላ መልክ የሚሰጡ ሰዎች ግፊት የተፈጠረ ችግር አሁን ህብረተሰቡ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ይሄንን ለመፍታት የመንግስትን መመሪያ ለማክብረ ተስማምተናል ከነሱ ጋር።
ሌላው በእነሱ ላይ ሲደርስ የነበረው ችግር፣ በእኛ ላይ አንዳንድ ነገሮች ይስተካከልልን የተባለው በሙሉ መንግሥት / የክልሉ መንግሥት ያደርጋል።
ስለዚህ ይሄን በተለየና በተጣመመ መንገድ የሚረዱ ሰዎች ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ነው እየቃኙ ያሉት ይሄ እንዲስተካከል ነው ጥረት ያደረግነው ፤ ችግሩን ለመፍታት በትዕግስት መከላከያ እየሞተም ቢሆን ለማስተካከል ጥረት አድርጓል ፣ ዛሬ ተሳክቶልናል። "
ሊንክ ፦ https://www.youtube.com/live/r17AHZmGQa4?feature=share

#ENDF🇪🇹
በሀገር ደረጃ ዛሬ 116ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተከብሯል።
ለመሆኑ በዓሉ ለምንድነው " ለ116ኛ ጊዜ " እየተባለ የሚከበረው ?
ይህ ቀን / ጥቅምት 15 የተመረጠው ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1900 ዓ/ም ያቋቋሙትን የጦር ሚኒስቴርን ታሳቢ በማድረግ ነው።
ከዚህ ቀደም የ " መከላከያ ሰራዊት ቀን " ተብሎ ሲከበር የነበረው ኢህአዴግ በ1987 ዓ/ም አዲስ የመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ አዘጋጅቶ በተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀበት ወቅት ነው።
በዚህ መነሻ የካቲት 7 ቀን በየዓመቱ ሲከበር ነበር።
ኢህአዴግ በውስጡ የነበሩት አመራሮች አጠቃላይ ሀገራዊ ለውጥ ካደረጉ በኃላ / በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የሀገር አስተዳደር የቀድሞው ውሳኔው " ከ1987 በፊት የነበረውን የኢትዮጵያ ሰራዊት እና የዘመኑ ትውልድ ተጋድሎን ውድቅ ያደረገና ቆርጦ ያስቀረ ነው " በማለት ቀኑን ወደ ጥቅምት 15 ቀይሮታል።
ቀኑ እንዲቀየር በተደረገው ጥናት ለበዓሉ መከበር መነሻ የሀገር ሰራዊት በቋሚነት ተደራጅቶ እንደ ተቋም የተመሰረተበት ቀን ሊመረጥ ችሏል።
ይህም ቀን ጥቅምት 15 /1900 ዓ/ም የአፄ ሚኒሊክ የጦር ሚኒስትር መ/ቤት ያቋቋሙበትና መስሪያ ቤቱን እንዲመሩ ሚኒስትር የሰየሙበት ቀን ነው።
ጥቅምት 15 /1900 ዓ/ም የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጦር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ፊትአውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ / አባ መላ ነበሩ።
የዘንድሮው የሰራዊት ቀን ለምን በወታደራዊ ሰልፍ ትርኢት ለማክበር ተፈለገ ?
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራት ኃላፊ ሌ/ጄነራል ዓለምእሸት ደግፌ ዛሬ በመስቀል አደባባር በተካሄደው ዝግጅት ላይ ባሰሙት ንግግር " በዓሉ በወታደራዊ ሰልፍ ትርኢት እንዲከበረ የተፈለገው ለእይታ ስለሚማርክ ብቻ ሳይሆን ዋናው እሳቢያችን ዛሬም ነገም ሰላማችንን ለማወክ የሚመኙ ካሉ ሁሌም ዘወትር ዝግጁ መሆናችንን ከወዲሁ ለማሳሰብ ነው " ብለዋል።
በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የሰራዊት ቀን በዓል ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የጦር ሰራዊት አመራር እና አባላት፣ የክልል ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ...እና ሌሎችም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው ነበር።