TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፀረ ሽብር ህግ⬇️

የጠቅላይ አቃቢ ህግ፣ የጸረሽብር ጉባኤ ጽ.ቤት እና የሲቪክ ማህበራት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት የጸረ ሽብር ህጉ እና የሲቪክ ማህበራት አሰራር ችግር ያለባቸው በመሆኑ ከህዝቡ #ሃሳብ ተሰብስቦ #ይሻሻላል፡፡

የጸረ ሽብር ህጉን ለማሻሻል ከነሃሴ 25 ጀምሮ በዋና ዋና ከተሞች ላይ ህዝባዊ ውይይት ተደርጎ ሃሳብ እንደሚሰበሰብ ነው በጋዜጣዊ መግለጫው የተመለከተው፡፡

በሲቪክ ማህበራት አሰራር ላይ ያሉትን አሰራሮች ለማሻሻል ደግሞ ከመስከረም 10 እስከ 14 ድረስ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶች ይካሄዳሉ፤ በዚህም ህብረተሰቡ ሰፊ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሲቪክ ማህበራት አሰራርን ችግሮች የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል ነው የተባለው በመግለጫው፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

" ኢትዮጵያ በኃይልና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳችም ነገር የለም " - የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር

ካለፉት ሳምንታት አንስቶ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ የመወያያ አጀንዳ እንደሆነ ይታወቃል።

በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ በቅርብ ርቀት ላይ እንደመገኘቷ የባሕር በር የማግኘት #ሃሳብ " የሕልውና ጉዳይ ነው " የሚል ንግግር ካደረጉ በኃላ በርካቶች የግላቸውን አስተያየት ሲሰጡ ነበር።

ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የባህር በር ለማግኘት ከጦርነትና ግጭት ውጭ የሆኑ ለጋራ ጥቅም የሰጥቶ መቀበል መንገዶችን ቢያብራሩም አንዳንዶች በዚሁ በባህር በር ጉዳይ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ወደ ጦርነት ትገባለች የሚል ስጋታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ፤ በባህር በር ጉዳይ ከየትኛውም የጎረቤት ሀገር ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማያስፈልግ በመግለፅ መሰል ሃሳቦች ካሉ መታቀብ እንደሚገባ ሲጠይቁ ነበር።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በዚሁ በኢትዮጵያ በኩል ስለተነሳው የባህር በር ጉዳይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ከነበሩት ውስጥ የጎረቤት ሀገር ዜጎችም የሚገኙበት ሲሆን #የወረራ_ስጋት እንዳላቸው ሲናገሩም ተደምጧል።

ሰሞኑን ስለሚሰነዘሩት አስተያየቶች ይመስላል የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በተከበረው የመከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል ላይ አጭር ነገር ተናግረው አልፈዋል።

ምን አሉ ?

" ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በአንዳንድ ጉዳዮች ውይይት ያስፈልገናል የሚል ጥያቄ ስታነሳ ወረራ ሊካሄድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ይደመጣል።

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በዚሁ በተከበረ ቀን መግለፅ የምፈልገው ኢትዮጵያ በኃይል እና በወረራ ማሳካት የምትፈልገው አንዳችም ነገር የለም።

ለጋራ ጥቅም ፣ ለጋራ እድገት ፣ ለጋራ ብልፅግና ሁሉም አሸናፊ በሚያደርጉ ጉዳዮች ከወንድሞቻችን ጋር ተወያይተን የጋራ ጥቅም የምናስከብር እንጂ በኃይል ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት ወንድሞቻችን ላይ ቃታ የምንሰነዝር እንዳልሆንን በአፅንኦት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ " ነው ያሉት።

@tikvahethiopia