TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.8K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጎንደር‼️

"ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች ቤት ተገኝተዋል።"

"37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡"
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት #መገኘታቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ገለጸ፡፡

የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል #አንገሶም_አርአያ ለአብመድ እንደተናገሩት መሣሪያዎቹ የተያዙት #በመተማ ዮሐንስ ከተማ በተቃጠሉ ግለሰቦች ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከጥይቶቹ በተጨማሪ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች፣ የቅስቀሳ መሣሪያዎች (ድምጽ ማጉያ) እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡ በአካባቢው ነባርና አዳዲስ ምሽጎች መገኘታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ጥይቶቹ የቅንቡላ፣ የአርፒጂ (የላውንቸር) እና የብሬን ናቸው፤ የእጅ ቦንብም ማግኘታቸውን ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡ መሣሪያዎቹ ለታንክ እና ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ ሆነው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ብቻ የሚፈቀዱ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

ክላሽ፣ ሽጉጦች፣ ስለታማ መሣሪያዎች፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ የደንብ ልብሶችም በተቃጠሉ ቤቶች ውስጥ መገኘታቸንም ነው ሌተናል ኮሎኔሉ ያረጋገጡት፡፡

አሁን የተገኙት የቡድን መሣሪያዎቹ ጥይቶቹ ናቸው፡፡ ሌሎች መሣሪያዎች አሁንም በግለሰቦቹ እጅ እንዳሉ እንደሚታመን ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም ተናግረዋል ፡፡ በቀጣይ የኅብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ ከክልሉ ፖሊስና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

ሰላም ለማደፍረስ የሚሠሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር በሚውሉበት ጊዜ መንግሥት በቶሎ ለህግ አለማቅረቡን መገምገማቸውንም ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡

ውሳኔዎች የዘገዩት የፍትህ ስርዓቱን ተከትሎና ማስረጃዎችን ከማሰባሰብ በኋላ የሚሰጡ በመሆናቸው መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና የህዝብ ደኅንነት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
#ኢትዮጵያ #ሱዳን #መተማ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመሸሽ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ አሳውቋል።

ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ብሏል።

እስካሁን በሱዳን ጦርነት ምክንያት #በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥርም በአጠቃላይ ከ12 ሺ በላይ መድረሱ ተመላክቷል።

ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በኩል ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት የመንግሥታቱ ድርጅት መሥሪያ ቤት መረጃን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia