TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቴሌብር #ኢትዮቴሌኮም

ገና በአጭር እድሜው 30 ሚሊየን ተጠቃሚ ያፈራ ፤ 370 ቢሊየን ብር በገበያ ያዘዋወረ ፤ ከ18 ባንኮች ጋር የተጣመረ ፡ እነሆ ቴሌብር ሱፐርአፕን አበሰረ!!!

ከእንግዲህ ለተለያዩ አገልግሎቶች በርካታ መተግበሪያዎችን አይጭኑም፦

በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም ስለተጣመሩ
ጊዜና ጉልበት ሳይባክኑ እልፍ ጉዳይዎን እዛው ይከውናሉ።

የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች፣ የምግብ እና ዴሊቨሪ አገልግሎት ሰጪዎች ኧረ ማን የቀረ አለ በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም በአንድ ተሰብስበዋል።

የስራ ውጥረት ሲበዛ የክፍያዎች ቀን ይረሳል ፤ ሱፐርአፕ አያንቀላፋም ቀደም ብሎ ያስታውሳል።

የደህንነት አጥሩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ፤ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ በፊት ገፅና በአሻራ

እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ
onelink.to/75zfa5 አውርደው ይሞክሩት

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ethiotelecom

በቴሌብር ሱፐርአፕ በአንድ ጊዜ ለበርካታ ሰዎች ገንዘብ መላክ ተችሏል !

በቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ገንዘብ ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ለመላክ የተቀባይ ቡድን በመፍጠር ለቡድኑ አባላት ተመሳሳይ ወይም የተለያየ የገንዘብ መጠን በአንድ ትዕዛዝ ለሁሉም እኩል ይልካሉ ጊዜዎን ድካምዎን ይቀንሳሉ!
ለሰራተኞችዎ ደሞዝ ክፍያ፣ ለወዳጅ ዘመድ ገንዘብ ሲልኩ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮችዎ ይጠቀሙበት ይወዱታል!

አዲሱን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ።

#ኢትዮቴሌኮም #ቴሌብር
#ኢትዮቴሌኮም

የመጀመሪያዋ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ደብረታቦር ገባች !

ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር የጥሪ ማሳመሪያ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ዛሬ አስረክበናል!

🎁 1 የ5ጂ ስማርት ስልክ ለአዳማዋ እድለኛ፣
🎁 2 ስማርት ቴሌቪዥኖች ለአዲስ አበባ እና ለአምቦ እድለኞች እንዲሁም
🎁 1 ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ደብረታቦር እድለኛ አስረክበናል!

በተጨማሪም እስከአሁን 2,352 የድምጽ ጥቅል፣ 1,030 የዳታ ጥቅል፣ 30 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋጋ ያለው የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ  ሽልማት ለዕድለኞች አበርክተናል፡፡

አሁንም ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ወደ 645 Y ብለው በመላክ ለሚደርስዎት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!

#ጥሪ_ማሳመሪያ_ጥሪት_ያተርፋል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን…
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንድ ሰው ከኢትዮ ቴሌኮም የገዛውን አክሲዮን ድርሻ ማዘዋወር፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ቢፈልግ ይችላል ወይ ? አትዮ ቴሌኮም አሁን የሚጀመረው የአክሲዮን ሺያጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውቋል። በዚህ ምዕራፍ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ብቻ መግዛት የሚችሉ ይሆናል። ዜጎች ድርሻቸውን ማዘዋወር ፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም የሚችሉት ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ምዕራፍ ብሎ…
#ኢትዮቴሌኮም #የሼርሽያጭ

ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር (Ethio Telecom S.c) 10% በመቶ ድርሻውን መሸጥ የሚያስችለውን ሥርዓት (Mini App) በቴሌብር ሱፐር አፕ መተግበሪያው ላይ አካቷል።

ዜጎች ይህንን ሼር ከመግዛታቸው አስቀድሞ ስለ አጠቃላይ የሼር ሽያጭ የቀረበ ዝርዝር መረጃ (prospectus) አንብበው መስማማታቸውን መግለጽ ይኖርባቸዋል።

ይህ ዶክመንት ምን ይላል ?

ዶክመንቱ ፥ የሼር መጠን ፤ መግዛት ስለሚቻለው የሼር ብዛት፤ ስለ አክሲዮን ማኅበሩ ዳራ፤ የሂሳብ ሪፖርት መረጃዎችን፤ ቀነ ገደቦችን፤ ስጋቶችን፤ ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሂደቶችን፤ የሼር አከፋፈል ሥርዓቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ነው።

ሂደቶቹ ምን ይመስላሉ ?

ዜጎች በ prospectus ዶክመንቱ እንዲሁም ውል እና ሁኔታዎች (Terms and conditions) ከተስማሙ በኃላ መግዛት የሚፈልጉትን የሼር መጠን በመምረጥ ያመለክታሉ።

የመኖሪያ አድራሻ ፣ መታወቂያ ፣ ፎቶ ፣ ስልክ ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎችን ከተሞላ በኋላ ሼር ለመግዛት ማመልከት ይቻላል። እነዚህን መረጃዎች ለማስተካከል እና ክፍያ ለመፈጸም 48 ሰዓት ተሰጥቷል።

ሼር ለመግዛት ካመለከቱ በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም የክፍያ ሂደቱን እንዲሁም ያስገቡት ዝርዝር መረጃ የማጣራት ሂደት የሚያካሂድ ሲሆን ሂደቱን ካለፉ የተሳካ ማመልከቻ ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ። ሂደቱን ካላለፉ መሰረዞን የሚገልጽ መልዕክት ይደርሶታል።

(የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ እንዲሁም ፎቶ ሲያነሱት በሚታይ መልኩ እንዲሆን ይመከራል)

ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው በላይ ግዢ ከተፈጸመ ምን ይደረጋል ?

መሸጥ ከሚታሰበው በታች ሼር ከተሸጠ ሼር ለመግዛት ያመለከቱ በሙሉ የጠየቁትን የሼር መጠን የሚያገኙ ይሆናል።

ሆኖም የሼር ግዢ ጥያቄው ከተቀመጠው በላይ ከሆነ በprospectus ዶክመንቱ መሰረት የአክሲዮን ድልድል (Allotment of Shares) ይካሄዳል።

ይህም ሼር መሸጥ ከሚያበቃበት ታኅሣሥ 25 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል።

ይህ ድልድል በተመጣጣኝ ድርሻ ስሌት (Pro-rata Algorithm) የሚካሄድ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ነው። ይህም እያንዳንዱ አመልካች ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲደርሰው የሚያስችል ነው።

ለምሳሌ ፦  አንድ ሰው 100 ሼር ግዢ ለመፈጸም ጥያቄ አቀረበ። የተመጣጣኝ ድርሻ ስሌቱ (Pro-rata Algorithm) ሁሉም 70% እንዲደርሳቸው ቢወስን 100 ሼር ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበው ሰው የሚደርሰው 70 ሼር ይሆናል ማለት ነው።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ድልድሉ ጥር 23/2017 ዓ.ም በይፋ ለህዝብ በይፋ ይገለጻል።

ተመላሽ ክፍያ በተመለከተ ?

አመልካቾች ድልድል ከተደረገ በኋላ የደረሳቸው የሼር መጠን ያክል ክፍያ ተቆርጦለት ቀሪው ገንዘብ ከአገልግሎት ክፍያው ጋር ተደምሮ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

ገንዘቡ ድልድሉ ይፋ በሆነ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል። ዜጎች ሼር ለመግዛት ካመለከቱ እና ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ድልድሉን አለመቀበል አይችሉም።

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር 10% ድርሻ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሽያጭ የሚደረግበት ይሆናል። በተጨማሪም ዜጎች ለራሳቸው እና ህጋዊ ውክልና ላላቸው ዜጋ ግዢውን መፈጸም ይችላሉ።

ከዚህ የሼር ሽያጭ ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝ ሲሆን። ከአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 450 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል። መንግሥት ሙሉ ለሙሉ የቀረበው ሼር ተሸጦ ካለቀ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ብቻ 67.5 ሚሊዮን ብር ያገኛል።

አክሲዮን ማኅበሩ፥ በኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ገበያ ዝርዝር ውስጥ ለመካተት (Listing) የሚያስችለውን ዝግጅት የሼር ሽያጩ ካበቃ በ12 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን በዶክመንቱ ተገልጿል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopia