TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ካህኑን ማን ገደላቸው ?

" ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ?

(ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ)

ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦

" ትላንት/መጋቢት 14 ቅዳሴ ቀድሰው በአጋጣሚ እኔ በውጪ አስቀድሼ ነበር ፤ ወደ ደጀሰላም ገባን ምግብ ተመግበን ተለያይተን ነው እነሱ ወደ ኃላ ነበሩ ከምግብ በኃላ እኛ እዚህ አካባቢ ነበርን ተሻግረው ቤታቸው ቆይተው የሌላ (ቄስ አሰፋ ይባላሉ) የእሳቸው ቤት ነው የፈረሰው የእሳቸው ቤት ፈርሶ ሊሻገሩ ገና ከቤታቸው ወጥተው ትንሽ እራመድ እንዳሉ ነው ተመቱ የሚባል ወሬ ሰማን።

ተደወለና ባጃጅ አምጡ ተብለን እስከቤታቸው ድረስ እንደምንም ተቋቁመውት ሄደዋል ከቤታቸው በኃላ አንድ ካህን አብረው ይዘዋቸው መጡ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲደርሱ ተሸነፉ ወደቁ ፤ እኔ ለማናገር ሞከርኩኝ ምንድነው ? ምን ሆነው ነው ? ምንድነው የተፈጠረው ? ስላቸው ምንም ሊመልሱልኝ አልቻሉም ወዲያው ተናነቃቸው ባጃጅ ላይ አስገባናቸው ወደ ክሊኒክ ወሰድናቸው እዛሪ ሪፈር ተባለ ወደ ጥሩነሽ (ሆስፒታል) ወስደው ሌሊት አረፉ የሚለውን ሰማሁ በጣም አዝኛለሁ። "

ቃላቸውን የሰጡ አገልጋይ ሁለት ፦

" ዘጠኝ ሰዓት ከለሊቱ አረፉ ይሉኛል የደብሩ ዋና ፀሀፊ ፤ እንዴት ? አልኳቸው ፈረሳ ነበረና እዛ ፈረሳ እኔ መጠምጠሜን አልያዝኩም፣ ጋቢም አልያዝኩም ማንም ያወቀኝ ሰው የለም ካህንም ልሁን ምዕመንም ልሁን አሉ፤ እሳቸው ግን ጋቢያቸውን ቆባቸውን አድርገው መጥተው እዛ ነው የደበደቧቸው አሉኝ።  ቅዳሴ ውለዋል ቀድሰው እዛ ማዶ ፈረሳ አለ  ሲባል ግን የኛ የማርያም አገልጋዮችም የፈረሰባቸው ነበረና እዛ ሄጄ አብሬም ልቀላቀል ፤ ባለኝ አቅም ልርዳቸው ብለው ነው ተነስተው የሄዱት፤ እጂ ቀድሰው ውለው ነው የሄዱት። "

ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን ሶስት ፦

" የአሟሟታቸውን ሁኔታ ሲነግሩኝ በዕለቱ በ14 ማለት ነው ፤ ቅዳሴ ቀድሰው ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው አቀብለው ወጣ እንዳሉ ነው ያልታወቁ ሰዎች መንገድ ላይ አደጋ ያደረሱባቸው የሚል ነው የተሰጠኝ መረጃ።

ቤት የላቸውም ፤ ስለቤቴ ብለው የተከራከሩትም ነገር የለም መንገድ ላይ እየሄዱ ነው የሌላ ሰው ቤት ፈርሶ ወደዚያ ለማስተዛዘን ሲሄዱ ነው ጥቃት የደረሰባቸው ብለው ነው የነገሩኝ አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች። "

ቃላቸው የሰጡ ምዕመን አራት፦

" ባጃጅ ላይ ስናስገባቸው አንድ ነገር ብቻ ነው የተናገሩት ' እባካችሁ እዚሁ ቤተክርስቲያን አድርጉኝ አትውሰዱኝ ' ሲሉ ተነፈሱ ከዚያ መናገርም አልቻሉም ፤ ውሃም ስንሰጣቸው መቀበል አልቻሉም እዛም ስንወስዳቸው መረጃ ሊነግሩን አልቻሉም "

የካህኑ ልጅ ፦

" ቤት ሲመጣ ደም ደምቶ እራሱ ላይ ነጠላ አድርጎ ነው የመጣው ከዚያ በኃላ ምን ሆነህ ነው ስለው መተውኝ ነው ያለው ሌላ ቄስ ነበሩ መጡና ሃኪምቤት ወሰዱት።

ሃዘን ናፍቆት ነው የሚሰማኝ አባ አባቴ ስለው በጣም ነው የምወደው ስለዚህ ካለሱ ማንም የሚያሳድገኝ የለም። "

ቀሲስ ዐባይ መለሰ በምዕመኑ እጅግ የሚወደዱ፣ የሚከበሩ፣ ሰርተው የሚያሰሩ ያላቸውን ሁሉም አቅም ለቤተክርስቲያኗ የሚሰጡ ትልቅ አባት እንደነበሩ ምዕመናኑ ገልጸዋል።

ካህናት በአካባቢው ላይ የተፈፀመው ድርጊት ፍርሃት ላይ እንደጣላቸው የተገለፀ ሲሆን በእሳቸው ህልፈት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንዳሉ ተጠቁሟል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ ምን አለ ? ያንብቡ : https://telegra.ph/Police-03-24-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#ተጨማሪ

የቀሲስ ዐባይ መለሰ ግድያ በስፋት ተሰማ እንጂ የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ባለችበት አካባቢ ብዙ ፈተና ይገጥማት እንደነበር አገልጋዮችና ምዕመናን ለ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን " ተናግረዋል።

እዛው ቤተክርስቲያን አካባቢ ስልክ የተቀሙ ፣ ጩቤ በያዙ ሰዎች ማስፈራሪያ የደረሰባቸው ፣ ሻሽ ጠምጥመው ሲሄዱ #የተመቱ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ያለውን ችግር የሚመለከታቸው አካላት እንዲያዩ ጠይቀዋል።

አንድ ምዕመን ፤ " ቤተክርስቲያን አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምባት መሆኗን ገልፀው ተልዕኮዋን ለማስፈፀም ሰላም ያስፈልጋታል " ብለዋል።

" የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ይህች ቤተክርስቲያን ከሚገባው በላይ እየተጎዳች ስለሆነ ጉዳቷን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ የግድ ነው ፤ መስዋዕትነት መክፈልም ያስፈልጋል ምክንያቱም ቅዱስ ስጋ ክቡር ደሙን ካልተመገብን እኛ ሀገረ እግዚአብሔርን አናገኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

መንግስት የመጀመሪያ ስራው ህግ ማስከበር መሆኑን የገለፁት እኚሁ ምእመን እንዲህ ያለ ጥቃት (በቀሲስ ዐባይ መለሰ ላይ የደረሰ) እንዳይደርስ ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ተገቢ የሆነ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባዋል " ብለዋል።

" ትልቁ ችግር መንግስት ስራውን ባለመስራቱ ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ ያለው " የሚሉት ምዕመኑ " መንግሥት ከማንኛውም ነገር በፊት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ሰላም ለማስከበር ነው ፤ ዜጎች የፈለጉበት ቦታ ሰርተው ፤ ጥረው ግረው እንዲኖሩ ዕልውናቸውንና ደህንነታቸው / ዕልውናችንን መጠበቅ ነው " ሲሉ  አስገንዝበዋል።

" ይህ ባለመሆኑ ነው ሰው በወጣበት የሚቀረው እዚሁ ሰፈሩ ውስጥ ጥቃት የሚደርሰው ፤ መንግሥት እንዲያህ አይነት ድርጊት እንዳይፈፀም ስራው ባለመስራቱ ነው ችግር እየተፈጠረ ያለው ፤ መንግስት ስራውን ሊሰራ ይገባል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#SPORT : ኢትዮጵያ በጊኒ ተሸነፈች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድናችን #የአፍሪካ_ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ አቻው ጋር አድርጓል።

ጨዋታውን ያደረገው በሞሮኮ " ሞሀመድ አምስተኛ " ስታዲየም ነው።

በዚህም ጨዋታ ብሔራዊ ቡድናችን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አሁን ያለው የምድቡ ደረጃ ፦

1ኛ. ግብፅ 6 ነጥብ
2ኛ. ጊኒ 6 ነጥብ
3ኛ. ማለዊ 3 ነጥብ
4ኛ. ኢትዮጵያ 3 ነጥብ

ብሔራዊ ቡድናችን ከቀናት በኋላ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን #ከጊኒ ጋር ያደርጋል።

More : @tikvahethsport    

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።

የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።

- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
👉 የሒሳብ፣
👉 የአካባቢ ሳይንስ፣
👉 አማርኛ፣
👉 አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።

- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።

- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።

- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።

- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.me/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
የትኞቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ ናቸው?

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች።

በስምምነቱ መሰረትም ፈራሚ ሀገራት መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ እንዳለባቸው ይጠቅሳል። (አንቀጽ 24፣ 3/ለ)

በተጨማሪም ፈራሚ ሀገራት [መስማት የተሳናቸው ሰዎች] በሁሉም የሕግ አሠራር ሂደቶች ከሌሎች ጋር በእኩልነት አስተማማኝ የፍትሕ ተደራሽነት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸውም ይላል፡፡ (አንቀጽ 13)

እርሶ በየትኛው የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋም መስማት የተሳናቸው ዜጎችን በተለይ ሴቶችን ያማከለ አገልግሎት ሲሰጥ ታዝበዋል? 👉 @RW_Ethiopia ያካፍሉን

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia
#Wolkite

ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ደቡብ ክልል፣ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ስለማድረጋቸው አሳውቀዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ፤ " የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው። " ያሉ ሲሆን " በዛሬው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለን ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ወልቂጤ ከተጓዙ ባለስልጣናት መካከል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይገኙበታል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቂጤ ጉዞ ጋር በተገናኘ ዛሬ የማህበራዊ መገናኛዎች ትኩረት ሆኖ የነበረው በከተማው የነበረው የእንቅስቃሴ / የስራ ማቆም አድማ እንዲሁም ደግሞ የሚጠበቀውን ያህል የከተማው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ አቀባበል አለማድረጉ ነበር።

በወልቂጤ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ ከተማዋ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ እንደነበር አመልክተዋል ፤ ይህ የሆነውን ህዝቡ እየጠየቀው ካለው #የክልልነት_ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

ምንም እንኳን የዞን ምክር ቤት በክልል መደራጀትን ውሳኔ አሳልፎ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢያስገባም እንዲሁም የክላስተር አደረጃጀትን እንደማይደግፍ በአብላጫ ድምፅ ቢወስንም የክልልነት ጥያቄው ግን ምላሽ እንዳላገኘ ይህ ደግሞ የህዝቡን ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" ህዝቡ መብቱን ነው የጠየቀው ፤ ለዚህ ደግሞ ኃይል ፣ እስር ፣ ማሳደድ፣ ማፈን መልስ አይሆንም መንግሥት አሁንም የያዘውን ግትር አቋሙን መልሶ ማጤን ይገባዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

በዞኑ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ አመራሮችን ጨምሮ በርካቶች ታስረው እንደነበር አይዘነጋም። በተጨማሪ ዞኑ ላይ የአመራር ለውጦችም ተደርገዋል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት ለመክፈል በተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ በወላይታ (እንዲደገም) ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ ዞኖች፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ፣ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ላይ በቅርቡ ህዝበ ውሳኔ መደረጉ ይታወቃል።

አንድ ላይ እንዲቀጥለው የተባሉት ሀዲያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል የጉራጌ ዞን የክላስተር የአደረጃጀትን ውሳኔ ቀደም ብሎ ያልተቀበለው / በምክር ቤቱም በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ያደረገው ዞን እንደነበር አይዘነጋም።

Photo : PM OFFICE & TIKVAH WOLKITE FAMILY

@tikvahethiopia