TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Addis Lisan (1).pdf
" ቀሪዎቹ 3 ሺህ 69 ቤቶች ከሁለት ወር በኃላ ጨረታ ይወጣባቸዋል " - ኮርፖሬሽኑ

የ4ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ጨረታ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን 5 ሺህ 397 ቤቶች ለጨረታ ቀርበው 2 ሺህ 328 ቤቶች አሸናፊ እንደተገኘላቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ4ኛ ዙር 40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ጨረታ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ኮርፖሬሽኑ ለአዲስ ልሳን ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ በአጠቃላይ ለጨረታ የቀረቡት ቤቶች 5 ሺህ 397 ሲሆን ለዚህም 52 ሺህ 600 አካባቢ ሰነድ መሸጡን ገልጿል።

ሰነድ ከገዙት ውስጥ የተፈለገውን መስፈርት አሟልተው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ያስገቡት 30 ሺህ ደገማ እንደሆኑ እና ከነዚህም ውስጥ 2 ሺህ 328 ቤቶች አሸናፊ እንደተገኘላቸው ተመላክቷል።

የጨረታ መነሻ ዋጋ 23 ሺህ 804 ብር ከ44 ሳንቲም እንደሆነ ያስታወሰው ኮርፖሬሽኑ ከሰነድ ሽያጭ 21 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደተሰበሰበ አሳውቋል።

ጨረታው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ቅሬታ ማቅረብ ይቻላል የተባለ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 ሺህ 69 ቤቶች ጨረታ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ከሁለት ወር በኃላ ጨረታ ይወጣባቸዋል ተብሏል።

ጨረታ የወጣባቸው ቤቶች በ13 ሳይቶች የሚገኙ ሲሆኑ እነዚህም ፦
👉 ቦሌ ቱሪስት እና ንግድ ሳይት
👉 ህንፃ አቅራቢ ሳይት ቡልቡላ ሎት 1 እና ቡልቡላ ሎት 2
👉 አስኮ ሳይት
👉 ክራውን ሳይት
👉 ሰንጋ ተራ ሳይት
👉 መሪ ሎቄ
👉 ሰሚት ሳይት 1፣2፣3 እና 4
👉 ቦሌ ባሻሌ ናቸው።

አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር በዚህ ይመልከቱ : https://t.me/tikvahethiopia/77305

Credit : Addis Lisan

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Wolkite ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ደቡብ ክልል፣ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ስለማድረጋቸው አሳውቀዋል። ውይይቱን ተከትሎ ፤ " የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው። " ያሉ ሲሆን " በዛሬው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል። በየደረጃው…
ምን ተጠየቁ ?

ዛሬ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር የተወያዩት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከተሳታፊዎች በክልል መደራጀት ጥያቄ፣ የልማት ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

የክልልነት ጉዳይን በተመለከተ አንድ ተሳታፊ አባት "የክልሉ ጉዳይ መቼ፣ እንዴት፣ በምን አይነት ሁኔታ ምላሽ ያገኛል የሚለው ቢቀመጥ" ሲሉ ዶ/ር ዐቢይን ጠይቀዋል።

አንድ ሌላ ተሳታፊ (ሴት) የክልልነት ጥያቄው የተጠየቀው "ማንነታችንን፣ ባህላችንን ለማሳደግ ታሳቢ በማድረግ ነው፤ ይሄን ብልፅግና ይመልስልናል ባህላችን፣ ቋንቋችን ያደገበት ሁኔታ የለም ፤ ቋንቋችንን፣ ባህላችንን ለማሳደግ የቱሪዝም ስራዎችን ወደ አካባቢያችን ለመሳብ እንዲሁም የልማት የጠቃሚ እንድንሆን በተለይም የውሃ፣ የመብራት ፣ መንገድ ችግሮችን ክልል ብንሆን መመለስ ይቻል ይሆናል በሚል ታሳቢ በማድረግ ነው የተጠየቀው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ምን ምላሽ ሰጡ ?

የክልልነት ጥያቄው በህግ አግባብ ብቻ ምላሽ ያገኛል ብለዋል። ጥያቄው ከተነሳ ጊዜ አንስቶ ምላሽ ለመስጠት በተሰራበት የህግ አግባብ ዛሬና ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቢስተናገድ የተሻለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ክልል የሚባለው ቢመለስ በ6 ወር ደመወዝ ባትከፍሉ ጭቅጭቅ ይቀራል ? አይቀርም፤ ክልል ያልነው እኮ ለልማት ብለን ነው እንጂ 10 ሰው ኮብራ እንዲይዝ አይደለም ትላላችሁ አይቀርም። አሁን መክረን ዘክረን የነገውንም ታሳቢ አድርገን መወሰን ይጠቅማል "

በሌላ በኩል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከልማት ጥያቄዎች ጋር በተየያያዘ በተለይም የውሃ፣ መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ት/ቤት ጥያቄ ቀርቦላቸው መልሰዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ባለፉት ዓመታት መንግስት በዞኑ ያለውን ችግር ለመፍታት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ያሉ ችግሮችን በእርጋታና ንግግር ይመለሳል ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ "ውሃ እየጠየቅን የቧንቧ መስመር የምንሰብር ከሆነ፣ መንገድ እየጠየቅን ድልድይ የምናፈርስ ከሆነ ወደምንፈልገው ነገር አያደርስም፤ ወደምንፈልገው የሚያደርሰን በተረጋጋ መንገድ ተወያይተን፣ ተመካክረን፣ ጊዜ ወስደን ምላሽ መስጠት ስንችል ነው" ብለዋል።

ፌዴራሉ መንግስት ከክልል ጋር በመመካከር አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ይፈልጋል ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " በምንችለው ልክ አጣዳፊ የሆኑ እንደ #ውሃ ያለውን ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ያለፉትንን ዓመታት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደነበረች ሊዘነጋ አይገባም ያሉት ዶ/ር ዐቢይ በሁሉም ቦታ የልማት ጥያቄዎች አሉ እንደ ሀገር ያለንን አቅም በውጤታማነት ጊዜን በመጠበቅ ከመጠቀም ያለፈ አማራጭ የለም ብለዋል።

ከልማት ስራ ጋር በተያያዘ መንገድን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተጀመሩ የመንገድ ስራዎችን ለማስጨረስ የሚያስፈልገው ገንዘብ 1 ትሪሊዮን መድረሱን ገልፀዋል።

"የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ አመት በጀት እዛ አልደረሰም" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ሙሉ በጀት መንገድ ላይ ቢውል እንኳን አዲስ ሊሰራ ቀርቶ የተጀመረውን አይጨርስም ስለዚህ ጊዜ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ "ጦርነት ውስጥ ነበርን፣ የዓለም መንግስታት ባይናገሩትም በብዙ መንገድ መደገፍ በሚገባቸው ልክ ሳይደግፉን የያዙን ጊዜ ነበር፣ ድርቅ ያጋጠመን ጊዜ ነበር፣ ብዙ ወጀቦች ያለበት ጊዜ ነው እንደዛም ሆኖ በየቦታው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ የሚሰጡ እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጡ አይደሉም" ብለዋል።

አክለው "ትንሽ ጊዜ መረጋጋት ከቻልን ነገሮች ወደ ሰላም እየሄዱ ስለሆነ በውስጥ ያለንን አቅም ከውጭም የምናገኛቸውን ድጋፎች ጨምረን በርካታ የልማት ስራዎችን ለመስራት እንሞክራለን" ሲሉ ተናግረዋል። /fbc/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የሰላም_ጥሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ተከታዩን የሰላም ጥሪ አቅርቧል  ፦ 1. ሦስቱ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ በስምምነቱ መሠረት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ መጥተው በበዓታቸው ተወስነው እየኖሩ ስለሆነ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው እንዲደረግ፣ 2. ሃያ አምስቱን ግለሰቦችን በሚመለከት ምንም እንኳን በሕ-ወጥ አድራጐታቸው የቀጠሉ…
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን " ጥያቄ #መቼም_ቢሆን የማትቀበለው መሆኑን አስታወቀች።

በዛሬ ዕለት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ የቀድሞ አባቶች መካከል ውይይት ተደርጎ እንደነበር ተሰምቷል።

ውይይቱን በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

በመገጫውም ፤ ቅዱስ ሲኖደስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦች በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ ቤት የይቅርታ ማመልከቻ እንዲያስገቡ ጥሪ አስተላልፎ እንደበር አስታውሷል።

ቢሆንም በይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ከተመለሱት ከአንዱ " አባ " ኃይለ ኢየሱስ ውጭ ሌሎች በይቅርታ ከመመለሰ ይልቅ ለውይይት እና ሕገ ወጥ ድርጊቱም #እንዲጸድቅላቸው መጠየቃቸውን ገልጿል።

" ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት የሰላም ዓደባባይ የንስሓ ሰገነት በመሆኗ ለፍቅር ረጅም ርቀት በመጓዝ ከግለሰቦቹ ጋር በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ እንዲሁም በሌሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት ተወያይታለች " ያለው መምሪያው " ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ሰላም የኢትዮጵያውያን የደኅንነት ኑሮ በእጅጉ ስለሚያሳስባት በብዙ ርቀት ለይቅርታ በሯን ከፍታ ስትጠባበቅ ነበረች " ብሏል።

ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ እና ሁሉንም እንወክላለን ያሉ 6 ግለሰቦች ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይቱ ግን የተዘረጋው የቤተ ክርስቲያን የፍቅርና ይቅርታ እጅ በግለሰቦቹ ግን እንደመልካም አልታየም አሳውቋል።

ከዚህ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከተደረሱ 10 የስምምነት ነጥቦች መካከል በተራ ቁጥር 6 የሚገኘው ውሳኔ "በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት "አባቶች" ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው ይመለሳሉ" የሚል ቢሆንም ግለሰቦቹ ግን በመርሕ ደረጃ ስምምነቱን እንቀበለዋለን በአፈጻጸም ደረጃ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ሹመታችንን ያጽድቅልን" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን መምሪያው በመግለጫው አስረድቷል።

ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሕገ ወጦቹን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኗን መምሪያው አሳውቋል ፦

1ኛ. በየትኛውም መንገድ የጋራ ውይይት አይኖርም፤

2ኛ. ለይቅርታ የሚመጡ ከሆነ በቡድን ተሰባስቦ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እንዲሆን፤

3ኛ. የይቅርታ ማመልከቻውን እያንዳንዳቸው ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዚህና በሌሎች መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ 21/07/2015 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተይይዟል)

@tikvahethiopia
ፎቶ / ቪድዮ ፦ የቀድሞው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

አቶ ስብሃት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ለህክምና መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አቶ ስብሐት ነጋ ለፍ/ቤት በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ገልፀው ህክምናቸውን አድርገው ለመመለስ ወደ ውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸው ክስ መስርተው እንደነበር ይታወሳል።

በህዳር 23 ቀን 2015 በነበረ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍትሃብሔር ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት አቶ ስብሃት ነጋ ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ #ተገቢ_አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ነበር።

ይኸው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመፈጸሙን ተከትሎ አቶ ስብሃት በጠበቃቸው አማካኝነት ውሳኔው እንዳልተፈፀመላቸው ገለጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።

በዚህም በቀረበው አቤቱታ መነሻ ለምን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳልተፈጸመ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች  ቀርበው  እንዲያብራሩ ከተደረገ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔው እንዲፈጸም በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

አቶ ስብሃት ነጋ በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ  ከብዙ መጉላላት በኋላ ለህክምና ከኢትዮጲያ ወደ ውጭ ሀገር መውጣት ችለዋል።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
Video / Photo : Social Media

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) መግለፃቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ትላንት…
ፎቶ፦ ዛሬ የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፤ የመንግስት ኃላፊዎች፤ ከኖርዌይና ከተለያየ አካባቢ የመጡ የውጪ ሀገር ወዳጆቻቸው እና በበርካታ ምዕመናን በተገኙበት ነው።

Photo Credit : EOTC TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ በትላንትናው ዕለት የተደረገውን ጥሪ በመቀበል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመቀበል በዛሬው ዕለት ወደ እናት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን የሚገልዕ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በማቅረብ በይፋ መመለሳቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፦

- ወደ ሥራ እንደምትመልሳቸው
- ደመወዛቸውን እንደምትከፍል
-  የታሸገውን ቤታቸውን በመክፈት እንደምታስረክባቸው ገልጻለች።

@tikvahethiopia