TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.8K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የተሽከርካሪ አደጋው ያጋጠመው ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያአበሎ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል #ኮንሶ ከተማ #ኮንትሮባንድ_ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ተሽርካሪ ከተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በያአበሎ ወረዳ ኛሮ ቀበሌ ኤላ ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋም ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ከቦረና ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክተታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia