TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ የአቶ ሙላቱ ጉጆ የወንድሙ ልጅ በሁላ ወረዳ ጫልቤሳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አግብታ ሄዳለች። በሲዳማ ባህል መሰረት ሴት ልጅ አግብታ ከአከባቢ ከሄደች በኃላ የልጅቷ ቤተሰብ የዘመድ ልጆችን እና የልጅቷን ጓደኞች ሰብስቦ የተዳረችውን ልጅ ጥየቃ ፤ የሚበላ ነገር አስይዞ ይልካል። በዚህ መሰረት የአቶ ሙላቱ ጉጆ ልጅ የአጓቷ ልጅ አግብታ ወደሄደችበት በቀን 11/03/15 ዓ.ም ከቤተሰብ…
#Update

15 ዓመት ተፈርዶበታል !

ከሁለት ሳምንት በፊት በሲዳማ ክልል ፤ " የሁላ ወረዳ ፍርድ ቤት " አንዲት የ13 አመት ታዳጊን የደፈረ ግለሰብ ላይ የ3 አመት ከ9 ወር የፍርድ ውሳኔ መስጠቱ #ብዙዎችን_ያስቆጣ እንደነበር አይዘነጋም።

የተበዳይ ቤተሰቦች ባቀረቡት ይግባኝ መሰረት ባንሳ አከባቢ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ዛሬ ጥር 3 ቀን 2015 በይርጋለም የቀረበውን አቤቱታ በመመርመር የቀድሞውን ውሳኔ በመሻር አጥፊው በ15 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ማስታወሻ : https://t.me/tikvahethiopia/75508

Credit : Ermias Elias (HO)

@tikvahethiopia
የ17 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የአራት አመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በአማራ ክልል ፤ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ 018 ቀበሌ ንዋሪ የሆነው ክንድየ ግዛቸው የተባለ ግለሰብ ታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ/ም የዚሁ ቀበሌ ንዋሪ የሆነች  የ4 ዓመት ህጻን ከምትጫወትበት ቦታ አታሎ ወደ ጫካ ውስጥ ካስገባት በኋላ ደፍሯት ለመሰወር ይሞክራል።

ምንም እንኳን ግለሰቡ ለመሰወር ቢሞክርም የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፀጥታ ኃይል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ተጣርቶበት መዝገቡ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ይላካል።

ጉዳዩን የተመለከተው የጎንቻ ወረዳ ፍርድ ቤት ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማረጋገጡ ዛሬ ጥር 3 ቀን 2015    ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ክንድየ ግዛቸው በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

የተደፈረችው ህጻን ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰባት በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላት እንደሚገኝ ታውቋል።

ምንጭ፦ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ ረቡዕ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ተመርቋል።

ስለ ማዕከሉ ምን ይታወቃል ?

- ማዕከሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሊዝ ነፃ ባቀረበው በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያለው መሬት ላይ የተገነባ ነው።

- የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

- የቻይና መንግሥት 80 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት የግንባታውን ሙሉ ወጪ ሸፍኗል።

-  የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ 25 ወራትን  ፈጅቷል።

- ማዕከሉ የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን፣ የመረጃ፣ የላብራቶሪ፣ የስልጠና ፣ የኮንፈረንስ ማዕከል ፣ ቢሮዎች እና አፓርትመንቶች አሉት።

- የማዕከሉ ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ (አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ የማጠቃለያ ሥራዎች) እየተካሄደ ነው።

- ማዕከሉ በቅርቡ ሙሉ ስራው ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል።

- በግንባታው ላይ #ቻይናውያንና #ኢትዮጵያውያን የህንፃ ባለሞያዎች እየተሳተፉበት ነው።

Info : ENA
Photo Credit : Tesfaye Wube (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ? የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦ " ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት። ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም። ስርዓተ…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔውም በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ ተወያይቷል።

በዚህም ፤ ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የሕዝብ ( #የተማሪ_ወላጆችን_ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው ዕለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ  (ሁለተኛ) ቋንቋ እንዲሰጥ፤

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም የከተማው  ትምህርት ቤቶች የአገር ውስጥ ቋንቋ መማራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ፤

4ኛ:-  ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች #አረብኛና #ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፤

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን፤

6ኛ:-  በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የሥራ እና ቴክኒክ ትምህርት  በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ በሚያስቀምጠዉ መስረትና ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና  በተጠናው ጥናት  መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ፤

7ኛ:-  የግል ትምህርይ ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ  250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት፤ በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥምቀት ጎንደር ከተማ በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጓ አሳውቃለች። የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፤ በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አሳውቋል። በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል…
#GONDAR

የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው።

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል።

ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት በዓልን የጥበብ መፍለቂያና የፍቅር ከተማ በሆነችው በጎንደር  ኑ አብረን እናክብር " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ጎንደር የሃይማኖት፣ የፍቅር ፣ የጥበብ መፍለቂያ፣ የቱሪስት ምስእብ ፣ የኩሩ ህዝብ ባለቤት ከተማ ናት " ያለው አስተዳደሩ ፤ የጎንደር ህዝብ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪ ህዝብ ነው ፤ ኑ የጥምቀት በዓል በጋራ እናክብር ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ከነገ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ስራ ይጀመራል። የውል መዋዋያው " #መገናኛ " በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ነው። በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች #በአካል እየተገኙ ውል እንዲዋዋሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል። …
የ20/80 እና 40/60 ውል እንዴት እየሄደ ነው ?

" በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ " በጥሩ ሁኔታ " እየተካሄደ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፓሬሽኑ በ20/80 14ኛ ዙር  እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ  ከጥር  1/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

" ውል ከጀመረበት ቀን ጀምሮ 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን በሁለቱም የቤት ልማት ኘሮግራሞች መውሰድ ችለዋል " ብሏል።

ተቋሙ ፤ " ባለ እድለኞች እንዳይጉላሉ በቂ ቦታ እና የሰው ሃይል መድቤ በማስተናገድ ላይ ነኝ " ያለ ሲሆን ውሉ ከተጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 60 የስራ ቀናት ብቻ ይቆያል ሲል አስታውሷል።

@tikvahethiopia