TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.6K photos
1.39K videos
200 files
3.74K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል…
#Update

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑ 2.556 ቢሊዮን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ የ4 ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት ዛሬ አጽድቋል።

ይህ የ4 ዓመት ፓኬጅ፦
- የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን
- በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን
- የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን የሚደግፍ ነው ተብሏል።

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታት ተብሏል።

በተጨማሪ በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊዮን SDR ወይም 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ6 ሰዎችን ማግኘት አልተቻለም  "- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኪንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰዉን የመሬት መንሸራተት አደጋ በተመለከተ ክልሉ ዛሬ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫ " የቀበሌዉን ማህበረሰብ ቁጥር ለመለየት በተደረገ የቤት ለቤት ቆጠራ ስድስት ሰዎች አልተገኙም " ብሏል። አሁንም አስክሬን ፍለጋዉን እንደቀጠለ ጠቁሟል። በሌላ በኩል ፤ እስካሁን…
#Update

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።

በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል።
#DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን  ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው  ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ  ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት  ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ  ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።

የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ  በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን  መቷታል።

በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።

ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ  የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ  ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ  ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን  ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88024?single

#CentralEthiopiaRegionPolice  #WolkiteUniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ልጄን አድኑልኝ " - መምህርቷ እናት መምህርት አልሻምጌጥ ንጉስ ፤ ልጇ የአብቃል በተወለደ በሀያ አንድ ቀኑ ነው የልብ ህመም እንዳለበት ያወቀችው። ላለፉት 5 አመታት የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና መዕከል አስመዝባ ብጠብቅም ወረፋ ሊደርሳት አልቻለም። " አሁን ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስትል ገልጻለች። ከሀያ አንድ ቀኑ ጀምሮ ከሀዋሳ አዲስ አበባ እየተመላለሰች ሰርጀሪውን ስትጠብቅና ማስታገሻ…
#Update

" የተሰበሰበልንን 300 ሽህ ብር ከፍለን ወረፋ ብናስይዝም ገንዘቡ ሊሞላልን ባለመቻሉ ህክምናዉ ሊያልፈን ነው " -  ወላጆች

ከዚህ ቀደም በልብ ክፍተት ህመም እየተሰቃየ የሚገኘዉን ህጻን ህክምና በተመለከተ ለኢትዮጵያ ህዝብ የድጋፍ ጥሪ መድረሱን ተከትሎ አንዲት ልበ ቀና እህት 200 ሺህ ብር እንዲሁም ከህዝቡ በተሰበሰበ 100 ሽህ ብር በድምሩ 300 ሺህ ብር ተከፍሎ ወረፋ ተይዞለት ነበር።

ይሁንና አሁን ላይ ወረፋዉ ቢደርስም ቀሪዉ ገንዘብ መሰብሰብ ባለመቻሉ የህጻኑ ወላጆች በከባድ ጭንቀት ዉስጥ የወደቁ ሲሆን የህጻኑ ስቃይም ከጊዜዉ መሄድ ጋር ተባብሶ ቀጥሎ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።

" እባካችሁ የሆስፒታሉ ወረፋ ሳያልፈን ልጃችንም ሳያመልጠን ድረሱልን " የሚሉት የህጻኑ ወላጆች መምህርት ወ/ሮ አልሻምጌጥ ንጉሴ እና አቶ አንተነህ ደፈርሻ " አቅም ያላችሁ በገንዘባችሁ አቅም የሌላችሁ ደግሞ በጸሎት አግዙን " ብለዋል።

በልብ ክፍተት ችግር እየተሰቃዩ ያለዉንና በተያዘለት ቀጠሮ የልብ ክፍተቱ የማይስተካከል ከሆነ ለከፋ ችግር ይወድቃል የተባለዉን ህጻን ለመርዳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000243926053 አልሻምጌጥ ንጉሴ መኮንን መጠቀም እንደሚቻል መምህርቷ እናት ተናግረዋል።

በስልክ ቁጥር
0916155490 በመደወል ደግሞ አስገላጊ ማስረጃ እና ጥያቄ ቤተሰቡን መጠየቅ ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy “ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች…
#Update

" ለልማት ይፈለጋል ልቀቁ " በመባሉ የተማሪ ወላጆችን ያበሳጨው የአዲስ ግሎባል አካዳሚ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

አዲስ ግሎባል ትምህርት ቤት ያለበት ቦታ " ለልማት ይፈለጋል " በመባሉ የተማሪ ወላጆች ልጆቻችን የት እናስመዝግብ ? ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል መጠየቃቸው ይታወሳል።

ት/ቤቱ በበኩሉ፣ ባይሆን የአንድ አመት ጊዜ እንኳ እንዲሰጠው ነበር የጠየቀው።

ት/ቤቱ ምን አይነት ውሳኔ ላይ ደረሰ ?

ዛሬ ትምህርት ቤቱ አነጋግረን ነበር ፤ የትምህርት ቤቱ ዲን ት/ቤቱ በኪራይ ቤት ለማስተማር መገደዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በኪራይ በማስተማሩ ለይ ተስማምታችሁ ነው ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ የትምህርት ቤቱ ዲን ፤ " ምን እናድርግ ! በኪራይ እንድንሰራ መንግስትም ድጋፍ እንደሚያደርግልን ነግሮናል " ብለዋል።

" ልማቱ መቀጠል አለበት " ስለተባለ የመጨረሻው አማራጭ በኪራይ ቤት ተማሪዎቹን ማስተማር መሆኑን አስረድተዋል።

ስለዚህ ተማሪዎቹ አይበተኑም በኪራይ ቤቱ ለማመር ተስማምተዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ማስገደድ አንችልም። የሚፈልጉን ነባር ተማሪዎች አብረውን ይቀጥላሉ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ኪራይም ባይሆን በራሳቸው መንገድ የሚለቁ ይኖራሉ " ያለው ትምህርት ቤቱ፣ " ስለዚህ አዲስም የያዝናቸው አሉ። ነባር ተማሪዎችንና ወላጆቻችንን ይዘን እንቀጥላለን " ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በንግድ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሬ እንዴት ዋለ ? በባንኩ የውጭ ምንዛሬ በተለይ የዶላር ዋጋ ከትላንት ከሰዓቱ የተለየ አልነበረም። ዶላር ትላንትና ከሰዓት ሲገዛ እና ሲሸጥ በነበረበት ዛሬም በዛው ውሏል። አንድ ዶላር መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫው 81 ብር ከ6207 ሳንቲም ሆኖ ውሏል። ዩሮም ዛሬ ከትላንቱ ያን ያህል ልዩነት አልነበረውም። መግዣው 86 ብር ከ63 ሳንቲም መሸጫው 88 ብር…
#Update

ለነገ አርብ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጨምሯል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነገ አርብ ምንዛሬ ዋጋን ዛሬ ምሽት ይፋ አድርጓል።

በዚህም አንዱ የአሜሪካን ዶላር መግዣው 83 ብር ከ9413 ሳንቲም ፤ መሸጫው 85 ብር ከ6201 ሳንቲም እንዲሆን ቆርጧል።

ፓውንድ ስተርሊንግም በእጅጉ ጨምሯል። መግዣው 101 ብር ከ9101 ሳንቲም ፤ መሸጫው 103 ብር ከ9483 ሆኖ ይውላል ብሏል።

ዩሮም ጨምሯል። መግዣው 90 ብር ከ5307 ሳንቲም መሸጫው 92 ብር ከ3413 ሳንቲም እንደሚሆን አሳውቋል።

የUAE ድርሃም በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ ድርሃም ነገ በ20 ብር ከ4557 ሳንቲም እየተገዛ ፤ በ20 ብር ከ8648 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል።

#TikvahEthiopia #CBE #Floatingexchangerate

@tikvahethiopia
#Update

የጤና ሙያተኞች የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ተማሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰኔ 19/2016 ዓ.ም መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

በ17 የጤና ሙያዎች የተሰጠውን የምዘና ፈተና 15 ሺ የሚጠጉ ተመዛኞች መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

ከምዘናው ፈተናው እርማት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዚህ ሳምንት ተጠናቀው፤ ውጤቱ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና-ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#የደመወዝ_ጭማሪ " ታች ላለው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ መንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ምን ተባለ ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት…
#Update

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በቅርቡ እንደሚጸድቅ የገንዝብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

" ለታችኛው የደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛ የተሻለ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚያችል ጭማሪ ተሰርቷል " ብለዋል።

ዝርዝሩ በቅርብ ይጸድቃል ሲሉም አሳውቀዋል።

ከዓለም አቀፍ ተቋማት ከተገኘው ድጋፍ ውስጥም አንዱ የሚውለው ለሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ / በድጎማ መልኩ እንደሆነ አመልክተዋል።

ትላንትና በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ እንዳለው በመግለፅ ጭማሪ እንደሚደረግ ተናግረው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኑ የደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት እንደጠየቀና ፤ ከታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግሥት ሠራተኛ 300% ደመወዙ እንደሚጨመር በይፋ መናገራቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia