TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከሰሞኑን - ሰሜን ኢትዮጵያ ! ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ከኢፌድሪ መንግስት ፣ ከአሜሪካ መንግስት ፣ ከተመድ ፣ ከአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት የተሰጡ መግለጫዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች ፦ ➦ አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ ፤ በባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ " ህወሓት / TPLF " በአማራ ክልል በ " ቆቦ " አካባቢ ዘመቻ ማካሄዱንና በዚህም…
#Update

" በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል " - የኢትዮጵያ መንግስት

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

" ይህንን ሲያደርግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል " ብሏል።

በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ እንደሚግኝ አመልክቷል።

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ መሆኑንም አሳውቋል።

ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ መሆኑንም ገልጿል።

መንግስት አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል ብሏል።

" በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር አድርጎ ይወስደዋል " ሲል አክሏል።

" በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል " ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ። ውይይቱ ፤ በኢትዮጵያ እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ኬንያ ስላላት ወሳኝ ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። ሚኒስትሩ ፤ በታህሳስ ወር ለማካሄድ ከታቀደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዕቅዶች ዙሪያም ውይይት…
#Update

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።

ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ በፊት ህወሓት የሰላም ድርድር የሚያደርጉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል፤ የሰላም ንግግሩ ተካፋዮችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ማቅናታቸውን አመልክቷል።

ከወራት በፊት የፌዴራል መንግሥት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን አባላቱ አቶ ደመቀ መኮንን (ሰብሳቢ)፣  ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (አባል)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ (አባል) ፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር (አባል)፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (አባል) ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ (አባል)፣ ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር (አባል) መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#የመከላከያ_ሠራዊት_ቀን

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከለካያ ሚኒስቴር ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በየዓመቱ " ጥቅምት 15 " ቀን እንዲከበር ወስኗል። ቀኑ " የሠራዊት ቀን " ተብሎ እንዲሰየም ሚኒስቴሩ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶችን መቃኘቱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ የሠራዊት ቀን ሲከበር የመጀመሪያው ነውን ?

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ1950 ዓ.ም ግንቦት 20 የተካሄደው የስፖርት ውድድር በሠራዊታቸው ውስጥ የፈጠረው መነቃቃት አስደስቷቸው ዕለቱ የጦር ኃይሎች ቀን ሆኖ በየ 3 ዓመቱ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፈዋል።

ከ1966 ዓ/ም በኋላ የጦር ኃይሎች ቀን አንዴ ሲከበር አንዴ ሲቋረጥ ቆይቷል።

ከ1987 ዓ/ም ጀምሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት በአዋጅ የተቋቋመበትን ቀን ለማሰብ የካቲት 7 ቀን የሠራዊት ቀን ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።

ጥቅምት 15 ለምን ተመረጠ ?

ይኽ ቀን " የሠራዊት ቀን " ሆኖ ሲመረጥ የተለያዩ ታሪካዊ ኩነቶች ከግምት ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደ አንድ የሀገሪቱ ተቋም ሆኖ በሚኒስቴር መስሪያ ቤትነት ደረጃ የተቋቋመበት ጥቅምት 15 ቀን 1900 የሠራዊት ቀን እንዲሆን ውሰኔ ላይ ተደርሷል።

አጼ ምኒሊክ 1900 ካቋቋሟቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አንዱ የጦር ሚኒስቴር ሲሆን ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ በሚኒስትርነት ተሾመውም ነበር።

ንጉሱም ይህንን ዜና በይፋ ለዓለም ሀገራት ማሳወቃቸውን ተከትሎ በአሜሪካና በእንግሊዝ ጋዜጦች ጭምር ታትሞ ወጥቷል።

ዘንድሮ ቀኑ በፖናል ውይይት እንዲሁም በመጽሐፍ ምረቃ ብቻ የሚከበር ሲሆን በቀጣይ "ለማይታወቁ ጀግኖች" እንዲሁም ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የቀብር ሥፍራ ለማዘጋጀት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ተመረጡ። የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል። ትረስ እድሜያቸው 47 ሲሆን የቦሪስ ጆንሰን ተተኪ ሆነዋል። ሶስተኛዋ የሀገሪቱ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደሆኑ ተገልጿል። ትረስ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሪሺ ሱናክን ሲሆኑ ያሸነፉት 57.4% ድምፅ በማግኘት እንደሆነ ዶቼ ቨለ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#UK #China

ሪሺ ሱናክ የዩናይትድ ኪንግደም ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው።

ሊዝ ትረስ በተሾሙ በሰባት ሳምንት ስልጣን በቃኝ ያሉ ሲሆን እሳቸውን ለመተካት በተደረገው ውድድር ሪሺ ሱናክ አሸናፊ ሆነዋል።

ሱናክ ፤ የዩናይትድ ኪንግደም #የመጀመሪያው " እስያዊ " ዝርያ ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ።

ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ከሰባት ሳምንታት በፊት በተደረገ ፉክክር ሪሺ ሱናክ ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም በሊዝ ትረስ ሊሸነፉ ችለዋል።

ሊዝ ትረስ ' ግብር እቀንሳለሁ፤ ንግድን አሳልጣለሁ " ያሉት አዲስ ፖሊሲ ፍጹም ያልተጠበቀ የገበያ ምስቅልቅልና ብሔራዊ ጦስ ይዞባቸው መጥቶ ነው ሥልጣን እንዲለቁ የሆኑት።
 
ለ45 ቀናት ያህል ስልጣን ላይ የቆዩት ሊዝ ትረስ በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ ለአጭር ጊዜ የቆዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመዝግበዋል። 

በሌላ መረጃ ፥  የቻይና ገዥ የሆነው ኮሚኒስት ፓርቲ ትላንት ባደረገው ጉባኤ ዢ ዢንፒንግን ዋና ጸሓፊ አድርጎ መምረጡን ተከትሎ ለ3ኛ ጊዜ ስልጣናቸው ተራዝሟል።

የፓርቲው #ዋና_ጸሃፊ በሃገሪቱ የመሪነት ቦታ የሚያስገኝ ሲሆን መጋቢት በሚደረገው የብሄራዊ ህዝቦች ጉባኤ በይፋ ስልጣናቸው ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ተጀምሯል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ፤ የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ ጥቅምት 20 እንደሚዘልቅ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና ህወሓት መካከል የሚካሔደውን የሰላም ንግግር እንድታስተናግድ በመመረጧ ክብር ተሰምቷቸዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን እንድታስተናግድ ስትጋበዝ " ያለ ማቅማማት ተስማምተዋል " ያሉት ቃል አቀባዩ ፤ እንዲህ አይነት ንግግር አፍሪካ " ደህንነቷ የተረጋገጠ እና ግጭት የሌለበት አህጉር " እንድትሆን ከሚሻው የአገራቸው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዓላማ ጋር የተስማማ እንደሆነ ገልጸዋል።

አውዳሚው የትግራይ ግጭት ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ የተጀመረው የሰላም ንግግር በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አመቻችነት የሚካሄድ ነው።

በሰላም ንግግሩ ላይ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፑምዚ ለምላምቦ በደጋፊነት ይካፈላሉ።

" ደቡብ አፍሪካ ለአመቻቺው ቡድን መልካሙን ትመኛለች " ያሉት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቃባይ፤ የሰላም ንግግሩ " የእህት አገር ኢትዮጵያ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ዘላቂ ሰላም የሚመራ ስኬታማ ውጤት " ያመጣል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል። ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል። ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ…
#Update

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ፤ " ፈተና አንፈተንም " ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ  እንደማይችሉ አረጋግጠዋል፡፡

በግል መፈተን እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ያልተፈተኑና በተለያዩ #አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ፣ የወለዱ ተማሪዎች #ከአንድ_ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

የፈተና ዉጤት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ እንደሚገለፅ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Jigjiga

ዛሬ ከሰዓት በጅግጅጋ ፤ " ጋራድ ዊልዋል  ኤርፖርት " በተከፈተ ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 3 ሰዎች መቁሰላቸውን ለመስማት ችለናል።

የኤርፖርቱ የፀጥታ ኃይል አባል የሆነው ግለሰብ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ፓርላማ አባል ጁዋሪያ ሱብዕስ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል።

በኤርፖርቱ በተከፈተ ተኩስ ሰለባ የሆኑት ተጓዦች እንደሆኑ ተመላክቷል።

የነበረው ሁኔታ ላይ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀም ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

በጁዌሪያ ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው የሶማሊ ክልል ፖሊስ አመልክቷል።

የድርጊቱ ተሳታፊ የሆነው የፀጥታ ኃይል አባል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከተደረገ በኃላ በኤርፖርቱ የነበረው እንቅስቃሴ ወደ መደበኛነት የተመለሰ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ተጀምሯል። የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ፤ የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ ጥቅምት 20 እንደሚዘልቅ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት እና ህወሓት መካከል የሚካሔደውን የሰላም ንግግር እንድታስተናግድ በመመረጧ ክብር…
#AU

የ " ኢትዮጵያ መንግስት " እና የ " ህወሓት " ን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል።

- በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

- ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለሆነች ለሀገሪቱ መንግስት እና ለፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ምስጋና አቅርበዋል።

- ሙሳ ፋኪ ማሀመት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ ሁኔታ ሰላምን ለማስፈን እና ለግጭቱ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ለማስረግ ባሳዩት ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደተበረታቱ ገልፀዋል።

- የአፍሪካ ህብረት " የሰላም ንግግር " ተሳታፊ ወገኖች ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላም እንዲሰፍን ፣ የተረጋጋችና አንድነቷ የተጠበቀ እንድትሆን ህብረቱ ድጋፉን እንደሚቀጥል ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል።

" ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ ነው " ያለው ፓርቲው " በቀጣይ ሁኔታው የደረሰበት ደረጃ በሚመለከተው አካል ይገለፃል " ብሏል።

ፓርቲው በማእከላዊ ኮሚቴ አባሉ ላይ በደረሰው ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል። " ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ…
#Update

" በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል መንግስት ጅግጅጋ " ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት " የተከሰተውን ድርጊትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ላይ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ በጥበቃ ላይ የነበረ " የፌደራል ፖሊስ " አባል በከፈተው ተኩስ የ1 ሰው ህይወት ማለፉንና በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አሳውቋል።

" አባሉ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ም/ቤት አባልና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም #ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች 4 ዜጎች በህክምና ተቋማት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል " ሲል ክልሉ አመልክቷል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ #በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከድረጊቱ በኋላ በኤርፖርት የተፈጠረውን ክስተት ወዳያኑ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ኤርፖርቱ ወደ መደበኛው ስራ ተመልሷል ሲል ክልሉ በመግለጫው አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ #የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ እንደምትግኘ የገለፀው የሶማሌ ክልል መንግስት " ጉዳዩ ተመርምሮ ወደፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል " ብሏል።

@tikvahethiopia