TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* ጥቆማ

STEMpower እና Visa ከTikvah-Ethiopia ጋር በመሆን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ባለፉት 5 ዙሮች ወደ 900 የሚጠጉ ሰልጣኞች መሳተፍ ችለዋል።

6ተኛ ዙር ደግሞ ተጨማሪ 300 ሰልጣኞችን ለማሳተፍ ዝግጅት ተደርጓል። እርስዎም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተመዝግበው የስልጠና እድሉን መጠቀም ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያካትተው፦

* የ6 ቀን መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና

* በተጨማሪ የ3 ወር የንግድ ማማከር እና ድጋፍ

* 9 ወር የማማከር ድጋፎች፣ የኔትዎርኪንግ እና የተለያዩ ክትትሎች በተጨማሪም ቢዝነ  ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉበተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላች እስከ  ጥቅምት 24 2015 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/pmZGkvcPtG

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ?

- "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል።

- #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን ተፈታኞች ይዘው እንዳይመጡ መልዕክት ቢተላለፍም በ33 የፈተና ጣቢያዎች 59 ተፈታኞች #ስልክ_ይዘው ገብተው ለመጠቀም ሙከራ አድርገው ተይዘዋል።
👉 ጫት፣
👉 አደንዛዥ ዕፅ፣
👉 ሲጋራ፣
👉 ስለታማ ነገሮች፣
👉 ጥይት፣
👉 አልኮል ..... ወዘተ ተፈታኞች ይዘው በመምጣት በተለያየ መልክ ለማስገባትና በአንዳንድ ቦታዎችም ለመጠቀም ሙከራ አድርገዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ " ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ግቢ " የሚወስደው ድልድይ በመደርመሱ ምክንያት 451 ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል ፤ 1 ተማሪ ህይወቱ ሲያልፍ 232 ተማሪዎች ቀላል የአካል ጉዳት ፣ 201 ተማሪዎች መካከለኛ ጉዳት ፣ 13 ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ፣ 5 ተማሪዎች በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ሁከት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ 5 የፀጥታ ኃይሎች እና 2 ፈተና አስፈፃሚዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- " በሶስት ዩኒቨርሲቲዎች " ቀደም ሲል በነበር የጤና እክል ምክንያት 3 ተማሪዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በጉዞ ወቅት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ የተወሰኑ ተማሪዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ፈተና መውሰድ ያልቻሉና በከፊል የተፈተኑ በአንድ ወር ጊዜ የሚዘጋጀውን ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል። ተፈታኞቹ የጤና ሁኔታቸው ለፈተናው የማያበቃቸው ካሉ ከ2015 ዓ/ም ተፈታኞች ጋር በመደበኛነት እንዳፈተኑ ይደረጋል።

- " ፈተና አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ዳግም በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እንድል አይሰጣቸውም፤ በግል በ2015 ዓ.ም የመፈተን መብታቸው የተጠበቀ ነው።

በ " ማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ፈተና ሳይፈተኑ የወጡ ተማሪዎች ፦

👉 ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ መካነ ሰላም ካምፓስ (1,700 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (1,226 ተማሪዎች)
👉 ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (2,711 ተማሪዎች)
👉 ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (7,356 ተማሪዎች) በድምሩ 12,993 ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተና ሳይጀምሩና የአንድ ቀን ሁለት ፈተና ከወሰዱ እንዲሁም የሁለት ቀን 4 ፈተናዎች ከወሰዱ በኃላ " አንፈተንም " ብለው ጥለው የወጡ ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች ከዚህ በኃላ በ " መደበኛ ተማሪነት " መፈተን #የማይችሉ ሲሆን በ2015 በግል መፈተን ይችላሉ።

- በታወቁ የጤናና ሌሎችም እክሎች ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ።

- " የፈተናው ዉጤት " በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ ይፋ ይደረጋል።

@tikvahethiopia
ስለ ስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ ይወቁ ! ጤናማ ልጅ ይውለዱ !

ከ " እርግዝና በፊት " እንዲሁም ከ " እርግዝና በኋላ " ፎሊክ አሲድን በመውሰድ የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውሃ መከማቸትን ይከላከሉ !

በዓለማችን በዓመት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናት የዚህ በሽታ ተጠቂ ይሆናሉ፡፡

በአፍሪካ ይህ በሽታ በብዛት ከሚከሰትባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች።

ስፓይና ቢፌዳ ማለት ደግሞ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ወይም የህብለሰረሰር በትክክል አለማደግ ሲሆን የሚከሰተውም የመጀመሪያዎቹ አራት የእርግዝና ሳምንታት ውስጥ ነው፡፡ ይህ የጤና ችግር ያለባቸው ህፃናት ሽንት እና ሰገራ ለመቆጣጠር ችግር እና ለተለያዩ የአካል ጉዳቶች ይጋለጣሉ፡፡

ምልክቶቹም የውጭኛው የጀርባ ክፍል ላይ የሚታይ እብጠት ወይንም ፀጉር መሰል ምልክት መታየት ነው፡፡

ይህ የጤና ችግር ያለባቸው ህፃናት የቀዶ ጥገና ህክምና የሚደረግላቸው ሲሆን ይህም የነርቭ ህዋሳቶችን የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለማድረግ የሚረዳ ይሆናል፡፡

የነርቭ ዘንግ ማለት ከጀርባችን ከመሃል በመጀመር የላይኛውን ቀጥሎም የታችኛውን ከ21ኛው 28ኛው ቀን ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ መዝጋት ያለበት የራስ ቅል እና የህብለ ሠረሰር ዘንግ ክፍተት ነው፡፡

ሃይድሮሴፋለስ ማለት ጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ መጨመር ሲሆን በእርግዝና ወቅት ወይም ልጆች ከተወለዱ በኋላ በኢንፌክሽን ሊፈጠር ይችላል፡፡

የሃይድሮሴፋለስ ምልክት የጭንቅላት መጠን በፍጥነት መጨመር ወይም ማበጥ ነው፡፡ ሀይድሮሴፋለስ በቀዶ ህክምና የሚረዳ ሲሆን ከመጠን በላይ የተከማቸው ፈሳሽ እንዲወገድ መንገድ መፍጠር ነው፡፡

https://telegra.ph/IF-SBH--HOPE-SBH-10-27

@tikvahethiopia
መሐመድ ጄሌ ጃራሶው ተያዘ።

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር የ " አልሸባብ " ከፍተኛ አመራር የሆነውን መሐመድ ጄሌ ጃራሶውን በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ገልጿል።

ጦሩ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራርን የያዘው / በቁጥጥር ስር ያዋለው ዛሬ ሀሙስ በመካከለኛው ሸበሌ ክልል ዋር-ኢሴ መንደር አቅራቢያ ባደረገው ኦፕሬሽን ነው ተብሏል።

ሞሃመድ ጄሌ ፤ በጆውሃር እና በራጌኤሌ ከተሞች የአልሸባብ የገንዘብ ዘረፋ ማዕከላትን በኃላፊነት ሲመራ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ በትላንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ ምን አሉ ? - "የፈተና ዝግጅት እና ህትመት" ከቀድሞው እንዲለይ በኮድ ብዛት እና በገፅ አወቃቀር በመለየት በሁለቱም የትምህርት መስኮች " 12 ኮድ " እንዲኖር እና የመለያ ኮዱ ከሚታወቅበት 2 ኮድ ወደ 3 ተቀይሮ ፈተናው ተሰጥቷል። - #ስልክ እና ማንኛውም #ኤሌክትሮኒክ_መሳሪዎችን…
" ተመጣጣኝ ቅጣት በማሳለፍ ድጋሚ ሊፈተኑ የሚችሉበት እድል ይመቻችላቸው " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ላለፋት አስርት ዓመታት ይስተዋል የነበረውንና እንደነውር ሳይሆን እንደባህል ጭምር እየተቆጠረ የመጣውን የፈተና ሥርቆትና ማጭበርበር ለማስቀረት ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች እንዲፈተኑ በማድረግ በትምህርት ጥራት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሄደበትን ርቀትና ጥረት በበጎ ጅምር በአድናቆት እንደሚመለከተው ገልጿል።

በዚሁ ሂደት ላይ ግን በአማራ ክልል 12,000 ገደማ ተማሪዎች "ፈተና ተሰርቋልና አንፈተንም" በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች በወቅቱ ይሰጥ የነበረውን ፈተና ሳይወስዱ ቀርተዋል ሲል በመግለጫው አመልክቷል።

" ትምህርት ሚኒስቴር ጥቅምት 15 በሰጠው መግለጫ ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎችን ድጋሚ እንደማይፈትን አሳውቋል " ያለው እናት ፓርቲ ፤ " ምንም እንኳን ፈተናውን ላለመውሰዳቸው የተማሪዎቹ #ጥፋትና #ሓላፊነቱንም ራሳቸው የሚወስዱ ቢሆንም ምን አልባት ክልሉ በአጠቃላይ ከቆየበት ሁኔታ፣ ልጆቹ ያሉበት እድሜ እና መሰል ውዥንብሮች ተጽዕኖ አድርገውባቸው በመሆኑና በጥቂቶች ጥፋት አብዛኞቹ ሰላባ በመሆናቸው የተፈጠረ ችግር ነው ብለን እናምናለን " ብሏል።

ፓርቲው፤ ሚኒስቴሩ በአንድ በኩል ለወጥ የሄደበትን ርቀት የሚያጠለሽበት በመሆኑ በሌላ በኩል እልህ መጋባቱ ከመንግስት ጠባይ የሚጠበቅ ባለመሆኑን የልጆቹን የዓመታት ድካም፣  የወላጅ ጥሪት አሟጦ ማስተማርና የሀገር ሀብት ብክነት ጭምር ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ለዘላለም ከመንገዳቸው ከማሰናከል ይልቅ በቀጣይ የፈተና ጊዜያትና ዓመታት ለሚፈተኑ ተማሪዎች ጭምር ጥብቅ መልዕክት በሚያስተላልፍ መልኩ ተመጣጣኝ ቅጣት በማሳለፍ ድጋሚ ሊፈተኑ የሚችሉበትን እድል እንዲያመቻችላቸው ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ " የፌስቡክ ገጹ " (ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው) ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ፤ ደንበኞች እንዲሁም የገጹ ተከታታዮች በፌስቡክ ገጹ የሚተላለፉ ማንኛውም መልዕክቶች የአየር መንገዱ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

ችግሩን ለመፍታት በአሁኑ ሰዓት ከሜታ ኩባንያ ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Jigjiga

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ጁዌሪያ መሀመድን የገደለው ግለሰብ በህግ ይጠየቃል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ብልፅግና ፓርቲ ገለፁ።

ጄዌሪያ መሀመድን ተኮሶ በጥይት የገደለው የኤርፖርት የጥበቃ አባል የሆነው ግለሰብ (የፌዴራል ፖሊስ) ለፈፀመው ድርጊት " በህግ እንደሚጠየቅ እናረጋግጣለን " ብለዋል ሁለቱ አካላት።

ይህንን ያሉት የጁዌሪያ መሀመድን ቤተሰብ ሐዘንን ለመከፈል በምክር ቤት አባሏ ቤተሰቦች ቤት በተገኙበት ወቅት ነው።

በወቅቱ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፓርቲው ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣ የፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንተና እንዲሁም የክልሉ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማንና ከሌሎችም ተገኝተው ነበር።

የስራ ኃላፊቹ ለሟች ቤተሰቦች በልጃቸው ላይ የተፈጸመውን " አስነዋሪ ግድያ " መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱን በፅኑ እንደሚያወግዙ ገልፀዋል፤ ድርጊቱን የፈጸመውን ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ ነግረዋቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ጉዳት የደረሰባቸው እና የቆሰሉ ሌሎች ዜጎች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ  የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ወደ አዲስ አበባ ሸኝተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU የ " ኢትዮጵያ መንግስት " እና የ " ህወሓት " ን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫው ምን አሉ ? - የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል። - በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)…
#PeaceTalks

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።

የሰላም ንግግሩ እስከ እሁድ እንደሚቀጥል ነው የሚጠበቀው።

የደቡብ አፍሪካ/ፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ አመቻችነት ነው እየተመራ የሚገኘው።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN)፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ደግሞ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ለስራ ጉብኝት ወደ ካናዳ (ኦታዋ) በሄዱበት ወቅት በዛው ከነበሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ውይይት እንዳካሄዱ ገልፀዋል።

ፋኪ በውይይቱ ፤ ለአፍሪካ ሰላም የፖለቲካ ሂደትን በተመለከተ እንዲሁም በታህሳስ ወር ለሚካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል።

የደ/አፍሪካው ሰላም ንግግርም "ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሊቀመንበሩ (ሙሳ ፋኪ መሀመት) እና የአፍሪካ ህብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን #ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ፎቶ ፦ ሮይተርስ/AU

@tikvahethiopia
#DrAbrhamBelay

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፤ በትግራይ ያጋጠመውን ቀውስ አይነተኛ የመፍቻ መንገድ፣ " ህዝቡ በተደራጀ አዲስ የሀሳብ ጥላ የመፍትሔው ባለቤት እና አካል ለመሆን ሲወስን #ብቻ የሚረጋገጥ ነው " አሉ።

የመከላከያው ሚኒስትር ይህንን ያሉት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ነው።

" ጊዜው ያለፈበት የፖለቲካ ኃይልም ሆነ አስተሳስብ፣ ከትግራይ ህዝብ ኑባሬ ደህንነት፣ ሰላምና መረጋጋት ከቶ ሊበልጥ አይገባም " ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ፤ " በመላው ትግራይ እና የተለያዩ አከባቢዎች የምትገኙ የትግራይ ተወላጆች የመፍትሔ ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ ፣ የተደራጀ #አስቸኳይ ህዝባዊ ስክነትና ምክክር እንዲሰፍን እንድንዘጋጅ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia