TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

10 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል !

የመመረቂያ ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን  ተማሪ በጥይትና በስለት ለመግደል የሞከረው  ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጥቷል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመመረቂያ  ጽሁፍ በማቅረብ ላይ የነበረችን ተማሪን ከጀርባዋ ሆኖ በጥይት ተኩሶ በመምታትና በስለት  ደጋግሞ በመዉጋት ለመግደል የሞከረ  ተከሳሽ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ፖሊስ ገለፀ።

ተከሳሽ ፦ አማኑኤል እንድርያስ
ነዋሪነቱ ፦ በጉራጌ ዞን አብሽጌ ወረዳ ቁሊት ሁለት ቀበሌ
የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው ፦ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ
የክሱ ዝርዝር ፦ ግለሰቡ የግል ተበዳይን ለመግደል በማሰብ ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የጦር መሳሪያና ስለት ይዞ ይገባል።

የመመረቂያ ምርምር ጥናታዊ ፅሁፍ በምታቀርብበት ክፍል ውስጥ ከጀርባዋ ሆኖ  በመቀመጥ በያዘው ሽጉጥ ተኩሶ ትከሻዋን  መቷታል።

በኋላም ደንግጣ ለመሮጥ ስትሞክር ተከታትሎ ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ስለታም ቢላዋ ጭንቅላቷን 6 ጊዜ ያህል ደጋግሞ በመዉጋት የመግደል ሙከራ ወንጀል በመፈጸሙ ነው የተከሰሰው።

ተከሳሹ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነው። ከዚህ በፊት ተጎጂዋ እና የግል ተበዳይን በመደብደቡ በዲሲፕሊን ተከሶ በዩንቨርስቲዉ አመራሮች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታዉ እንዲታገድ በመወሰኑ ወንጀሉን በዚህ ቂም ተነሳስቶ እንደፈፀመ የተከሳሹ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የጉራጌ ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ  የጦር መሳርያና ጥይቶችን የመያዝ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው በተከለከለ ስፍራ የጦር መሳሪያ  ይዞ በመገኘቱ እና በፈፀመዉ የመግደል ሙከራ ወንጀል የቀረበበትን ክስ  ማስተባበል ባለመቻሉ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በጥይትና በስለት ጉዳት የደረሰባት የግል ተበዳይ ህክምና ተከታትላ አሁን  ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

ለማስታወሻ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/88024?single

#CentralEthiopiaRegionPolice  #WolkiteUniversity

@tikvahethiopia