TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Assosa

ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia