TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.1K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sport ተጋጣሚውን 9 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ክለብ ! ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው በ #CECAFA ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያው ንግድ ባንክ ቡድን ተጋጣሚውን ዋሪየርስ ኩዊን በሰፊ የግብ ልዩነት 9 ለ 0 አሸንፏል። መዲና አዎል 4 ግቦችን እንዲሁም ሎዛ አበራ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ። More : @tikvahethsport
#TikvahSport | በተጋጣሚዎቻቸው ላይ የጎል ናዳ ያወረዱት 2ቱ ኢትዮጵያውያን !

በታንዛንያ ሀገር ፤ ዳሬሰላም ከተማ የ #CECAFA የሴቶች ሻሚዮንስ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ በመሳተፍ ላይ ሲሆን የዚሁ ክለብ ተጫዋቾች የሆኑት ሎዛ አበራ እና መዲና አዎል በታጋጣሚ ቡድኖች ላይ የጎል ናዳ አውርደውባቸዋል።

እስከሁን ባለው ከ3 ክለቦች ጋር በተደረገ ጨዋታ ሎዛ አበራ 9 ጎሎችን እንዲሁም መዲና አዎል 6 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

የጎል ናዳው የወረደው በየትኞቹ ክለቦች ላይ ነው ?

👉 ዋሪየርስ ኩዊን በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ሎዛ ብቻዋን 5 ጎል ፤ መዲና 4 ጎል አስቆጥረውባቸዋል።

👉 ፎፊላ በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ደግሞ ሎዛ 3 ጎሎችን መዲና 1 ጎል አስቆጥረዋል።

👉 ኤፒ አር ኪጋሊ በሚባለው ክለብ ላይ ሎዛም መዲናም አንድ አንድ ጎል አስቆጥረዋል (ይሄ ጨዋታ ዛሬ የተካሄደ ነው)

በድምሩ ሁለቱ ተጫዋቾች ብቻ በውድድሩ 15 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://t.me/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

በ2015 የትምህርት ዘመን ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና (ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ) ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ላይ ምላሽ አለኝ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) ከተናገሩት ፦

" አቻ ምሳሌ ላይሆን ይችላል ግን አንድ ምሳሌ ላንሳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሉ ከሺህ በላይ የሚሆኑ በሁሉም ት/ቤቶች ያለው አቅም ፣ የመምህራን፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰረተ ልማት አቅም እና መምህራኑ የተመዘኑ / ምዘናውን ያለፉ መሆን አለመሆናቸው ያለው ምጣኔ በጣም የተለያየ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ወጥ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ያስፈልገናል እንደ ሀገር።

የ2ኛ ደረጃ ፈተና የምንሰጠው አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ትምህርት በእርግጥ አጠናቋል ለሁለተኛ ደረጃ አጠናቃቂ ነው ተብሎ በቅቷል ወይ ለማለትና ለመለካት ነው።

ይሄ ፈተና ስታንዳርድ ፈተና ነው። በየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም አይደለም የሚዘጋጀው ፣ በሁለተኛ ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ብቻ አይደለም ታሳቢ የሚያደርገው፤ እንደ ሀገር ሁለተኛን ደረጀን የጨረሰ ሰው ምን አይነት እውቀት እና ስብዕና ሊኖረው ይገባል የሚለውን የሚፈትሽ ነው።

መምህራኑ ሁሉም ተፈትነው ብቁ ሆነው እስኪያልፉ ፣ ያለን መሰረተ ልማት በትምህርት ቤቶች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለን አቅም ተመጣጣኝ እስክናደርግ ድረስ አንድን ሪፎርም አንጀምርም ካልን ዝንተዓለም ያንን ሪፎርም አናደርግም።

ሪፎርሙ መጀመር አለበት የሆነ ጊዜ ላይ መጀመር አለበት የተባሉ ጉድለቶች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እንደ ትምህርት ሴክተርም እንደትምህርት ሚኒስቴርም እንገነዘበዋለን።

የመምህራኖቻችንን ብቃት ለማሳደግ በየአመቱ ከልማት አጋሮችም ፣ ከመንግስትም ግምጃ በሚሊዮኖች እያፈሰስን መምህራን በ2ኛ ፣ 3ኛ ዲግሪ እናስተምራለን።

እንደሚታወቀው መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሀገራችን 4ኛው ትልቁ በጀት የሚመደብለት ሴክተር ነው ሰፊውን የሚወስደው የከፍተኛ ትምህርት ነው የውስጥ መሰረተ ልማታቸውን፣ አደረጃጀታቸውን ለማሳደግ የሚውል ሀብት አለ እነዚህ ቁርጠኝነቶች በመንግስት በኩል የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል ነው።

መምህራኖቻችን በቀጣይነት እያበቃን መሄድ አለብን እርግጥ ነው እንደዛም ሆኖ ግን ይሄ ስራ መጀመር አለበት ፤ አሁን ካልጀመርነው ከበቂ በላይ ጉዳት ደርሷል የትምህርት ጥራቱ ላይ።

በፈተና ብቻ አይደለም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ በትኩረት በመለየት ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና በጥራት በመስጠት ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን አነስተኛውን መስፈርት በፖሊሲው መሰረት 50 ፐርሰንት በማድረግ እነኚህ ሪፎርሞች መምህራን ልማት ላይ የምንሰራውን ፤ የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያን ገድበን የወሰድናቸውን ሪፎርሞች ድምር ውጤት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው ፤ ይሄንን ማድረግ ተገቢ ነው ጊዜው አሁን ነው ብለን ነው የገባንበት። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እንኳን አደረሳችሁ !

ለኦርቶዶክስ እና ለካቶሊክ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቅድስት ድንግል ማርያም ትንሳኤ እና ዕርገት / ጾመ ፍልሰታ ፍቺ አደረሳችሁ።

@tikvahethiopia
#በወንጀል_ይፈለጋሉ #Wanted

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተጠርጣሪዎች በወንጀል እየፈለጋቸው ይገኛል።

የተጠርጣሪዎቹን አድራሻቸውን የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገለሰብ በስልክ ቁጥር ፦

👉 0115309139 ዘውትር (በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30)

👉 በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።

ነፃ የስልክ መስመር 861 መጠቀምም ይቻላል።

ግለሰቦቹ በሞጆ፣ አንድ ወርቅ ቤት በመግባት ሲዘርፉ የሚታይ ሲሆን ከመካከላቸው የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሰ ይገኝበታል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወደ ወርቅ ቤቱ በመግባት በሰዓቱ ስራ ላይ የነበረችውን ግለሰብ በማዘናጋት ብዛት ያለው ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዘርፈው ሲወጡ በቤቱ የደህንነት ካሜራ አይን ውስጥ ገብተዋል።

@tikvahethiopia
#Gambella

በጎርፍ አደጋ ወገኖቻችን ተፈናቀሉ።

በጋምቤላ ክልል በ4 ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከአራት ሺህ በላይ አባዎራና እማዎራ ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።

ከክልሉ አደጋ ስጋት አመራር በተገኘው መረጃ በሃገራችን ደጋማዉ አካባቢ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በላሬ፣ በመኮይ በዋንቱዋና በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷታ።

የጎርፍ መጥለቅለቅ ከደረሰባቸዉ 4 ወረዳዎች ዉስጥ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ አባዎራና እማዎራ ከመኖሪያ ቀያቸዉ የተፈናቀሉ ሲሆን ለጊዜዉ ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።

የደረሰው ጉዳት ዝርዝር ፦
- በኢታንግ ልዩ ወረዳ 2040 አባወራና እማወራ፣
- በላሬ ወረዳ 1000፣
- በዋንቱዋ ወረዳ 619፣
- በመኮይ 480 አባወራና እማወራ የተፈቀሉ ሲሆን በጂካዎ ወረዳም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋዉ በቤት ዉስጥ ያሉ ቁሳቁሶች እንዲሁም በቁም እንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷሳ።

በጎርፍ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከክልሉ መንግስትና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በመነጋገር አፋጣኝ ድጋፍ የሚደርስበት ሁኔታ ይመቻቻል ሲል የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አስታውቋል።

መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
በወይንሸት ካምፕ ምን ተፈጠሮ ነበር ?

በደብረ ብርሃን ከተማ ወይንሸት ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃይ በተደረገ የምገባ ፕሮግራም ችግር ተከስቶ እንደነበር እና ችግሩን መቆጣጠች መቻሉ ተገልጿል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በቀለ ገብሬ ነሀሴ 15 ቀን 2014ዓ.ም በወይንሸት መጠለያ ካምፕ ውስጥ ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ ለ3 መቶ ተፈናቃዮች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም መካሄዱን ገልጸው ከተመገቡት ውስጥ 1 መቶ 17ቱ መታመማቸውን አስረድተዋል፡፡

ችግሩ እንደተከሰተ የከተማው አመራሮች፣ የጸጥታ መዋቅር አካላትና የጤና ባለሙያዎች ባደረጉት ርብርብ የታመሙትን ወገኖች በፍጥነት ደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ፣ 04 ጤና ጣቢያ ፣ አየር ጤና፣ እና ጠባሴ ጤና ጣቢያዎች በመውሰድ እንዲታከሙ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ታመው ከነበሩት ውስጥ 116ቱ ወደ መጠለያ ጣቢያቸው መመለሳቸውን አረጋግጠው ፤ አንድ ሰው ግን አሁንም ህክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከምግቡ ጋር ተያይዞ ለተፈጠረው ችግር  መንስዔው ምን እንደሆነ ለማወቅ ለደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስታል ናሙናው ተሰጥቶ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የናመናው ምርመራ  ውጤቱ እንደደረሰም ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቀዋል፡፡

የችግሩን መንስዔ ውጤት እንደደረሰ ትክክለኛው መረጃ ይፋ እስከሚደረግ ድረስ ህብረተሰቡ  በትዕግስት እንዲጠባበቅ የጤና መምሪያ ኃላፊው ማሳሰባቸውን የከተማው አስተዳደር በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስፍሯል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የአሸንዳ፣ ሻደይ፤ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት !

በሰሜን የሀገራችን ክፍል ላይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል የአሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ እና ሶለል በዓላት ይጠቀሳሉ።

በዓላቱ በተለይ በሴቶች ዘንድ በእጅጉ በድምቀት ነው የሚከበሩት።

እነዚህ በዓላት ከባለፈው ዓመት በፊት በዓለም አቀፉ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ስጋት በአደባባይ ሳይከበሩ ቀርተዋል ፤ ባለፈው ዓመት ደግሞ በጦርነት ሳቢያ ተቀዛቅዘው ተከብረዋል።

ዘንድሮ በአማራ ክልል የሻደይ ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት ከአምናው በተሻለ ሁኔታ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በትግራይ ክልል የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ግን ዘንድሮም እንደቀደሙት ዓመታት በድምቀት ከሌላ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከዓለም ሀገራት ጎብኝዎች ተሰባስበው ሊያከብሩት አልተቻለም።

የጦርነቱ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ባለመፈታቱ ወደ ክልሉ የሚደረግ ምንም እንቅስቃሴ የለም፣ የስልክ ሆነ ኢንተርኔት ግንኙነት ባለመኖሩ ነዋሪዎች ከዘመድ አዝማዶቻቸው ጋር እንኳን አደረሳችሁ መባባል እና ባህላቸውን ለሌሎች ለማስተዋወቅ አልተቻላቸውም።

የአሸንዳ ፣ አሸንድዬ ፣ ሻደይ በዓላት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ገጽታ ያላቸው ሲሆን ከማህበራዊ እሴታቸው በተጨማሪ በየዓመቱ የሚፈጥሩት የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እያየለ መጥቶ ነበር።

በተለይ በዓላቱ ሚከበሩባቸው አካባቢዎች ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እጅግ ከፍተኛ ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ጦርነት ተዳምሮ ባለፉት 2 ዓመታት አጠቃላይ የቱሪስት እንቅስቃሴውን አዳክሞታል።

በሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ወርዶ በዓላቱ ዳግም በድምቀት የሚከበሩበት ጊዜ ይመጣ ዘንድ ምኞታችን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የአሸንዳ፣ ሻደይ፤ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት ! በሰሜን የሀገራችን ክፍል ላይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል የአሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ እና ሶለል በዓላት ይጠቀሳሉ። በዓላቱ በተለይ በሴቶች ዘንድ በእጅጉ በድምቀት ነው የሚከበሩት። እነዚህ በዓላት ከባለፈው ዓመት በፊት በዓለም አቀፉ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ስጋት በአደባባይ ሳይከበሩ ቀርተዋል ፤ ባለፈው…
ስለ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል ምን ያህል አውቃለሁ ?

የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።

በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።

በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።

ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።

በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።

በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።

ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።

(ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው)

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#አሸንዳ

በአሸንዳ በዓል ዙሪያ የተደረገ ጥናት!

(መብራህተን ገ/ማሪያም)

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ፍቅር፣ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ነው።

በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል፤ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው።

የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ጭፈራዎችና ትእይንቶችም እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በአሸንዳ በዓል ላይ የሚነገሩ ስነ ቃሎች ይዘት በአብዛኛው ህብረትን የሚሰብኩ፣መድልዎን የሚጠየፉና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ ናቸው።

ልጃገረዶች በዓሉን በህብረሰቡ ውስጥ ያለውን እርስ በርስ የመተባበር፣የመረዳዳትና የጀግንነት መልካም እሴቶችን አጉልተው ለማሳየት ይጠቀሙበታል።

በዓሉ ሴቶች ያላቸውን የፈጠራ፣ የመደራደር፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት በተግባር የሚያሳዩበትና መልካም ስሜታቸውን የሚገልጹበትም ነው።

በተጨማሪ በህዝቡ ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች በስነ ቃልና በዘፈን መልክ እንዲስተካከሉ የሚነቅፉበት፣ማህበረሰቡ መድልዎን እንዲጠየፍ፣የሴቶችን መብት የሚጋፋ የአስተዳደር መዋቅር አሊያም ወንድ ካለ እንዲስተካከል መልዕክት የሚያስተላልፉበት ጭምር ነው።

አሸንዳ በዓል ለትግራይ ህዝብ ባህል የመሰረት ድንጋይ ተደርጎ ይወሰዳል፤ በዓሉ ማንነትን አጉልተው የሚያሳዩ እሴቶች አሉት።

አሸንዳ ለሴቶች መብት አጥብቆ የሚታገል፣ መከባበርንና መረዳዳትን አብዝቶ የሚሰብክ፣ ሰዎች ባላቸው የሃብት መጠን ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ ክብር እደሚገባቸው በስነ ቃልና በዘፈን መልክ መልዕክት ይተላለፍበታል።

#Repost2013

@tikvahethiopia