TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ክረምት በመጣ ቁጥር በሌላም ጊዜ በተመቻቸ መንገድ እጦት ምክንያት የሚሰቃዩ፣ ስራቸው የሚስተጓጎል፣ ለክህምና ቶሎ መድረስ ሳይችሉ ቀርተው ህይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቅ ዜጎች ብዙ ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ በሀገር ኢኮሮኖሚ እና በዜጎች ኑሮ መሻሻል ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖም ከባድ ነው።

በሀገራችን በርካታ መንገዶች ቢገነቡም ገና እጅግ ብዙ መስራት ይቀራል። ብዙ ሊታዩ የሚግባቸው እጅግ በጣም ወሳኝ ቦታዎችም አሉ።

በተለይም ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ባሉባቸው አካባቢዎች በመንገድ እጦትና ብልሽት ብዙ እንግልት ይፈጠራል።

የሚሰሩ መንገዶች መጓተት፣ የጥራት ጉድለት ፣ በጊዜው አለማለቅ፣ ሲበላሽ አለመጠገን፣ ወሳኝ ቦታዎች ላይ የመንገዶችን አለመስራት ችግሮች በመንገድ ምክንያት ለሚፈጠረው እንግልት እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

ከላይ በፎቶ እና ቪድዮ የተያያዘው ከኦሮሚያ ክልል (ከቲክቫህ አባላት)ና ከአማራ ክልል (ከአሚኮና አዊ ኮሚኒኬሽን) የተገኙ ሲሆን ብዙ ቦታ የለውን የመንገድ ችግር ማሳያ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ፦

ከከሳ- ግምጃቤት - አምበላ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል። ጥገናውን መንገዱን ወደ አስፋልትነት ለማሳደግ የተረከበው የቻይናው ccecc ተቋራጭ እያከናውነው መሆኑን ተገልጿል።

የወልድያ-ጋሸና መንገድም ጥገናውን ለማክናወን (1.1 ቢሊዮን ብር) የተቋራጭነት ስራው በአማራ መንገድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ተይዞ የነበረ ሲሆን ስራው እየተሰራ በጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ ነበር ተብሏል።

ተቋራጩ ያቀረባቸው ንብረቶች በመዘረፉ ወደ ስራ ለመግባት አስቸጋሪ እንደነበር ተገልጾ አሁን ላይ የመንገዱ አገልግሎት እንዳይቋረጥ የሚያስችል ጥገና ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን አሚኮ ዘግቧል።

ፎቶ /ቪድዮ ፡ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፣ አሚኮ፣ አዊ ኮሚኒ.

@tikvahethiopia
#GujiZone

• " እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ባለው ጊዜ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ቁጥሩ ግን ሊጨምር ይችላል " - የሰባ ቦሩ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ

• " የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " - የጉጂ ዞን ኮሚኒኬሽን

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን ፤ ሰባ ቦሩ ወረዳ በድርቅ ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ ረሃብ ተከስቶ 12 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቢሮው፤ እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ ብቻ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጾ ቁጥሩ ግን ሊጨምር እንደሚችል አሳውቋል።

በወረዳው 35,442 ዜጎች አስቸኳይ ምግብ እርዳት ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን እነዚህ ዜጎች በንሳ ፣ በደጋላልቻ ፣ ሰባሎሌማሞ ፣ በኡቱሉ፣ ኦዴ ፣ ሀራጌሳ ቀበሌዎች ያሉ ናቸው ተብሏል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መኮና ሀጤሳ ፤ ለወረዳው አልፎ አልፎ የምግብ እርዳታ ቢመጣም ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።

በወረዳው የሟቾች ቁጥር በየቀኑ #እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት የምግብ እና መሰል እርዳታቸዎች መቋረጣቸው ማህበረሰሙ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን ገልፀዋል።

የጉጂ ዞን የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ፤ በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች 5 ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል ብሏል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልኮ፤ " በረሃብ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች መረጃ የለኝም " ብለዋል። ነገር ግን " በአካባቢው የፀጥታ ችግር አለ " ሲሉ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Guji-Zone-08-04

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደቡብ ክልል ? በደቡብ ክልል ስር ያሉ 10 የዞን እና 6 ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ክልሉን በሁለት ክላስተር ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቀዋል። እስካሁን በአዲስ ክልል ለመደራጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል በም/ቤቶቻቸውም አፅድቀዋል የተባሉት ፦ - የወላይታ ዞን፣ - የጋሞ ዞን፣ - የጎፋ ዞን፣ - የደቡብ ኦሞ ዞን፣ - የኮንሶ ዞን - የጌዲኦ ዞን - የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ - የቡርጂ…
#Update

" 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ጥያቄያቸውን አቅርበዋል "

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ያሉ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በሁለት ክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን እንዳቀረቡለት ገለፀ።

ዞኖቹ እና ልዩ ወረዳዎቹ በክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ዛሬ መሆኑ ተገልጿል።

የፌደሬሽን ም/ ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥያቄውን መቀበላቸውም ተነግሯል።

ም/ቤቱ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳውቃል ብለዋል።

በአንድ ላይ በክልልነት እንደራጅ ብለው ጥያቄያቸውን ያቀረቡት 10 ዞኖች እና 6ቱ ልዩ ወረዳዎች እነማን ናቸው ?

- ወላይታ፣
- ጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ኮንሶ፣
- ደቡብ ኦሞ፣
- ጌዴኦ ዞኖች
- ደራሼ፣
- ባስኬቶ፣
- ኧሌ፣
- አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ በክልል እንደራጃለን በማለት በየምክር ቤቶቻቸው በማጽደቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፦

- ስልጤ ፣
- ከምባታ ጠምባሮ፣
- ሀዲያ ፣
- ሀላባ ዞኖች
- የም ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ በመሆን አንድ ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው አፅድቀው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#ተመዝገቡ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፤ የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙኃን እንዲያደርሱ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሰኔ 27/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ #ነሐሴ_13_ቀን_2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም #በአካል_በመቅረብ ማመልከትና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

Via @EthMediaAuth
#አሜሪካ #ቪዛ

" አንዳንድ ተጓዦች የቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ድረስ ይፈጅባቸዋል "

ለጉብኝት ፣ ለሥራ ወይም ለመኖር ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚጠይቁ አመልካቾች ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ " እጅግ የተራዘመ " ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው ተሰምቷል።

ይህ የተሰማው ሰሞኑን ከወጡ የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃዎች እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

አንዳንድ ዓለምአቀፍ ተጓዦች የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ለማግኘት ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደሚፈጅባቸው ተናግረዋል።

በካቶ ኢንስቲትዩት የስደተኞች ፖሊሲ ኃላፊ ዴቪድ ቤየር ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤ " በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ለ2 ዓመታት መዘጋታቸውና ቪዛ ‘መስጠት ማቆማቸው የፈጠረው ችግር ነው’ " ብለዋል።

“ በወረርሽኙ ምክንያት የተከማቸ ሥራ አለ፤ ከአንድ ዓመት በላይ ቀጠሮ ያስፈለገውም ለዚሁ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

የቀጠሮ ርዝመት ከኤምባሲ ኤምባሲ ቢለያይም ‘አሁን ያለው ሁኔታ ግን ከ1994ቱ የሽብር ጥቃት ወዲህ የከፋ ነው’ ሲሉ ቤየር ገልፀዋል።

ከጥቃቱ ሁለት ዓመታት በኋላ ጉዳይ ለማስፈፀም የሚወስደው ጊዜ ሦስት ሳምንት ያህል እንደነበር አንድ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ በወቅቱ ለአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሠንጠረዥ እንደሚያሳየው ለአንዳንድ ቪዛ አመልካቾች ቃለ መጠይቅ ለማደረግ ከ1 ዓመት በላይ ሲወስድ የንግድና የጉብኝት ቪዛ አመልካቾች ደግሞ ከ6 ወራት በላይ እንደሚጠብቁ ተገልጿል።

አሜሪካ ለ40 ሃገሮች ተጓዦች ያለ ቪዛ ገብተው ለዘጠና ቀናት እንዲቆዩ እንደምትፈቅድ የአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሽልማት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሽልማት (በካቢኔ ውሳኔ) ፦ 🇪🇹 ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን 10 ሚሊዮን ብር 🇪🇹 የወርቅ ቅብ ሰሃን " እናመሰግናለን " የሚል ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ 🇪🇹 አትሌት ዳዊት ስዩም 250 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት መቅደስ አበበ 250 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው 350 ካሬሜትር መሬት 🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ 350…
#ሽልማት

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበው የአትሌቲክስ ቡድን አባላት የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ።

የዛሬው የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው የምስጋናና የማበረታቻ ሽልማት መርሀግብር ላይ ነው።

በዚህም መሰረት ፦

🥇 የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኙ አራቱ አትሌቶች (ለተሰንበት ግደይ፣ ታምራት ቶላ፣ ጎተይቶም ገብረስላሴ፣ ጉዳፍ ፀጋይ) ለእያንዳንዳቸው የ60 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ ፤

🥈 የብር ሜዳሊያ ላስገኙት አራት አትሌቶች (የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችውን ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ) ለእያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር ስጦታ ፤

🥉የነሀስ ሜዳሊያ ላስገኙት ኹለት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ30 ሺህ ብር ስጦታ ፤

➡️ ዲፕሎማ ላገኙ 10 አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ስጦታና ለተሳተፉ 16 አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ7 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የፌደሬሽኑ አመራሮች፣ አሠልጣኞች እና የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ መሪዎች በየደረጃቸው የተለያዩ የገንዘብ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል።

Credit : Addis Maleda Newspaper

@tikvahethiopia