TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ፣ የተመድ ተወካዮች ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ከትግራይ ክልል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ይዘው ተመልሰዋል። ከዚህ ቀደም መልዕክተኞቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ የመብራት፣ የቴሌኮም፣ የባንክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በፍጥነት ወደነበረበት…
#GoE

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች እና አምባሳደሮች የመቐለ ቆይታን በተመለከተ ጉዳዩን የያዙበት መንገድ በመንግስት ላይ ቅሬታ እንደፈጠረበት ገልፀዋል።

አምባሳደሩ፤ ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ለሰላም ንግግር ጥረት ማድረግ ሲገባቸው በሌላ ወገን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ላይ ተጠምደዋል ብለዋል።

" ተቋርጠው የሚገኙ መሠረታዊ አገልግሎቶች በተመለከተ የመንግሥት አቋም ግልጽ ነው ፤ አገልግሎት ማስጀመር የሚቻልባቸው ሁኔታ መፍጠር እና የሰላም ንግግር መጀመር ቀዳሚ መሆን አለበት " ሲሉ ገልፀዋል።

" ልዩ መልዕክተኞቹ እና አምባሳደሮቹ ከመቐለ ጉዟቸው በኋላ ባወጡት መግለጫ አሁንም ' ያልተገደብ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ' የሚል ትርክት እንደቀጠለ ነው " ያሉት አምባሳደሩ " አሁን ላይ ወደ ክልሉ ያልተገደብ በረራ እና የጭነት መኪኖች ጉዞ እየተደረገ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የነዳጅ ጉዳይም መፍትሄ እንደተሰጠውና በሁሉም አድናቆት የተቸረው ጉዳይ ነው ብለዋል።

የሰላም ንግግሩን በተመለከተም ፤ " የሚመራው የአፍሪካ ኅብረት ብቻ ነው " ሲሉ አስረግጠው ፅፈዋል።

ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥት ከህወሓት ጋር የሚደረገውን ንግግር መምራት ያለበት የአፍሪካ ኅብረት እንዲሆን ፍላጎት እንዳለው ገልጾ ነበር።

ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው " ህወሓት " ደግሞ ድርድሩ በበላይነት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንዲመሩ ጠይቆ ነበር።

ማክሰኞ ትግራይ ክልል መቐለ የተጓዙት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መልዕክተኞች ደግሞ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደውን ንግግር ለመደገፍ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ቢቢሲ ፅፏል።

ማስታወሻ t.me/tikvahethiopia/72609?single

@tikvahethiopia
ይህ ተጠቀሙ !

@officialtikvahethiopiaBot

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህ ከማንኛውም የጥላቻ አመለካከት ፣ ከአድሏዊነት ፣ ከአግላይነት ፣ ከወገንተኝነት የራቀው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ቦታ ነው።

እንደሚታወቀው በዚህ ቤተሰብ ከተሰባሰብን አመታት ተቆጥረዋል።

ትልቁ የመሰባሰባችን ምክንያት እርስ በእርስ የምናውቀውን ፣ የሰማነውን ፣ ያየነውን ፣ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነውን መረጃ፣ ጥቆማ እንድንለዋወጥ፣ ለሀገር ይሆናል ብለን የምናስበውን እንድናጋራ፣ እርስ በእርስ እንድንተጋገዝ ፣ ለሀገር በጎ አስተዋጽዖ ለማበርከት ብቻ ነው።

እርስ በእስር መረጃ ተለዋውጠን ለብዙሃኑ አባላት በይፋ የምናደርስበት መንገድ ደግሞ በውስጥ መስመር በምንላላካቸው መልዕክቶች መሆኑ ይታወቃል እስከዛሬ ስራ ላይ የነበረው @tikvahethiopiaBot ካለፉት ጥቂት ወራት አንስቶ የቴክኒክ መደነቃቀፍ ገጥሞታል በዚህም በትክክል መልዕክቶችን ለመቀበል አልተቻለም።

@tikvahethiopiaBot ተስተካክሎ ሁሉንም መልዕክቶችን መቀበል እስኪቻል ድረስ @officialTikvahethiopiaBot እንድትጠቀሙ ይሁን።

ከካለፉት ሳምንታት ወዲህ መልዕክቶችን ልካችሁ ፣ አስፈላጊውን ጥቆማ እንዲደርስ ብላችሁ በ @tikvahethiopia / @tikvahethmagazine ያልቀረበለችሁ ቤተሰቦቻችን መልዕክታችሁን በ @officialtikvahethiopiaBot በድጋሚ ላኩልን።

NB : መልዕክቶች በውስጥ እንዲያልፉ የተደረገው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትን ስብሰብ ዓላማ ያልተረዱና ሆን ብለው ሰዎችን ለመዝለፍ፣ ጥላቻ እንዲያድርባቸው ለማድረግ፣ የራሳቸውን መጥፎ አመለካከት ለማስረፅ የሚመጡትን ለይቶ ለማውጣትና ለመቀነስ ነው።

@tikvahethiopia
#ጾመ_ፍልሰታ

የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታን በተመለከተ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትከዋሽንግተን ዲሲ፤ ሰሜን አሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ፍጹም ሰላም ያላት ሀገር እንድትኖረው ነው፤ ይህ ትክክለኛ ፍላጎት ነው፡፡ ይሁንና ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ስለማይሆን ፍጹም ሰላም በሀገር ሰፍኖ ሕዝባችን እግዚአብሔር በሰጠው ምድር በፍቅር፣ በአንድነት በነጻነትና በእኩልነት እንዲኖር ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ወቅት የቅድስት ድንግል ማርያምን ጸሎትና ስእለት ተማኅፅኖና አስተበቊዖት አጋዥ አድርገን በልዩ ሱባዔ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በንሥሐ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ነዳያንን በመርዳትና ቅዱስ ቊርባንን በመቀበል እሱን መማፀን ይኖርብናል፡፡

... በሀገራችን የተከሠቱት ያላስፈላጊ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት እየተሞከሩ ያሉ አንዳንድ የሰላምና የውይይት ድምፆች ተስፋ ሰጪ ስለሆኑ ሥር ሰደው፣ በተግባር ተተርጉመው፣ ለተጐዳው ሕዝባችን መጠገኛ ይሆኑ ዘንድ፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ በዚህ ዙርያ በሱባዔው ወቅት ወደ እግዚአብሔር አቤት በማለትና ሂደቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ በዚህ በጎ ሐሳብ እንዲገፉበትና ሕዝባችንንና ሀገራችንን ከጥፋት እንዲታደጉ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የሥርየት፣የፍቅር፣ የአንድነት ጾም ያድርግልን።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ጾመ_ፍልሰታ

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶለካውያን የ2014 ዓ.ም የፍልሰታ ፆም መግቢያን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ይህንን የፍልሠታ ጾም ስንጾም እና ሱባኤ ስንገባ ምንም እንኳን ዛሬም ቢሆን በብዙ ጨለማ ተከብበን የዲያብሎስን ውጊያ እየተጋፈጥንም ቢሆን እንደ ክርስቲያንነታችን በጽኑ እምነት እና ተስፋ ተሞልተን ነው። ምክንያቱም ምንም ያኽል ቢጨላልም ንጋት አይቀርምና። ሞት የመጨረሻ ቃል የለውምና። ትንሣኤ መሆኑ አይቀርምና።

ስለሆነም እያንዳንዳችን በልባችን በዚህ በጾም ወቅት ከእኔ በላይ የተቸገረ የሚሰቃይ፣ የተፈናቀለ፣ የተሰደድ፣ በጦርነት አውድ ዘወትር በስጋት እና ጭንቀት የሚኖር አለ በማለት የወንድማዊ የርህራሄ ፣ የአለኝታነት እና የቅርበት መንፈስ እየተሰማን ሊሆን ይገባል።

እነዚህንም የጾምና የሱባኤ ቀናት በተጋድሎም በማሳለፍ ለበዓለ ፍልሰታዋ በሰላም ለመድረስ ያብቃን። አምላክ የተቀደሰ የተባረከ ጾመ ፍልሰታ ለመላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሁሉ ያድርግልን እያልኩ የደስታ ምንጭ የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለእኛ ለልጆቿ እና ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ትለምንልን፡፡ አሜን!

ቸሩ አምላካችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ኢትዮጵያን ይባርካት፡፡ "

ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕረዝደንት

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ICRC

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ህይወታቸውን እንደሚታደግ ገልጾ ፦ በሐይቅ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ኮምቦልቻ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ዓዲግራት፣ መሆኒ፣ ሽሬ፣ ኣክሱም፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ዋድላ፣ ባህር ዳር፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢዶሎ ሆስፒታሎች ያሉትን የአንድ መስኮት የአገልግሎት ማዕከላትን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሌላ በኩል ኮሚቴው በጤና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን እና ውጤታማ የሆነ ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በቅርበት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ 14 የክልል እና ዞን የኢቀመማ ቅርንጫፎች የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ መሳሪያዎችን እና የአምቡላንስ አቅርቦቶችን ድጋፍ ማድረጉ አሳውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች #ተቀብረው_ሳይፈነዱ_የሚቀሩ ፈንጂዎች በሰዎች አካል ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚገልፀው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጎጂዎችን ለመርዳት በኢትዮጵያ ውስጥ በባህር ዳር፣ ደሴ፣ አሶሳ፣ አሰላ፣ ነቀምት፣ አርባምንጭ፣ መናገሻ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ መቐለ እና ኪዩር ሆስፒታል የአካል ማገገሚያ ማዕከላትን በማጠናከር ላይ እንደሆነ ገልጿል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

በቡኢ የኮማንድ ፖስት ግብረኃይል መቋቋሙ ተሰማ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጭ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም " ሲል አሣውቋል።

በከተማ አስተዳደሩም የኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት መቋቋሙን ገልጿል።

" አብዛኛው ማህበረሰብ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ያለው የቡኢ ከተማ " " ነገር ግን አንዳንድ ሠርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የእነዚህ አፍራሽ አካላት ሴራ ሰለባ እንዳይሆን እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል " ብሏል።

ከዛሬ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮም በከተማው ውስጥ " ጉራጌ ክልል ወይም ክላስተር አንቀበልም " የሚሉ ተሸርቶችን ፣ኮፊያዎችን እና ባነሮችን ይዞ ወይም ለብሶ መውጣት እንደማይቻል አሳስቧል።

ከሰሞኑን የደቡብ ክልል ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው ውሳኔ አሳልፈው ትላንት ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርበዋል በዝርዝሩ ውስጥ የጉራጌ ዞን የለበትም።

በሁለት ተከፍሎ ከአጎራባች ዞኖች ጋር አንድ ክልል ይመሰርታል ከተባሉት ውስጥ አንዱ የጉራጌ ዞን ሲሆን ዞኑ በአዲሱ ክልል አደረጃጀት ዙሪያ እስካሁን በምክር ቤት ተሰብስቦ አልወሰነም / አላፀደቀም።

የዞኑ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ከቀናት በፊት ፤ " የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው " ሲሉ ገልፀው ፤ የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት ዙሪያ እንዳልተወያየትና በቀጣይ በጉዳዩ መቼ ውይይት እንደሚደግ እንደማይታወቅ ገልፀው ነበር።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።

ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳቦ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳቦ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።

ቴሌብር ቁጠባ፦ ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን ወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳቦ ገቢ ይደረጋል።

ተጨማሪ መረጃ እንልክላችኃለን!

@tikvahethiopia
" ... አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው " - የሶማሌ ክልል ፕ/ት ሙስጠፌ ሙሁመድ

በቅርቡ በሶማሊያና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ጥቃት ፈፅሞ የነበረው የአልሸባብ ቡድን 800 ታጣቂዎቹ መገደላቸውን 100 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ በተረጋገጠ ትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

የአልሸባብ ጥቃት በሽንፈት መጠናቀቁን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሙስጠፌ አልሸባብ ዳግመኛ ወደ ድንበር እንዳይጠጋ እና እንዳይዳፈር የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia