TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
20/80🔝

ነገ ረቡዕ የካቲት 27 በእጣ ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፈው የ20/80 #የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ዝርዝር እና #በዕጣው ለመግባት የሚያስፈልገው የቁጠባ መጠን።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ /ያለመከሰስ መብት ተነሳ። የደገፉ የምክር ቤት አባላት ፦ 93 ድምፀ ተአቅቦ ፦ 6 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል እና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ የተደረገው በፍትህ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ ነው። የህግ ከለላው የተነሳው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን…
#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች #ፍትህሚኒስቴር

ፍትህ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ላይ (ከዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት መነሳት ጋር የተያያዘ) ፦

" ... ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ምሩፅ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀርበው በሰጡት መግላጫ እንዲሁም በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ለህዝብ በይፋ በሰጡት ማብራሪያ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ቴክኖሎጂውን አልምቶ የጨረሰ በመሆኑ ቴክኖሎጂው ከሰው ንክኪ ነፃ በመሆኑና በኢንሳ በኩል ተፈትሾ ማረጋገጫ ያገኘ እንዲሁም ለዕጣው አወጣጥ ከባንክ የተላከው ዳታ በአግባቡ የተጫነ መሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።

መስተዳደሩም የኃላፊውን ማረጋገጫ በመቀበል እና በማመን ዕጣው ሐምሌ 1 በህዝብ ፊት እንዲወጣ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከተሰጠው ማረጋገጫ በተቃራኒ ከፍተኛ ከፍተኛ የሆነ የዳታ ማጭበርበር ተግባር የተፈፀመ መሆኑ አመላካች መረጃ በማግኘት ኦዲት እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቶ እንዲፈተሽ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት ከኢንሳ ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከኢኖቬሽን ሚኒስቴር በተዋቀረው የባለሞያ ቡድን በተደረገው ማጣራት ፦

1ኛ. ሲስተሙ አዲስ እና የገባው ዳታ በማንም ያልታየ ለመሆኑ ለከተማው አመራር ጭምር በኃላፊው ማረጋገጫ የተሰጠ ቢሆንም ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ወደ ኮምፒዩተሩ የገባውን ዳታ ለአምስት ጊዜ የተመለከቱ መሆኑ፤

2ኛ. ለዕጣ ብቁ ናቸው ተብሎ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተላከው 79 ሺህ ተመዝጋቢዎች በላይ ለዕጣው ብቁ ያልሆኑ 73 ሺህ ሰዎችን በድብቅ ወደ ኮምፒዩተሩ በመጫን የተጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 172 ሺህ እንዲያድግ ያደረጉ መሆኑ፤

3ኛ. ኃላፊው ከቤቶች ልማት የተላከውን የተወዳዳሪዎችን መረጃ ለሚያስገባ ባለሞያ ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ እንዲሰራ ማድረግ ሲገባቸው በቀጥታ ለአልሚው በመስጠት የዳታ ማጭበርበሩ እንዲፈፀም ያስደረጉ መሆኑ፤

4ኛ. ሲስተሙ የማልማት ተግባሩ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያልጠበቀና የሚና መደበላለቅ የታየበት በተለይም ሶስቱን አካላት አልሚውን፣ የተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የሚና ክፍፍል የሌለበት እና ሁሉም በአንድ ሰው ማለትም በአልሚው ብቻ የተሰራ በመሆኑ አሁን ለተከሰተው ማጭበርበር በር እንዲከፍት ያደረገ መሆኑ፤

5ኛ. ዳታው የተጫነበት ኮምፒዩተር አዲስ እና የዳታ አጠቃቀሙን ከእጅ ንክኪ ነፃ እንዲሆን የሚፈልግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኮምፒዩተሩ ለስራው የማይፈለግ ባዕድ ሶፍትዌር ጭምር የተጫነበት ከመሆኑ በላይ የዕጣ አወጣጥ ሂደቱን በኦንላይን ጭምር እንዲከታተሉ የሚያስችል የነበረ መሆኑ ፤

6ኛ. ስለደህንነቱ ምንም አይነት ፍተሻ ባልተደረገበት ቴክኖሎጂ በኢንሳ ተፈትሾ ችግር እንደሌለበት ማረጋገጫ የተሰጠበት ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ የከተማ አስታዳደር አመራሩን በማሳሳት ዕጣ እንዲወጣ ያስደረጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

በአጠቃላይ ዕጣውን ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ ወይም ሲስተም የአሰራር ስርዓቱን ያልተከተለ፣ አግባብ ባለው ተቋም ያልታየና ምንም አይነት የደህንነት ማረጋገጫ ያልተሰጠበት፣ ለማጭበርበር የሚረዳ ባዕድ ሶፍትዌር የተጫነበት ፣ ለዕጣው ብቁ ናቸው ተብሎ ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ ከተላከው ዳታ ውጭ ሌላ ዳታ ማስገባት መረጃ መጨመር፣ ማጥፋት እንዲሁም ማስተካከል የሚያስችል እድል ለአልሚው በድብቅ የሚሰጥ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል።

ድርጊቱ በቢሮው ኃላፊ እና በስሩ የተሳተፉት ሌሎች ግለሰቦች የተፈፀመ መሆኑ ተረጋግጦ አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። "

@tikvahethiopia
#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ፦

" ...የ20/80 ባለ ሶስት መኝታ ቤት እጣ ውስጥ ያልተካተተ መሆኑ ይታወቃል ይህም ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 9 አመታት ያህል ሳያቋርጡ በመቆጠብ ላይ ቢገኙም በ14ኛ ዙር አጣ ውስጥ ሳይካተት መቅረቱ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው በእጣው ተሳታፊ ያልሆኑ የማህበረሰብ ከፍሎች መግለጻቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ማወቅ ተችሏል፡፡

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካለው ገቢ አንጻር በ1997 እና 2005 ዓ/ም ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ ምዝገባ በማካሄድ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር መቅረፍ ሲገባው በቀደመው አሰራር የነበረውን ኢፍትሃዊ፣ ለዘረፋና ለማጭበርበር የተመቸ የእጣ አወጣጥ አሰራር የቀጠለ መሆኑን በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡

ስለዚህ ከዚህ አሰራር ራሱን በማረም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች ግልፀኝነትንና ፍትሃዊነትን በተከተለ ሁኔታ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡ "

(የኢሰመጉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia